Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትተተኪ ተጫዋቾችን ለማፍራት ግቡ ያደረገው የሐዋሳ የሴንትራል ዋንጫ ጨዋታ

ተተኪ ተጫዋቾችን ለማፍራት ግቡ ያደረገው የሐዋሳ የሴንትራል ዋንጫ ጨዋታ

ቀን:

በኢትዮጵያ የፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፉ ክለቦች በሊጉ ልምድ አላቸው ለተባሉ፣ ዕድሜያቸው ለገፋ ተጫዋቾች፣ እንዲሁም ከተለያዩ አፍሪካ አገሮች ለሚፈልሱ ተጫዋቾች ረብጣ ብሮችን አፍስሰው መሸመት ከተለመደ ሰነባብቷል።  ለአንድ የውድድር ዘመን በሚሊዮኖች ብር የሚመድቡት ክለቦቹ፣ ታዳጊዎችን እየመለመሉ ቡድናቸውን ከማጠናከር ይልቅ፣ በዝውውር ገበያው ላይ የሚያወጡት ገንዘብ ከፍተኛ ነው። በዚህም ምክንያት ተተኪዎችን ማፍራት አለመቻላቸው ብሔራዊ ቡድኑ ለተጫዋቾች ዕጥረት ሲዳረግና ውጤቱም ሲያሽቆለቁል ይስተዋላል። ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ በክለቦች እንዲሁም በብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂና አጥቂ ማግኘት አዳጋች ሆኖ ዘልቋል።

የውድድር ዕጥረት፣ የማዘውተሪያ ሥፍራ ማጣትና የባለሀብቶች ወደ እግር ኳሱ ቀርበው ያለመሥራት እንደ ዋነኛ ችግር ተደርጎ ሲነሳ ይስተዋላል። በአንፃሩ ጥቂት ክለቦች እንዲሁም በተለያዩ ፕሮጀክቶችና ባለሀብቶች በተተኪዎች ላይ ሲሠሩ ይስተዋላል።

tender

በየዓመቱ ተተኪ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ለማፍራት በሚከናወነው የሴንትራል ሐዋሳ ታዳጊዎች ዋንጫ ውድድር ላይ በከተማዋ የሚገኙ 37 ክለቦች ተካፋይ ሆነዋል።
ከነሐሴ
እስከ ጳጉሜን 2 ቀን 2013 ዓ.ም. በሐዋሳ ቄራ  ተብሎ በሚጠራው ሜዳው በሰነበተው  በዚህ ውድድር ላይ  ዕድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ 15 ክለቦች፣  እንዲሁም ከ15 ዓመት በታች የሆኑ 22 ክለቦች ተሳትፈውበታል።

በፀጥታና ኮቪድ-19  ምክንያት ለሁለት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው 12ኛው የሴንትራል ካፕ የታዳጊዎች እግር ኳስ ውድድር ላይ የታዳጊ ብሔራዊ ቡድን የቴክኒክ ኮሚቴ ኃላፊ ኢንስትራክተር ተመስገን  ዳና እና  የተለያዩ የክለብ መልማዮች ተገኝተዋል። ውድድሩን በቴክኒክ ኮሚቴ ኃላፊነት የመሩት ኢንስትራክተር ተመስገን ዳና ናቸው፡፡

ውድድሩ በሐዋሳ ከተማ ሴንትራል ሐዋሳ ሆቴል ባለቤት ወ/ሮ አማረች ዘለቀ መሥራችነት ስፖንሰር አድራጊነት ላለፉት 12 ዓመታት ሲካሄድ የቆየ የታዳጊዎች የእግር ኳስ ውድድር  እንደሆነ  የውድድሩ ኮሚቴ ሰብሳቢና የሐዋሳ ሴንትራል ሆቴል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፍትሕ ወልደሰንበት (ዶ/ር) ለሪፖርተር አስረድተዋል።

‹‹ውድድሩ በዋናነት ዓላማ ያደረገው ታዳጊ ወጣቶች የዕረፍት ጊዜያቸውን በአልባሌ ቦታ እንዳያውሉ፣ በስፖርትና በአዕምሮ ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት፣ ለከተማው፣ ለክልሉ እንዲሁም ለአገሪቷ  ተተኪ ተጫዋቾችን ለማፍራት ግቡ ያደረገ ነው፤›› ሲሉ ፍትሕ (ዶ/ር) አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል። በዚህም ውድድር በከተማው የሚገኙ የንግዱ ማኅበረሰብና ስፖርት ወዳድ አካላት ታዳጊዎችን ስፖንሰር በማድረግ ውድድሩን  በክለብ በማሳተፍ የበኩላቸውን አስተዋጽâ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ይህ ዓመታዊ ውድድር ከተጀመረ ጀምሮ ብዙ ዕውቅ ተጫዋቾችን ለክለቦችና ለብሔራዊ ቡድን በማፍራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በዘንድሮውም ውድድር በቅርቡ የታዳጊዎች ስፖርት አካዴሚ በመክፈት ላይ የሚገኙት የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ሽመልስ በቀለና አዳነ ግርማ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ  ተጫዋቾችን ሲመለምሉ መቆየታቸው ተጠቅሷል።

በውድድሩ ከ13 ዓመት በታች ለሁሉም እግር ኳስ ቡድን እና ከ15 ዓመት በታች አልኒየም እግር ኳስ ቡድን በአሸናፊነት ያጠናቀቁ ሲሆን፣ ዋንጫና የተለያዩ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

tender

ለአንድ ወር በቆየው በዚህ ውድድር ላይ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል የስፖርት ኮሚሽነሮች የተገኙ ሲሆን፣ የሐዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ (ረዳት ፕሮፌሰር) የቄራ ሜዳው ወሰን ተከብሮ ምቹ የውድድርና የማሠልጠኛ ቦታ እንዲሆን ግንባታ ይደረግለታል ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ለ12 ዓመታት ሲከናወን የቆየው የሴንትራል ሐዋሳ ታዳጊዎች እግር ኳስ  ጨዋታ ካፈራቸው ተጫዋቾች ውስጥ ከ23 ዓመት ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች መካከል መስፍን ታፈሰ፣ ብሩክ በየነና  ወንድምአገኝ ኃይሉ ይጠቀሳሉ።

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...