Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

በሆንኩኝ አቧራ

ትኩስ ፅሁፎች

በሆንኩኝ አቧራ

‹‹ዐይቶ ዝም ሰምቶ ዝም፣

ከሆድ ያለ አይነቅዝም፡፡››

ይላል ያ’ገሬ ሰው፣

አንጀቱ እያረረ፣

ውስጥ ውስጡን ሲብሰው፡፡

እኔ አፍቃሪ ሆኜ አንቺ ተፈቃሪ፣

በትነሽ ልትዘሪኝ፣

አጭደሽ ልትከምሪኝ፣

ዘርጥጠሽ ልትወቂኝ፣

ሁሌም ስትሞክሪ፣

በጣለብኝ ዕዳ ሌላ ምን እላለሁ፣

ሁሉን ስታደርጊኝ ቻል አደርገዋለሁ!!

ይልቅ ከዚህ ሁሉ፣

ምነው ባደረግሽኝ ብናኙን አቧራ፣

ነፋስ ተሸክሞኝ ካ’ይንሽ እንድገባ፣

ባ’ይንሽ እንድሞላ፡፡

መዝገበቃል አየለ ገላጋይ ‹‹ዶፍ አዘል ደመና›› (2013)

 

* * *

 

ተረቶች የሚጀምሩት እንዴት?

‹‹አባዬ!›› አለች ሕፃኗ ልጅ፤ ‹‹ሁሉም ተረቶች የሚጀምሩት ‹ከዕለታት አንድ ቀን› በማለት ነው እንዴ?››

‹‹ኧረ አይደለም የኔ ቆንጆ፤ አንዳንዶቹ ‹እኔን ብትመርጡኝ› በማለት ነው የሚጀምሩት፡፡››

* * *

ሁሌም የምትቀድመዋ ሴት

አዛውንቱ ሰውዬ ወደ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ ባለቤታቸው ድምጿን ሰጥታ እንደሆን ጠየቁ፡፡

የምርጫ ጣቢያው ኃላፊም ቀድማቸው መምረጧን ከገለጹላቸው በኋላ ለማንኛውም ላረጋግጥ በማለት ሙሉ ስሟንና አድራሻዋን ጠይቆ አጣራ፡፡ በእርግጥም ድምፅ ሰጥታለች፡፡

አዛውንቱ በዚህ ክፉኛ ተበሳጨ፡፡ ‹‹እንዴት ዓይነት አበሳ ነው፤ እባካችሁ? ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየች ይኸው ስምንት ዓመት አለፋት፡፡ ሆኖም በየምርጫው ድምጿን ቀድማኝ ትሰጣለች፡፡ ዛሬ እንኳን ላገኛት እችላለሁ በሚል ተስፋ ነበር የመጣሁት፡፡››

መሪ እና ተመሪ

ዶናልድ ትራምፕ እንደተመረጠ ስብስባ ጠራ፡፡ በስብሰባው ላይ የስለላ ድርጅቶቹ ኤፍቢአይ፣ ሲአይኤና የመከላከያው ዲአይኤ ኃላፊዎች ሪፖርቶቻቸውን አቅርበው እንደጨረሱ ፕሬዚዳንቱ፣ ‹‹ጽንፈኛው አይኤስን ማጥፋት አለብን›› አለ፡፡

ሲአይኤ፡- ‹‹ይህን ማድረግ አንችልም፡፡ ከቱርክ፣ ከሳዑዲ፣ ከኳታርና ሌሎችም ጋር በመሆን የፈጠርናቸው ናቸው፡፡››

ትራምፕ፡- ‹‹ዴሞክራቶች ናቸው የፈጠሯቸው!››

ሲአይኤ፡- ‹‹ዴሞክራቶች አይደሉም የፈጠሯቸው፣ ጌታዬ፡፡

አይኤስን የፈጠርነት እኛ ነን፣ ያስፈልጉናል፡፡ እነሱ ከሌሉ ከነዳጅ ኩባንያዎቻችን የምታገኘውን የገንዘብ መዋጮች ታጣለህ፡፡››

ትራምፕ፡- ‹‹ለፓኪስታን የሚሰጠውን ድጋፍና ዕርዳታ አቋርጡ፡፡ ህንድ እንደምታደርግ ታድርጋቸው፡፡››

ሲአይኤ፡- ‹‹ጌታዬ፣ ይህንም ማድረግ አንችልም፡፡ ብሔርተኛው ሞዲ ነው’ኮ የዚያች አገር መሪ፤ ለዘብተኛው ማንሞሃ አይደለም፡፡››

ትራምፕ፡- ‹‹ቢሆንስ ታዲያ?››

ሲአይኤ፡- ‹‹ሞዲ የፓኪስታን ግዛት የሆነችውን ባሉቺሰታን ግዛት ወርሮ ይይዛል፡፡››

ትራምፕ፡- ‹‹ምን ጨነቀኝ!››

ሲአይኤ፡- ‹‹የህንድ ካሽሚር ግዛት ውስጥ ሰላም ስለሚሰፍን የጦር መሣሪያ መግዛት ያቆማሉ፡፡ ከዚያም ኃያል አገር ይሆናሉ፡፡ ጌታዬ፣ ህንድ በካሽሚር ጉዳይ ተጠምዳ እንድትቆይ ፓኪስታንን በገንዘብና በሌላም መደገፍ አለብን፡፡››

ትራምፕ፡- ‹‹ታሊባንን ማጥፋት አለባችሁ፡፡››

ሲአይኤ፡- ‹‹ጌታዬ፣ ይህንንም ማድረግ አንችልም፡፡ ሩሲያን በ1980ዎቹ አስረን ለማቆየት የፈጠርነው ነው፡፡ አሁን ደግሞ ፓኪስታንን ስለ ኒዩክሌር ኃይሏ ሳይሆን ስለእነሱ በማሰብ እንድትጠመድ አድርጎልናል፡፡››

ትራምፕ፡- ‹‹የእስልምና መንግሥታትን ማጥፋት ይኖርብናል፡፡ በሳዑዲ ዓረቢያ መጀመር እንችላን፡፡››

ሲአይኤ፡- ‹‹ጌታዬ፣ ይህንንም ማድረግ አንችልም፡፡ ነዳጃቸውን ስለምንፈልግ እኛው የፈጠርናቸው መንግሥታት ናቸው፡፡ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ካደረግን ሕዝባቸው ነዳጁን በእጁ ያስገባል፡፡ ስለዚህ በእነሱ እጅ እንዲገባ አንፈቅድም፡፡››

ትራምፕ፡- ‹‹እንግዲያው ኢራንን እንውረራት፡፡››

ሲአይኤ፡- ‹‹አይቻልም፣ ጌታዬ!››

ትራምፕ፡- ‹‹ለምን?››

ሲአይኤ፡- ‹‹በውይይት ላይ ነው የምንገኘው፣ ጌታዬ፡፡››

ትራምፕ፡- ‹‹ምን? ስለምንድነው የምትወያዩት?››

ሲአይኤ፡- ‹‹አንዳንድ እጃቸው የገቡ መሣሪያዎችን ማስመለስ እንፈልጋለን፡፡ ከዚያም በላይ ግን እስራኤልን ለመቆጣጠር ኢራን ታስፈልገናለች፡፡››

ትራምፕ፡- ‹‹እንዲያ ከሆነ ኢራቅን እንደገና እንውረራት፡፡››

ሲአይኤ፡- ‹‹ጌታዬ፣ አይኤን እንዲቆጣጠርልን በኢራቅ የሚገኘውን የሺአ መንግሥት እንፈልገዋለን፡፡››

ትራምፕ፡- ‹‹ሙስሊሞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እያገድኩ ነው፡፡››

ሲአይኤ፡- ‹‹ያን ማድረግ አያዋጣንም፣ ጌታዬ!››

ትራምፕ፡- ‹‹በአገራችን የሚኖሩ ሕገወጥ ስደተኞች በሙሉ እንዲባረሩ አደርጋለሁ፡፡››

ሲአይኤ ‹‹ይህንንም ማድረግ አትችልም፣ ጌታዬ!››

ትራምፕ፡- ‹‹ለምን?››

ሲአይኤ፡- ‹‹እነርሱ ከተባረሩ ድንበር ላይ የምንገነባውን ግንብ ማን ይገነባልናል?››

ትራምፕ፡- ‹‹ግንቡን አስቀድማችሁ ሥሩ፣ እናንተ ደናቁርት!››

ሲአይኤ፡- ‹‹እንደዚያ ካደረግንማ ግንቡ ውስጥ ወይም አሜሪካ ስለሚሆኑ አሜሪካ የመቆየት መብት ይኖራቸዋል!››

ትራምፕ፡- ‹‹ከሌሎች አገሮች በፈቃድ መጥተው የሚሠሩትን ‹ኤች-ቢ ኤስ› ያላቸውን በማገድ እቀጣቸዋለሁ!››

ሲአይኤ ‹‹አትችልም፣ ጌታዬ፡፡››

ቺፍ ኦቭስታፍ፡- ‹‹ያን ካደረግን፣ ዋይት ሐውስን ለህንድ ባለሙያዎች ኮንትራት መስጠት ይኖርብናል፡፡ ምክንያቱም አሁን በዚህ ያሉት ብዙዎች ሠራተኞች የዚያ አገር ሰዎች ናቸው፡፡››

ትራምፕ፡- ‹‹ምን ዓይነት ውጥንቅጥ ውስጥ ነው የገባሁት? ነገሩ እንዲህ ከሆነ ለምን  ተመረጥኩ?››

ሲአይኤ፡- ‹‹በዋይት ሐውስ እንድትዝናና ነዋ፣ ጌታዬ! እኛ እኩይ ሰዎችን እንፈጥራለን፤ አንተ ታፀድቅልናለህ፡፡ ከዚያም ስንፈራረም ከምድረ ገጽ እንዳጠፋሃቸው ትገልጻለህ፣ ጌታዬ!››

ትራምፕ፡- ‹‹ፈጣሪ የነፃነትና የጀግኖች ምድር የሆነችው አሜሪካን ይባርክ!!!››

* * *

አገሪቱን ከፓርቲ የምናስቀድምበት ጊዜ ነው፤ ቀጣዩን ትውልድ ደግሞ ቀጣዩ ምርጫ፡፡

  • ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ (የአሜሪካው)
  • አረፈ ዓይኔ ሐጐስ ‹‹ፖለቲከኞች እፈሩ›› [2013]
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች