Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየ2013 ዓ.ም. የኢትዮጵያ  ስፖርታዊ ክንውኖች

የ2013 ዓ.ም. የኢትዮጵያ  ስፖርታዊ ክንውኖች

ቀን:

ያለፈው 2013 .ም. በኢትዮጵያ በርካታ ስፖርታዊ ክንውኖች ተስተናግደዋል። ከነዚህም መካከል በዋና ዋናዎቹ ላይ ያደረግነው ዳሰሳ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ስኬታማ ጉዞ

2012 .ም.  በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦና ደብዝዞ የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ጨዋታ፣ 2013 . ስኬታማና ተስፋ የተዘራበት ሆኖ አልፏል።

- Advertisement -

ሆኖም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሪምየር ሊጉን ውድድር ለክለቦች አሳልፎ ከሰጠ በኋላ፣ በሼር ካምፓኒ መተዳደር  ጀምሯል። ሼር ካምፓኒውም ከመልቲ ቾይስ አፍሪካ አዲስ ውል ማሰሩ አዲስ ክስተት ነበር።  ይሄም ሊጉ ለመጀመርያ ጊዜ ውድድሩን በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት እንዲተላለፍ አስችሎታል።  ቀድሞ ክስና ውዝግብ የማያጣው ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ ምዕራፍ ብቅ ያለበት ዓመት ስለነበር ለክለቦችና ለተጫዋቾች አዲስ የዕድል በር የከፈተ አጋጣሚ ሆኗል፡፡

ስድስት ከተሞች ላይ እየተዘዋወረ ሲከናወን የከረመው፣ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በርካታ ጨዋታዎች የቀጥታ ሥርጭትማግኘታቸው
ባሻገር በሊጉ ሲካፈሉ የነበሩ 13 ክለቦች 163 ሚሊዮን ብር ከቴሌቪዥን  መብት ክፍያ ማግኘት ችለዋል። ይሄም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ የመጀመርያ ያደርገዋል።
ሊጉም በተያዘለት መርሐ ግብር ያለ ተመልካች ተከናውኖ፣ ፋሲል ከነማ  የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል። ፋሲል ለመጀመርያ ጊዜም በአጠቃላይ 10,346,877 ብር ወደ ካዝናው ከቷል።

ከዚህም  ባሻገር በውድድሩ ድንቅ ብቃታቸውን ማሳየት የቻሉ ተጫዋቾችና አሠልጣኞች የተለያዩ ሽልማት ተበርክቶላችዋል።

የኢትዮጵያ  ብሔራዊ ቡድን  ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈበት ዓመት

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ሌላኛው ስኬታማ ጉዞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተስፋ ሰጪ ውጤት ተጠቃሽ ነው። በኮቪድ-19 ምክንያት ለሰባት ወራት ተበትኖ የቆየው ቡድንን ለካሜሮን አፍሪካ ዋንጫ ማሰናዳት ግድ ይል ነበር። ከአይቮሪኮስት፣ ማዳጋስካርና ኒጀር ጋር የተደለደለው ዋሊያው፣ በባህር ዳር ስታዲየም ላይ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በድል በማጠናቀቅ፣ ከስምንት ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ያለፈበት ዓመት ነበር።  መስከረም 2013 .ም. አሠልጣኙ አብርሃም መብራቱን አሰናብቶ፣ ውበቱ አባተን የቀጠረው የኢትዮጵያ እግር ኮስ ፌዴሬሽን በተጣበበ ጊዜም ቢሆን ጠንካራ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።

በተለይ ከዚህ ቀደም ባልነበረ የዝግጅት ባህል፣ በተለያዩ ስታዲየሞች ከመዘጋጀቱም በላይ የተለያዩ አገሮችን በመጋበዝ የወዳጅነት ጨዋታ ማድረጉ ብሔራዊ ቡድኑን ጠንክሮ እንዲዘጋጅ አስችሎታል። 

ዋሊያዎቹ በካሜሮንጥር ወር ላይ በሚከናወነው የአፍሪካ ዋንጫ፣ ከካሜሮን፣ ከቡርኪናፋሶውና ኬፕ ቨርዴ ጋር ተደልድለዋል።  ለዚህም ውድድር  ጠንካራ ዝግጀት እያደረገ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር 2022 የኳታር ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከጋና፣ደቡብ አፍሪካና ዚምባቡዌ ጋር ተደልድሎ የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ ይገኛል።

የዋሊያዎቹ ስብስብ፣ በአዳዲስ ተጫዋቾች እየዳበረ፣ በየጨዋታውም መሻሻልን እያሳየ ይገኛል።  በዚህም መሠረት በአፍሪካ ዋንጫ እንዲሁም በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ  ተስፋ ሰጪ ብሔራዊ ቡድን ይታያል ተብሎ ይጠበቃል።

ቶኪዮ ኦሊምፒክና አትሌቲክስ

 ለሁሉም ስፖርታዊ ክንውኖች እንቅፋት ሆኖ የቆየው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አትሌቲክሱም ላይ የራሱን ጥላ አጥልቶ ማለፉ አልቀረም። ምንም እንኳን አትሌቲክስ የግል ስፖርት ቢሆንም፣ አትሌቶች ያለምንም ውድድር ለረዥም ጊዜ ሥልጠና ለማድረግ ተገደዋል። በተለይ ደግሞ በርካታ ዓለም አቀፍ ውድድሮች መሰረዛቸውን ተከትሎ፣ ለበርካታ ወራት ልምምድ ለማድረግ ለተገደዱት አትሌቶች አሰልቺ ነበር።

ሆኖምኢትዮጵያ መገለጫ ከሆኑት ስፖርቶች ውስጥ አንዱ የሆነው አትሌቲክስ 2013 .ም. መልካም ዓመት ነበር ብሎ በምልዓት ደፍሮ ለመናገር አያስችልም።
ከአትሌቶች እንቅስቃሴ ባሸገር  ዓመቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ደራርቱ ቱሉን፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አሸብር ወልደጊዮርጊስን (/) እንዲመሩ የተመረጡበት ዓመት ነበር። ይሄም  በኮቪድ-19  ምክንያት ለአንድ ዓመት ተራዝሞ ለነበረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ  መሰናዶ ዋዜማ ላይ መደረጉ ትኩረትን የሳበ ጉዳይ ነበር።
የሁለቱም ተቋማት ትኩረት ቶኪዮ ኦሊምፒክ ነበር። በዚህም መሠረት በኦሊምፒክ ኮሚቴ ድጋፍ አትሌቶቹ ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በተለያዩ  ርቀቶች ላይ የሚካፈሉ 100 በላይ አትሌቶችም ተመርጠው ዝግጅት ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ የመጨረሻዎቹ 35 አትሌቶች ሆቴል ሆነው ዝግጅታቸውን ሲያደርጉ ነበር። በዝግጅቱ ወቅትም በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን  ኦሊምፒክ ኮሚቴ መካከል የነበረው አለመግባባት የበርካቶችን ትኩረት የገዛ አጋጣሚ ነበር። የውዝግቡ አንኳር ምክንያት ይሄ ነው ብሎ መናገር ባይቻልም፣ የአትሌቶች ምርጫና የቶኪዮ የጉዞ ሒደት አንደኛው ነበር።

የኢትዮጵያ  የቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳትፎዋ

ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በአትሌቲክስ፣ በወርልድ ቴኳንዶ፣ በዋናና ብስክሌት  መካፈል ችላለች። ከስምንት ወራት በላይ ዝግጀት ሲያድርግ የቆየው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን 35 አትሌቶችን ይዞ ተጉዟል። ከአትሌቶች ምርጫና የጉዞ ሒደት ጋር በተያያዘ ውዝግብ ሲያስተናግድ የነበረው  ቡድኑ አንድ ወርቅ፣ አንድ ብርና ሁለት የነሐስ በድምሩ አራት ሜዳሊያዎች ይዞ ተመልሷል። ውጤቱ ኢትዮጵያ ከሦስት አሠርታት ወዲህ ከተሳተፈችባቸው ኦሊምፒኮች አንፃር ዝቅተኛ ሆኖ ተመዝግቧል። ለዚህም በሁለቱ ተቋማት መካከል የነበረው አለመግባባት መንስዔ እንደሆነ ተገልጿል። ኦሊምፒክ ኮሚቴም ይቅርታ የጠየቀበት  ኦሊምፒክ  ሆኖ አልፏል። በአንፃሩ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታ የተካፈሉ አትሌቶችና አሠልጣኞች ዳጎስ ያለ ገንዘብ ተበርክቶላቸዋል።

ኢትዮጵያ ከአትሌቲክስ ባሻገር ለመጀመርያ ጊዜ በቴኳንዶ ስፖርት ተወክላ ዲፕሎማ በሰሎሞን  አማካይነት አግኝታለች። ከዚህም ባሻገር በብስክሌት በሰላም አምሃ እንዲሁም በዋና መካፈል ባትችልም በሊና ተወክላ ነበር።

ከኦሊምፒክ ባሻገር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ዓለም አቀፍ የግል ውድድሮች ላይ መድመቅ የቻሉበት ዓመት ነበር። ለተሰንበት ግደይ 10,000 ሜትር በ5,000 ሜትር የዓለም ክብረወሰን መስበር የቻለችበት ዓመት ነበር።

ሌላው የዓመቱ ድንቅ ክስተት ኢትዮጵያ በፓራሊምፒክ ታሪክ የመጀመርያውን ወርቅ በትዕግሥት ገዛኸኝ ያገኘችበት ዓመት ነበር፡፡ በቶኪዮ 2020 ፓራሊምፒክ ጨዋታዎች የአፍሪካ ሻምፒዮኗ ትዕግሥት፣ ቅዳሜ ነሐሴ 22 ቀን 2013 .. በተካሄደው በጭላንጭል የሚያዩ 1,500 ሩጫ፣ የራሷን ምርጥ ሰዓት 4:23.24 በማስመዝገብ  ነው ለፓራሊምፒክ አሸናፊነት የበቃችው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...