Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልአገር አቀፍ የቴአትር ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

አገር አቀፍ የቴአትር ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

ቀን:

በአዲስ አበባ አገር አቀፍ የቴአትር ፌስቲቫል ሊካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ ቴአትር ባለሙያዎች ማኅበር አስታወቀ፡፡

ማኅበሩ ይህንን የገለጸው ማክሰኞ ነሐሴ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡ ፌስቲቫሉ የሚካሄደው በተመረጡ ስምንት ቦታዎች መሆኑን፣ በአጠቃላይ 48 አጫጭርና የሙሉ ጊዜ ቴአትሮች ለተመልካች ይቀርባል ተብሏል፡፡

የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱል ከሪም ጀማል እንደገለጹት፣ ከነሐሴ 21 እስከ 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ደረስ የሚካሄደው ይህ የቴአትር ፌስቲቫል፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ለማነቃቃትና ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ነው፡፡

- Advertisement -

በፌስቲቫሉ ከሚቀርቡት 48 ቴአትሮች መካከል 20 የሚሆኑት ከዚህ በፊት ለዕይታ የቀረቡና አሁንም እየታዩ የሚገኙ፣ 26 የሚሆኑ ደግሞ አጫጭርና ቅንጭብ መሆናቸውን ተጠቁሟል፡፡ ከዚህ በፊት ታይተው በመድረክ ላይ ተቀርፀው የተቀመጡ በእስክሪን አማካይነት ለተመልካች እንደሚቀርቡ ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡

ትርዒቶቹም ከ20 ደቂቃ እስከ 2፡30 ሰዓት ቆይታ ያላቸው መሆኑን የገለጹት አቶ አብዱል ከሪም፣ ከነባር እስከ አዳዲስ የቴአትር ሥራዎች በመድረክ የሚታዩ ይሆናል፡፡ ከሚታዩት ቴአትሮች ውስጥም ሦስት የሚሆኑት በኦሮሚኛ ቋንቋ የተሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በፌስቲቫሉም 16 ተቋማት ተውኔቶቻቸውን ለማቅረብ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልጸው፣ በግለሰብ ደረጃም ተውኔቶቻቸውን ለማቅረብ የተዘጋጁ ባለሙያዎች እንዳሉም አብራርተዋል፡፡ በቴአትር ፌስቲቫል የሚሳተፉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣ የሀገር ፍቅር ቴአትር፣ የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ፣ ራስ ቴአትር፣ ሕፃናትና ወጣቶች ቴአትር፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲና ሌሎችም ተቋማት እንደሚሆኑ ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ተገልጿል፡፡

ከዓርብ ነሐሴ 21 ቀን ጀምሮ የሚካሄደው ፌስቲቫል ዘርፉን በማነቃቃት ወደነበረበት ከፍታ ለመመለስና አዳዲስ የፈጠራ ሥራ ያላቸውን የቴአትር ባለሙያዎችን ከተመልካቾች ጋር ለማገናኘት ያለመ መሆኑን በማኅበሩ የፌስቲቫሉ አስተባባሪ ወ/ሮ መዓዛ ወርቁ ተናግረዋል፡፡

​​​​​​​የቤኒያሚን ኔታንያሁ የሥልጣን ስንብት

በፌስቲቫሉ ከ48 በላይ የሚሆኑ ቴአትሮች ለተመልካች ለማሳየት ዕቅድ ቢያዝም፣ በገንዘብ እጥረትና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ትዕይንታቸውን ሊያቀርቡ እንዳልቻሉ ወ/ሮ መዓዛ ገልጸዋል፡፡

በተለይም በአንዳንድ ከያንያን በኩል ያለው የአመለካከት ችግር የጎላ መሆኑን የገለጹት አስተባባሪዋ፣ በመንግሥት መዋቅር ሥር ያሉ ተቋማት ላይ በሚታየው ክፍተት ዘርፉን ማሳደግ እንዳልተቻለ አክለዋል፡፡

ለአምስት ቀን የሚቆየው ይህ ፌስቲቫል በቴአትር ላይ ያሉ ችግሮች ለመለየት በመፍትሔ ላይ አብሮ በመምከር ለወደፊት በሙያው ችግር ላይ ለመሥራት የሚያስችል የተግባቦት ሰነድ በማዘጋጀት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡

ዘርፉንም አንድ ዕርምጃ ከፍ ለማድረግ ማነቆ ከሆኑ ነገሮች መካከል የፋይናንስ እጥረትና ሌሎች ችግሮች መሆናቸውን ወ/ሮ መዓዛ ሳይናገሩ አላለፉም፡፡

ፌስቲቫሉ የሚካሄድባቸው ቦታዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣ የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት፣ አምባሳደር ሲኒማ፣ የኦሮሚያ ባህል ማዕከል፣ የአዶት ሲኒማ፣ የሴንቸሪ ሲኒማ፣ የኤድናሞል ሲኒማና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ናቸው፡፡  

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...