የቀድሞ የሶቪየት መሪ ሚኻኤል ጎርባቾቭ ከባለቤቱ ጋር ምሥራቅ ጀርመንን ከጎበኘ በኋላ በባበሩ ወደ ሩስያ እየተመለሰ ነበር፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ ባለቤቱ፣ ‹‹ውዱ ሚኻኤል፣ የት ነን?›› ስትል ጠየቀችው፡፡
እጁን በመስኮት አውጥቶ፣ ‹‹ገና ጀርመን ውስጥ ነን፣ ውዴ›› ብሎ መለሰላት፡፡ ከሰዓታት በኋላ ‹‹አሁንስ የት ነን?›› ስትል ጠየቀችው፡፡ እጁን በመስኮት አውጥቶ ‹‹አሁን ፖላንድ ነን፤›› አለ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ባለቤቱ ጥያቄዋን ሰለሰች፡፡ ‹‹አሁን የት ነው ያለነው?›› እንደልማዱ እጁን በመስኮት አውጥቶ ቆየና፣ ‹‹ሩስያ ገብተናል፤›› አላት፡፡
ባለቤቱ፣ ‹‹እጅህን በመስኮት በማውጣት ብቻ የት እንዳለን ማወቅ እንዴት ቻልክ?›› ስትል በጉጉት ጠየቀችው፡፡
አረፈ ዓይኔ ሐጎስ ‹‹ፖለቲከኞች እፈሩ›› [2013]