ኢትዮጵያዊቷ የዓለምዘርፍ የኋላው እሑድ ነሐሴ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በአየርላንድ በተከናወነው የግማሽ ማራቶን ውድድር በ63:43 ደቂቃ በመፈጸም የዓለም ክብረ ወሰንንን ሰብራለች። ቀደም ሲል ክብረ ወሰኑ በ64፡02 ደቂቃ ተይዞ የነበረው በኬንያዊቷ ሩት ቼፕንጌቲች ነበር። ዲደብሊው እንደዘገበው፣ የዓለምዘርፍ ከውድድሩ በኋላም በሰጠችው ቃለ መጠይቅ «ሕልሜ ዕውን ኾኗል» በማለት ደስታዋን ገልጻለች።