Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሥር እየሰደደ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ‹‹ከኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በተጨማሪ ክትባቱን መከተብ...

ሥር እየሰደደ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ‹‹ከኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በተጨማሪ ክትባቱን መከተብ አስፈላጊ ነው!››

ቀን:

የጤና ሚኒስቴር ነሐሴ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው አሁናዊ መረጃ፣ በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ብቻ 1,621 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ መያዛቸውን፣ 13 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል፡፡ በዚሁ ቀንም 561 ግለሰቦች በፅኑ ሕሙማን ሕክምና ክፍል ይገኛሉ ብሏል።

በየዕለቱ የማስጠንቀቂያ መልዕክቶች እያስተላለፍን ብንገኝም ወረርሽኙ ሥር እየሰደደ ይገኛል ያለው ሚኒስቴሩ፣ አሁንም የመከላከያ መንገዶችን በመተግበር የኮቪድ-19 ቫይረስን በጋራ እንከላከል ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

ሰሞኑን የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (/ር)፣ በኮቪድ-19 ወረርሽኝና ክትባት ዙሪያ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹጽ፣ ከጥቂት ወራት በፊት ሁለትና ሦስት በመቶ የነበረው የሥርጭት ምጣኔ በአሁኑ ሰዓት በአማካይ አሥራ ሁለት በመቶ ደርሷል፡፡ በየቀኑ ወደ ፅኑ ሕክምና ማዕከላት የሚገቡ ሰዎች ቁጥርም በእጅጉ መጨመሩን አመልክተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አሁን ላይ ያለው ቁጥራዊ መረጃዎችና ሁኔታዎች የሚያሳዩት የሦስተኛው ዙር ማዕበል በኢትዮጵያ እየጀመረ ስለመሆኑ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ማኅበረሰቡ የሚጠበቅበትን መሠረታዊ የመከላከያ መንገዶችን አጠናክሮ ከዚህ በፊት ከነበረው በበለጠ የማይተገብር ከሆነ፣ ነገሮች እየከፉ ሊመጡ እንደሚችሉ ሳይንሳዊ ትንበያዎች ያሳያሉ ብለዋል፡፡ በመሆኑም መሠረታዊ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በተጨማሪ ክትባቱን መከተብ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

እስካሁን እንደ አገር 2.3 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን ለማኅበረሰቡ መስጠት ተችሏል ያሉት ሚኒስትሯ አያይዘውም፣ በአዲስ አበባ ዕድሜያቸው 35 ዓመት በላይ የሆኑ፣ ዕድሜያቸው 18 ዓመት በላይ ሆኖ ተጓዳኝ ሕመም ያለባቸውና በሥራቸው ምክንያት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች፣ እንዲሁም በክልሎች ዕድሜያቸው 55 ዓመት በላይ የሆኑ፣ ዕድሜያቸው 18 ዓመት በላይ ሆኖ ተጓዳኝ ሕመም ያለባቸውና በሥራቸው ምክንያት ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተከተቡ እንደሚገኙና የሚመለከታቸው የማኅበረሰብ ክፍሎችም ወደ ጤና ተቋም እየሄዱ እንዲከተቡ ሚኒስትሯ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት አሳስበዋል፡፡

እንደ ማሳሰቢያው ማኅበረሰቡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭት ለመግታትና ለመቆጣጠር ከዚህ በፊት ያደርገው ከነበረው በበለጠና በተጠናከረ ሁኔታ አካላዊ ርቀትን 2 ሜትር መጠበቅ፣ ማስክን ሁልጊዜና በአግባቡ ከማድረግ ባለፈ፣ የእጅ ንፅህናን በተገቢው መንገድ መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ አላስፈላጊ መሰባሰቦችን መቀነስ (በተለይ በዝግ ቦታዎች ላይ የሚደረጉትን) እንዲሁም ምልክቶች ሲታዩም በአፋጣኝ ራስን በማግለል የባለሙያ ምክር መጠየቅ ይገባል ያሉት ሚኒስተሯ፣ ከዚህ በተጨማሪ የቫይረሱንርጭት ለመግታት እንዲያግዝም በሥራ ላይ የነበረው የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ ቁጥር 30/2013 ማሻሻያ ተደርጎበታል ብለዋል፡፡

 በአዲሱ መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 803/2013) ዙሪያ ለሕዝብ ተከታታይ ገለፃ እንደሚደረግ፣ እንዲሁም የሕግ ማስከበርራው እንደሚጠነክር የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

በተያያዘም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ መንገዶች በአግባቡ እንዲተገበሩ ያሳሰበው የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ 8335 ወይም የክልል ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ማግኘት እንደሚቻል አስታውቋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የኮቪድ-19 ምልክት የሚያሳይ፣ የጉንፋን ምልክት ያለበት በአጠቃላይ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ የሚፈልግ በሁሉም የመንግሥት ጤና ተቋማት በመሄድ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ እንደሚችል አሳስቧል፡፡ የኮቪድ-19 ሥርጭት የከፋ አደጋ እንዳያደርስ ለቫይረሱ ሥርጭት ምክንያት እንዳይሆኑም አደራ ብሏል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ (Antigen RDT) ምርመራ ምንነትን እንዲህ ገልጾታል፡፡

 

የኮቪድ-19 ቫይረስ ምርመራ 30 ደቂቃ እንደሚደርስ ይውቃሉ?

ኮቪድ-19 ምርመራ ባደረጉ 30 ደቂቃ ውስጥ ውጤት የሚያደርስ የኮቪድ-19 መመርመርያ መሣሪያ (Antigen RDT) በሁሉምመንግሥት የጤና ተቋማት ይገኛል፡፡ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የኮቪድ-19 ምልክት ያለው፣ እንዲሁም የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ የሚፈልግ የማኅበረሰብ ክፍል በሁሉም የመንግሥት የጤና ተቋማት በመሄድ ምርመራውን ማግኘት ይችላል፡፡

ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ ጥቅሞች (Antigen RDT):_

◾️ምርመራው በተደረገ 30 ደቂቃ መድረሱ

◾️የኮቪድ-19 ቫይረስ ከተገኘባቸው ራስን በፍጥነት መለየት ስለሚቻል የቫይረሱ ሥርጭት መቀነስ ይቻላል

◾️ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ወደ ጤና ተቋም የሚሄድ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ይችላል፣ ውጤቱንም እዛው ያገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...