Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊክንፉን የዘረጋው የኮቪድ ሦስተኛው ዙር

ክንፉን የዘረጋው የኮቪድ ሦስተኛው ዙር

ቀን:

በየትኛውም የዓለም ክፍል ወረርሽኝ ሆኖ የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈው ኮቪድ-19 አሳሰቢነቱ ከምንጊዜውም በላይ እየሆነ ነው፡፡

ወረርሽኙ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ከዓመት ተመንፈቅ በኋላ ወደ ሦስተኛ ደረጃ እየሄደ መሆኑ ከነሐሴ መባቻ ጀምሮ በተለይ በኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሲነገር ቆይቷል፡፡

ይህንኑ ከሁለት ሳምንት በፊት የተንፀባረቀ ነጥብን የሚያጠናክር በኢትዮጵያ ሦስተኛ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስለመከሰቱ ምልክቶች መታየታቸውን የጤና ሚኒስቴር በይፋ ገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ነሐሴ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ ሦስተኛው ዙር (ዌቭ) ስለመከሰቱ ማሳያዎች በመኖራቸው ኅብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስበዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት (ከነሐሴ 10-16) ብቻ 5547 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፣ 66 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ 510 ሰዎችም በፅኑ መታመማቸውን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።

በዚህም ከጥቂት ወራት በፊት ከሁለት እስከ ሦስት በመቶ የነበረው የመያዝ ምጣኔ በአሁኑ ወቅት ወደ 12 በመቶ ያደገ መሆኑን አብራርተዋል።

ቅዳሜ ነሐሴ 15 ቀን የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 6,108 ሰዎች መካከል 1,282ቱ በቫይረሱ መያዛቸው የሚያመለክተው ወረርሽኙ በፍጥነት እየተስፋፋ መምጣቱን ነው። ቅዳሜ  የተመዘገበው ቁጥር ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከታዩት ከፍተኛው መሆኑ ታውቋል።

በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ካልተደረገ ችግሩ ከዚህ የከፋ እንደሚሆን ሳይንሳዊ ትንበያዎች እንዳሉም ሚኒስትሯ አመልክተዋል።

የቫይረሱን ሥርጭት በተመለከተ በአገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ በሆቴሎች፣ በስብሰባዎች፣ በእምነት ተቋማትና በማኅበራዊ መስተጋብሮች አካባቢ መዘናጋቶች መኖራቸው ይስተዋላል።

‹‹የችግሩ መውጫ ቁልፍ በእጃችን ነው›› ያሉት ሊያ (ዶ/ር) ስብሰባዎችን መቀነስ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ የእጅ ንጽህናንና ክትባት በመከተብ ሰው ራሱንና ቤተሰቦቹን ከቫይረሱ እንዲጠብቅ ጠይቀዋል።

በብዛት እየተሰራጨ ያለው ቫይረስ በአብዛኛው የሚያጠቃው ያልተከተቡ ሰዎችንመሆኑ ክትባቱ የሚመለከተው ሁሉ መውሰድ እንዳለበትም አሳስበዋል።

ክትባቱን በአዲስ አበባ በሁሉም ጤና ጣቢያዎችና ክልሎችም እየተሰጠ መሆኑንም አስታውሰዋል። በኢትዮጵያ በዓለም የጤና ድርጅት የፀደቁ 2.4 ሚሊዮን የሚደርሱ ወገኖች መከተባቸው ታውቋል።

ሔልዝ ዴስክ በድረ ገጹ እንዳስታወቀው፣ አንደኛና ሁለተኛ ሦስተኛ እየተባለ የሚጠራው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭት፣ ጉዳት የማድረስ መጠኑ እንደየ አገሮች ይለያያል፡፡ በአንድ አገር ውስጥ ሆኖም ከሥፍራ ሥፍራ ሊለያይ ይችላል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ሲታይም ከሁሉም አካባቢዎች ይበልጥ ተጋላጭ የሆነው የአዲስ አበባ ነዋሪ ነው፡፡ ከተማዋ በሕዝብ መጨናነቋ፣ የትራንስፖርትና የሌሎችም አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንደከዚህ ቀደሙ የኮቪድ መከላከያ መርሆችን ለመተግበር ያላቸው ቸልተኝነት፣ ቫይረሱ እየጠፋ ነው ወይም የለም የሚለው አመለካከት ለቫይረሱ መልሶ ማንሰራራት ጉልህ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...