Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየፓራሊምፒክ አትሌቲክስ ቡድን ሽልማት ይጠብቀዋል

የፓራሊምፒክ አትሌቲክስ ቡድን ሽልማት ይጠብቀዋል

ቀን:

ኢትዮጵያ በቶኪዮ 2020 ፓራሊምፒክ ጨዋታ ተሳትፎዋ በትዕግስት ገዛኸኝ አማካይነት የወርቅ ሜዳሊያን በማግኘት አዲስ የፓራአትሌቲክስ ታሪክ ምዕራፍ ተከፍቷል፡፡ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የፓራአትሌቲክስ የነገሠችው በ1,500 ሜትር በጭላንጭል በሚያዩ አትሌቶች መካከል በተደረገ ውድድር ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከትዕግስት ባሻገር፣ በተመሳሳይ 1,500 ሜትር ርቀት በእጅ ጉዳት በገመቹ አመኑና በጭላንጭል የሚያዩ ወንዶች ታምሩ ደምሴ ተወክላ ነበር፡፡

በዚህም በሪዮ ፓራሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚው ታምሩ፣ በ1,500 ሜትር ወንዶች ፍጻሜ ሰባተኛ ሆኖ በመፈጸም፣ እንዲሁም ሌላኛው ተወዳዳሪ ገመቹ አመኑ አምስተኛ ደረጃ በመያዝ ዲፕሎማ አግኝተዋል፡፡

- Advertisement -

ሦስት አትሌቶች በመያዝ ወደ ቶኪዮ ያመራው የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ አትሌቶች ቡድን ቅዳሜ ነሐሴ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. በቦሌ ኤርፖርት አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይና የስፖርት ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር አቀባበል አድርገውለታል፡፡

ከዚህም ባሻገር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ ትዕግስት በትውልድ ቦታዋ ደብረ ብርሃን ከተማ ስትደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል፡፡ በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱም የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪና የተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቶኪዮ 2020 ፓራሊምፒክ ጨዋታ ተሳትፎዋ በትዕግስት ገዛኸኝ አማካይነት የወርቅ ሜዳሊያን በማግኘት አዲስ የፓራአትሌቲክስ ታሪክ ምዕራፍ ተከፍቷል፡፡ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የፓራአትሌቲክስ የነገሠችው በ1,500 ሜትር በጭላንጭል በሚያዩ አትሌቶች መካከል በተደረገ ውድድር ነው፡፡

ትዕግስት በአቀባበሉ ላይ በርካታ አካል ጉዳተኛ አትሌቶች ዕድሉን ቢያገኙ ውጤታማ እንደሚሆኑ የተገኘው ውጤት ማሳያ ነው ስትል አስታየቷን ሰንዝራለች፡፡

በቶኪዮ ፓራሊምፒክ አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ የቻለው ብሔራዊ ቡድኑ በቅርቡ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ይሸለማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ ሦስት አትሌቶችን በመያዝ አንድ የወርቅ ሜዳሊያና ሁለት ዲፕሎማ በማግኘት ከአፍሪካ ስድስተኛ እንዲሁም ከዓለም 59ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ኢትዮጵያ በፓራሊምፒኩ ከአፍሪካ ኬንያንና ግብፅን በልጣ፣ በሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ ደቡብ አፍሪካና ናይጀሪያ ተበልጣ አጠናቃለች፡፡

በፓራሊምፒክ ጨዋታ ለመካፈል በዓለም ሻምፒዮናዎች ላይ መካፈል የግድ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በፓራሊምፒክ ላይ መካፈል የሚችሉ በርካታ ስፖርተኞች ቢኖራትም፣ በፋይናንስና በአገር ውስጥ የውድድር እጥረት መኖሩን ተከትሎ አትሌቶቹን ቁጥር መጨመር እንዳልተቻለ የኢትዮጵያ ቶኪዮ 2020 ፓራሊምፒክ ቡድን ቴክኒካል ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ገብረማርያም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ አስተያየት ከሆነ፣ በቀጣዩ የፓሪስ ፓራሊምፒክ ላይ በርካታ አትሌቶችን ይዞ ለመካፈል የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ሻምፒዮናዎችን ማከናወንና በፋይናንስ ማጠናከር ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ሚኒማ ለሟሟላት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ሻምፒዮናዎች ላይ መካፈል አስፈላጊነት ቢኖረውም በዓለም ሻምፒዮናዎቹ ላይ ለመካፈል፣ ለእያንዳንዱ አትሌት ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ እንደሚጠይቅ አቶ ዮናስ ያስረዳሉ፡፡

ይኼን ችግር ለመፍታትም የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ በቋሚነት የገቢ ምንጭ መፍጠር እንዳለበትና መንግሥትም የበለጠ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው አቶ ዮናስ ያሳስባሉ፡፡ በቀጣይ አትሌቲክሱ ላይ ትኩረት አድርጎ ለመሥራት ማቀዱንና አንድ አትሌት በሁለት ርቀቶች ላይ እንዲሳተፍ እንደሚደረግም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡ ከአትሌቲክስ ባሻገር በወርልድ ቴኳንዶ ስፖርትም ተሳታፊ ሊኖረው እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...