Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበተለያዩ ዓለም አቀፍ የሩጫ ውድድር የደመቁት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሩጫ ውድድር የደመቁት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

ቀን:

የቶኪዮ ኦሊምፒክ መጠናቀቅን ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ፊታቸውን ወደ ግል ውድድሮች አዙረዋል።

በኦሊምፒክ ጨዋታው ድል ያልቀናቸው አትሌቶች በመጠኑም ቢሆን በተሳተፉበት የግል ውድድር ደምቀው አልፈዋል። በሳምንቱ መጨረሻ በጀርመን በአዲዳስ ትጥቅ አቅራቢነት በአምስት ኪሎ ሜትር፣ አሥር ኪሎ ሜትርና ግማሽ ማራቶን የጎዳና ላይ ሩጫ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተካፍለዋል።

መስከረም 2 ቀን 2014 ዓ.ም. በአምስት ኬሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ውድድር ላይ የተካፈለችው ሰንበሬ ተፈሪ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግባለች። ሰንበሬ ርቀቱን  በ14:29 በሆነ ጊዜ በመፈጸም አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ ችላለች።

አትሌቷ የነበረውን 14:32  የነበረውን ሰዓት ነበር አሻሽላ ክብረ ወሰን መጨበጥ የቻለችው።  እሷን ተከትላ በኬንያ የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና ላይ በ3ሺሕ እና 5ሺሕ ሜትር  ሁለት  ሜዳሊያ ማግኘት የቻለችው መልክናት ውዱ 14:54 በሆነ ጊዜ ሁለተኛ እንዲሁም ንግሥቲ ሀፍቱ 14:54 በሆነ ጊዜ ሦስተኛ በመውጣት በበላይነት አጠናቀዋል። በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ለብሔራዊ ቡድን እንዲሁም በግል ውድድሮች ላይ ልምድ ያላት ሰንበሬ በቶኪዮ ኦሊምፒክ 5ሺሕ ሜትር ስድስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።

ከሰንበሬ ድል ባሻገር፣ በኬንያው የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና 3000 ሜትር እና በ5000 ሜትር ሁለት ሜዳሊያ ማግኘት የቻለው ታደሰ ወርቁ በአሥር ኪሜ የጎዳና ውድድር በኃይሌ ገብረ ሥላሴ እ.ኤ.አ. በ2002 ተይዞ የነበረውን 27:02 ብሔራዊ ክብረ ወሰን 26:56 በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ የኢትዮጵያ ክብረ ወሰን አሻሽሏል። ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሙክታር እድሪስ በአምስት ኪሜ የጎዳና ላይ ውድድር በደጄኔ ብርሃኑ እ.ኤ.አ. በ2005  የተያዘውን 13:10 ብሔራዊ ክብረ ወሰን፣ 13:09  በመግባት የርቀቱን ሰዓት አሻሽሏል።

በሌላ በኩል በዕንቁጣጣሽ ከተከናወኑ የሩጫ ውድድሮች መካከል በኦስትርያ 
ቬና የተደረገ ሌላኛው የማራቶን ውድድር ነበር።  በዚህም ውድድር በወንዶች
በተስፋ ጌታሁን በ2:09:42 ሰዓት ሁለተኛ፣ እንዲሁም በዚሁ ውድድር ላይ ተሳትፎ በአንደኝነት አጠናቆ የነበረው ደራራ ደሳለኝ ባልተፈቀደ ጫማ በመሮጡ ያገኘው ደረጃና ውጤት ተሰርዞበታል፡፡ ለውጤቱ ምክንያት የሆነው  የጫማው የሶል ውፍረት ከሚፈቀደው በላይ  በመሆኑ እንደሆነ ተዘግቧል።

ደራራ ደሳለኝ

በሴቶች  መሠረት ድንቄ በ2:25:31 ሰዓት ሁለተኛ እንዲሁም  ገለቴ ቡርቃ በ2:25:38 ጊዜ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በጀርመን ሃምቡርግ ማራቶን ተካፍለው ነበር። በርቀቱም በወንዶች ማስረሻ ቢሰጠኝ በ2:10:55 ሁለተኛ፣ በላይ በዛብህ በ2:14:01 ሰዓት ሦስተኛ እንዲሁም  ደረሰ ካሴ በ2:17:38 ጊዜ በመግባት አምስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡ በሴቶች  ጋዲሴ ሙሉ በ2:26:19 ሰዓት በአንደኝነት አጠናቃለች።

በቶኪዮ ኦሊምፒክ የደበዘዘው የአትሌቶች ውጤት፣ በግል ውድድሮች ላይ የተሻለ ሆኖ ሲመዘገብ መመልከት ከተጀመረ ሰነባብቷል።  ወጤቱ አገርን ወክለውና በግል ውድድር ያደረጉትን ውድድር ለተመለከተ በአትሌቲክሱ አንዳች ችግር እንዳለ የሚያሳይ ነው። በዚህም መሠረት አትሌቶች፣ አሠልጣኞች እንዲሁም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ችግሩን ለመፍታት በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ፍንጭ የሚሰጥ ነው የሚል አስተያየት እየተሰማ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...