Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊቻይና ለኢትዮጵያ የደገፈችው የኮቪድ-19 ክትባት አንድ ሚሊዮን ደረሰ

ቻይና ለኢትዮጵያ የደገፈችው የኮቪድ-19 ክትባት አንድ ሚሊዮን ደረሰ

ቀን:

ቻይና በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመቀነስ ስታደርግ ከየቆችው የመከላከያ ቁሳቁስ በተጨማሪ እስከያዝነው ሳምንት ድረስ አንድ ሚሊዮን ክትባቶችን ሰጥታለች፡፡

በተለይ በሥራቸው ፀባይ ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለመከተብ ይውላል የተባለውን 300,000 ዶዝ የሲኖፋርም ክትባት፣ ነሐሴ 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቻይና መንግሥት የተረከበው ጤና ሚኒስቴር ቻይና እስካሁን የለገሰችው የኮቪድ-19 ክትባት መጠን አንድ ሚሊዮን ደርሷል ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዥያዎ ዢዮዋን ክትባቱን ለጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ባስረከቡበት ወቅት፣ ከቻይና መንግሥት ለሦስተኛ ጊዜ ድጋፍ የተደረገው 300 ሺሕ ዶዝ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት በዋናነት በሥራቸው ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች በተለይም በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንደሚውል ዶ/ር ሊያ ተናግረዋል፡፡ ድጋፉ እየበዛ የመጣውን የኮቪድ-19 ሕሙማንና የሥርጭቱን ጫና ለመቀነስ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ሲሉም አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመግታት የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቤጂንግ በኮቫክስ ጥምረት በኩል 300 ሺሕ ዶዝ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት መላኳን አምባሳደር ዢዮዋን ገልጸው፣ አገሪቱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመግታት በምታደርገው ጥረት ቻይና ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አሳውቀዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ክትባቱ በዋናነት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንደሚውልና የትምህርት ዘርፉንም እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

በትምህርት ዘርፍ ላይ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል ከ50,000 በላይ መምህራን እንደተከተቡም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። የአሁኑ የቻይና መንግሥት ድጋፍ 150,000 መምህራንን ለመከተብ እንደሚያስችል ታውቋል። ክትባቱም የመደበኛ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለመምህራንና በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ላሉ ባለሙያዎች እንደሚደርስ ተገልጿል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...