Saturday, June 22, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

እያሽቆለቆለ የመጣው የቆዳና ሌጦ ወጪ ንግድ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ታገኝባቸው ከነበሩ ምርቶች ከቡና ቀጥሎ ቆዳና ሌጦ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የቁም እንስሳትም በውጭ ምንዛሪ ግኝት የነበራቸው አስተዋጽኦ ቀላል አልነበረም፡፡ አሁን ላይ ግን እነዚህ ምርቶች በአገሪቱ የወጪ ንግድ ገቢ ላይ እንደ ቀድሞ ተጠቃሽ ቦታ እየያዙ አይደለም፡፡

እነዚህ ምርቶች ቦታቸውን ለአበባና ለማዕድን ምርቶች እየለቀቁ ስለመሆኑ እየታየ ነው፡፡ የ2013 በጀት ዓመት የወጪ ንግድ አፈጻጸም እንደሚያሳየውም፣ ከቡና ቀጥሎ ያለውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት የማዕድንና የአበባ ምርቶች ተጠቃሽ ሆነዋል፡፡

በቀደሙት ዓመታት ከአጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ ከፍ ያለውን ቦታ ይዘው ይታዩ ከነበሩት የወጪ ንግድ ምርቶች መካከል አንዱ የነበረው የቆዳና የቆዳ ውጤቶች በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ እየወረደ መጥቷል፡፡

እንደማሳያ የሚሆነውም በ2010 በጀት ዓመት ከቆዳና ከቆዳ ውጤቶች የተገኘው የውጭ ምንዛሪ 132.4 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ከአጠቃላዩ የወጪ ንግድ ገቢ የነበረው ድርሻ 4.7 በመቶ ነው፡፡ ይህ ምርት በ2011 በጀት ዓመት ያስገኘው የውጭ ምንዛሪ ወደ 117.4 ሚሊዮን ዶላር ወርዷል፡፡ ይህም በበጀት ዓመቱ ከአጠቃላይ ወጪ ንግድ ገቢ ድርሻው ወደ 4.4 በመቶ ዝቅ እንደል አድርጎታል፡፡

የቆዳና የቆዳ ውጤቶች የቁልቁለት ጉዞ ቀጥሎ በ2012 በጀት ዓመት ከአጠቃላይ ወጪ ንግድ ድርሻው ወደ 2.4 ወርዶ ዓመታዊ የገቢ ድርሻውም ሚሊዮን ዶላር ሆኗል፡፡ ይህም ውጭ ምንዛሪ ግኝቱ በ36 በመቶ መውረዱን የሚያመለክት ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከቀዳሚው ዓመት ያነሰ ገቢ የተመዘገበበት ሆኗል፡፡

እንደ ቆዳና ሌጦ ያሉ የቀንድ ከብት፣ ሥጋና ተያያዥ የወጪ ንግዱ መውረድ የቀድሞ ደረጃቸውን እያሳጣቸው ሲሆን፣ ቦታውን እንደ አበባ ላሉ ምርቶች እንዲለቁ አድርጓቸዋል፡፡ የአበባ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችም ቢሆኑ፣ በዕቅዳቸው ልክ የታሰበውን ያህል ገቢ ማስገኘት ባይችሉም ከመጀመሪያዎቹ ሦስት የአገሪቱ የወጪ ንግድ ማስገኛ ምርቶች መካከል አንዱ መሆን አስችሏቸዋል፡፡ 

በኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ምርት ሰንጠረዥ ውስጥ ከተቀላቀለ 16 ዓመታትን ያስቆጠረው የአባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ በ2013 በጀት ዓመት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት በሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ከአበባ የወጪ ንግድ በ2013 በጀት ዓመት የተገኘው የውጭ ምንዛሪ 513 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ የሚያመለክት ሲሆን፣ ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር በንፅፅር ሲታይ ከ75 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብልጫ ያለው ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የአበባ አትክልትና ፍራፍሬ የወጪ ንግድ በ1996 ዓ.ም. ከዘርፉ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ 28 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ነው፡፡ አሁን ላይ 513 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ምርቱ የሚያስገኘው የውጭ ምንዛሪ ዕድገት ማሳየቱን ነው፡፡

የአበባ አትክልትና ፍራፍሬ ምርት የወጪ ንግድ በየዓመቱ ዕድገት እያሳየ በመምጣቱ ሦስተኛው የአገሪቱ የወጪ ንግድ ማግኛ በመሆን ቢጠቀስም፣ በተለይ በ2013 በጀት ዓመት ከተያዘለት ዕቅድ አንፃር አፈጻጸሙ ዝቅ ያለ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተለይ ዘርፉን በተመለከተ የአሥራ አንድ ወር ግምገማ በተደረገበት ወቅት የታየውም ይኸው ነው፡፡

ባለፉት አሥራ አንድ ወራት ከአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ በድምሩ 608.42 ሚሊዮን ዶላር ለማስገኘት ታቅዶ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ 474.11 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ተችሏል፡፡ ይህም ከተያዘው ዕቅድ አንፃር 77.93 በመቶ አፈጻጸም ያለው መሆኑን ሲያሳይ፣ ካለፈው በጀት ዓመት 11 ወራት ክንውን አኳያ ሲታይ በ3.625 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ0.76 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

ከሆርቲካልቸር ዘርፍ ትልቁን ድርሻ ከያዘው የአበባ ኤክስፖርት ባለፉት አሥራ አንድ ወራት 484.70 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ 420.87 ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ ይህም ከተያዘው ዕቅድ አንፃር 86.83 በመቶ አፈጻጸም ያለው መሆኑን ሲያሳይ፣ ካለፈው በጀት ዓመት 11 ወራት ክንውን አኳያ ሲታይ ደግሞ የ4.37 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በሌላ በኩል ከአትክልት ኤክስፖርት በድምሩ 104.98 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ 41.37 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ሲገኝ ይህም ከተያዘው ዕቅድ አንፃር 39.41 በመቶ አፈጻጸም እንዳለው ያሳያል፡፡  ካለፈው በጀት ዓመት 11 ወራት ክንውን አኳያ ሲታይ ደግሞ የ31.67 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

ከፍራፍሬ ምርቶች ኤክስፖርት 18.74 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ 11.88 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ይህም ከተያዘው ዕቅድ አንፃር 63.38 በመቶ አፈጻጸም አለው፡፡ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት 11 ወራት ክንውን አኳያ ሲታይ የ14.98 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

ከገቢ አንፃርም ከዘርፉ ይገኛል ተብሎ ስለታቀደውና የተገኘውን ገቢ በተመለከተ የተጠቀሰው ደግሞ፣ ባለፉት አሥራ አንድ ወራት ከአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ በድምሩ 608.42 ሚሊዮን ዶላር ለማስገኘት ታቅዶ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ 474.11 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ተችሏል፡፡ ይህም ከተያዘው ዕቅድ አንፃር 77.93 በመቶ አፈጻጸም ያለው መሆኑን ሲያሳይ ካለፈው በጀት ዓመት 11 ወራት ክንውን አኳያ ሲታይ በ3.625 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ0.76 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

ከሆርቲካልቸር ዘርፍ ትልቁን ድርሻ ከያዘው የአበባ ኤክስፖርት ባለፉት አሥራ አንድ ወራት 484.70 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ 420.87 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ተችሏል፡፡ ይህም ከተያዘው ዕቅድ አንፃር 86.83 በመቶ አፈጻጸም ያለው መሆኑን ካለፈው በጀት ዓመት 11 ወራት ክንውን አኳያ ሲታይ ደግሞ የ4.37 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ከአትክልትና ኤክስፖርት በድምሩ 104.98 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ 41.37 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ ይህም ከተያዘው ዕቅድ አንፃር 39.41 በመቶ አፈጻጸም ያለው መሆኑን ሲያሳይ ካለፈው በጀት ዓመት 11 ወራት ክንውን አኳያ ሲታይ የ31.67 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ከፍራፍሬ ምርቶች ኤክስፖርት 18.74 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ 11.88 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ሲገኝ ይህም ከተያዘው ዕቅድ አንፃር 63.38 በመቶ አፈጻጸም እንዳለው አሳይቷል፡፡ ካለፈው በጀት ዓመት 11 ወራት ክንውን አኳያ ሲታይም የ14.98 በመቶ ቅናሽ አለው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች