Friday, June 9, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከ1.12 ቢሊዮን ብር በላይ በማትረፍ የመጀመርያው የኢንሹራንስ ኩባንያ ሆነ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች 13.8 ቢሊዮን ብር የዓረቦን ገቢ አገኙ 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ፣ በአንድ ኩባንያ ከ1.12 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዘገበ፡፡

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዓርብ ነሐሴ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. የ2013 የሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን ይፋ ባደረገበት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔው ላይ እንደተገለጸው ከታክስ በፊት የተገለጸውን መጠን ትርፍ አግኝቷል፡፡

በዓመታዊ ጉባዔው ላይ እንደተገለጸው፣ በ2013 ዓ.ም. ያስመዘገበው ትርፍ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 13.5 በመቶ ብልጫ አለው፡፡  

በኢትዮጵያ ፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔ በይበልጥ ጎልቶ የሚታየው በባንኮች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሥራ ላይ ካሉ ባንኮች ከአንድ ቢሊዮን እስከ 20 ቢሊዮን ብር የሚደርስ ትርፍ እያስመዘገቡ ያሉ ባንኮች ቁጥር ከአሥር በላይ ደርሷል፡፡

በ2013 ዓ.ም. የባንኮች መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከታክስ በፊት 20 ቢሊዮን ብር ያተረፈ ሲሆን፣ ከግል ባንኮች ደግሞ አዋሽ ባንክ 5.56 ቢሊዮን ብር ማትረፉን መግለጹ አይዘነጋም፡፡ እንደ ባንኮቹ ሁሉ የኢንሹራስ ኩባንያዎች በቢሊዮን የሚቆጠር ዓመታዊ ትርፍ ምጣኔ ያስመዘገቡበት ወቅት ባይኖርም፣ ዘንድሮ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በማትረፍ ቀዳሚ መሆን ችሏል፡፡

በኢንሹራንስ ዘርፍ ግን ከ19 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔ በአማካይ 250 ሚሊዮን ብር አካባቢ ነው፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ ትልቁ የኢንሹራንስ ኩባንያ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ከ1.12 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረስ ከቻለባቸው ምክንያቶች ውስጥ፣ በ2013 የሒሳብ ዓመት ከፍተኛ የተባለውን 6.1 ቢሊዮን ብር ዓረቦን ገቢ ማሰባሰብ መቻሉና እከፍላለሁ ብሎ ካቀደው የጉዳት ካሳ በእጅጉ ያነሰ ክፍያ መፈጸሙ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡  

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በ2013 የሒሳብ ዓመት በአጠቃላይ የተመዘገበው የዓረቦን መጠን 13.8 ቢሊዮን ብር መድረሱ ታውቋል፡፡ በ2013 የሒሳብ ዓመት 19 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሰበሰቡት 13.8 ቢሊዮን ብር የዓረቦን መጠን፣ ከ2012 የሒሳብ ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ24.7 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ በሒሳብ ዓመቱ ውስጥ ከተሰበሰበው ውስጥ የጠቅላላ መድን ዓረቦን የ22.1 በመቶ፣ እንዲሁም የሕይወት ኢንሹራንስ የ65.6 በመቶ ብልጫ የታየበት ነው፡፡ በተለይ የሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ ዕድገት የታየበት ዓመት ስለመሆኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡  

በ2013 የሒሳብ ዓመት ከሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ የተሰበሰበው የዓረቦን መጠን 858.8 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ ሕይወት ነክ ካልሆነው ጠቅላላ ኢንሹራንስ ዘርፍ የተሰበሰበው የዓረቦን መጠን 12.96 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ በሒሳብ ዓመቱ 19 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የጉዳት ካሳ ምጣኔያቸው ደግሞ 57.3 በመቶ ሲሆን፣ ይህም ከአምናው መጠነኛ ቅናሽ የታየበት እንደሆነ መረጃው ያሳያል፡፡   

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች