Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

ቀን:

የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን በአሁኑ ጊዜ የተከሰቱ አጠቃላይ ችግሮችን ለማብረድና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን፣ ግጭትና ጥቃት እንዲሁም ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ፡፡

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል ተፈርሞ ለሪፖርተር በተላከ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ኮሚሽኑ ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎችን በማሰባሰብ፣ በየአካባቢው የተከሰቱ ግጭቶችና ጥቃቶችን ከእነ መንስዔዎቻቸውና መፍትሔያቸው ለመለየትና ለማጥናት ሞክሯል፡፡

በውጤቱ ማወቅ የተቻለው ግን ሥር የሰደደ ችግር በሕዝብ መካከል አለመኖሩን ነው፡፡ የአገር ሽማግሌዎች ዕድሉ ከተሰጣቸውና የሚሉትን መስማት ከተቻለ የተፈጠሩትን ችግሮች ከማርገብ ባለፈ በዘላቂነት መፍታት የሚችሉ መሆናቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

በመሆኑም ግጭቱ፣ ጥቃቱና ጦርነቱ ባለባቸው አካባቢዎች የሃይማኖት አባቶች ከሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች ከአገር ሽማግሌዎች፣ እናቶች ከእናቶች፣ እህቶች ከእህቶች፣ ወጣቶች ከወጣቶችና፣ ምሁራን ከምሁራን ጋር በስፋት ውይይት እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

በጦርነቱና ግጭቱ ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸውንና ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚችለውን በማድረግ መልሶ እንዲያቋቁሙ እንዲያደርግ የጠየቀው ኮሚሽኑ፣ አክቲቪስቶችም ሆኑ ጋዜጠኞች የሚያስተላልፏቸው መረጃዎች ግጭቶችን የሚያባብሱ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስቧል፡፡

የውጭ መንግሥታታ፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ሆኑ ለትርፍ ያልተቋቋሙ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ግጭቶችን ለማስቆም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣ የአገር ሉዓላዊነትን ከሚጥስና ከወገንተኝነት የፀዳ እንዲሆንም አሳስቧል፡፡ 2014 ዓ.ም. ሁሉም ነገር ተወግዶ የሰላም ዓመት እንዲሆን ምኞቱን ገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...