Sunday, June 23, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ ከውጭ ግንኙነት አማካሪያቸው ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ እየተነጋገሩ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር የውጭ አጋሮቻችን ደጋግመው ማብራሪያ እንድንሰጣቸው እየጠየቁ ነው፡፡ 
 • በምን ጉዳይ ላይ ነው ማብራሪያ የሚጠይቁት?
 • አዲስ መንግሥት ከተመሠረተ በኋላ የሚጀመረው የፖለቲካ ድርድር ሁሉን አሳታፊ እንደሚሆን ማረጋገጥ ፈልገው ነው ማብራሪያ እየጠየቁ ያሉት።
 • ሁሉን አሳታፊ እንደሚሆን አትገልጽላቸውም እንዴ ታዲያ?
 • ለማስረዳት ሞክሬያለሁ ነገር ግን
 • ነገር ግን ምን?
 • ሕወሓት በውይይቱ ተሳታፊ ይሆናል የሚለውን በቀጥታ ማረጋገጥ ፈልገዋል።
 • ምን አልካቸው?
 • ስም አልጠራም አልኳቸው።
 • ስም አልጠራም?
 • አዎ፣ ነገር ግን ሁሉን አሳታፊ ውይይት እንደሚካሄድ አሳውቄያቸዋለሁ።
 • ለምን ግልጹን አልነገርካቸውም?
 • ምን ብዬ? 
 • ማን እንደሚደራደር እነሱም አያውቁትም ብለህ፡፡
 • እንዴት አያውቁትም ብለው ቢጠይቁኝስ? 
 • አንድነት የፈጠሩት ለውጊያው እንጂ ለድርድር አይደለም በላቸው። 
 • እንደዚያ ነው እንዴ? 
 • የውስጥ ሽኩቻ ላይ መሆናቸውን አታውቅም እንዴ?
 • አልሰማሁም? በምን ምክንያት?
 • በሥልጣን ነዋ?
 • የምን ሥልጣን?
 • ከድርድር በኋላ በሚጠብቁት ሥልጣን።
 • እና እንዴት ነው ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት የምንጀምረው?
 • እስኪጀመር አንዱ ያሸንፋል፣ ካልሆ ደግሞ…
 • ካልሆነ ምን?
 • እኛ ያቋቋምነው ጊዜያዊ አስተዳደር ወክሎ ይደራደራል። 
 • ትክክል፣ ዋናው አሳታፊ ወይይት መሆኑ ነው።

[ክቡር ሚኒስትሩ ድካም ተጫጭኗቸው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው የቴሌቪዥኑን ዜና እየተመለከቱ በመገረም አንገታቸውን ሲወዘውዙ አገኟቸው] 

 • ምን የሚያስገርም ነገር አገኘሽ?
 • አትሰማም እንዴ ሚኒስትር ባልደረባህ የሚሉትን?
 • ምን አለ?
 • በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የመንግሥት መዋቅር በመጪው መስከረም ይዋቀራል እያሉ ነው።
 • እሱማ እውነት ነው። 
 • እውነት ነው አልክ?
 • አዎ፣ በታሪክ ያልነበረ የመንግሥት መዋቅር ነው ከጥቂት ሳምንት በኋላ የሚመሠረተው። 
 • ታዲያ እናንተ እንዴት ልትሆኑ ነው?
 • እኛ ምን እንሆናለን?
 • አሃ… እናንተ ትቀጥላላችሁ እዚህ መዋቅር ውስጥ?
 • እንዴት አንቀጥልም? ምነው ሠጋሽ እንዴ?
 • እናንተ ከቀጠላችሁ ምኑ ነው ታዲያ ታሪካዊ የሚሆነው?
 • የመንግሥት መዋቅሩ ነዋ፣ አደረጃጃቱ… 
 • ታሪካዊ የተባለው እሱ ነው?
 • አዎ፣ አደረጃጀቱን ማለታችን ነው።
 • ልትደራጅብን ነዋ!
 • ምን አልሽ?
 • አድምጥ… አድምጥ… 
 • ምንድነው?
 • አለቃህ ሌላ ታሪካዊ ነገር እያሉ ነው።
 • ምንድነው ያሉት?
 • በመቶ ዓመት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ጦር እየገነባን ነው እያሉ ነው።
 • እሱማ ትክክል ነው፣ ለማንም የማይመለስ ጦር እየተገነባ ነው። 
 • ኤጭ፣ ምንድን ነው የለከፋችሁ እንደዚህ?
 • ምንድነው? ምን ሰማሽ ደግሞ?
 • በኢትዮጵያ ታሪክ ተገኝቶ የማያውቅ ገቢ ነው ዘንድሮ ከኤክስፖርት የተገኘው እያለ ነው ቴሌቪዥኑ። 
 • አዎ፣ ታሪካዊ ገቢ ነው ዘንድሮ ከኤክስፖርት የተገኘው። 

 

 • ምን ያህል ተገኝቶ ነው?
 • ከዓምናው በአሥር እጅ የሚበልጥ መሰለኝ። 
 • ምኑ ነው ታዲያ ታሪካዊ ያደረገው?
 • ከዚህ ቀደም ይህን ያህል ተገኝቶ ስለማያውቅ ነዋ፡፡
 • ከዚህ ቀደም አልተላከማ? ዓምና ተልኮ ቢሆን ይገኝ አልነበረም እንዴ?
 • በይ ተይው፡፡
 • እናንተም ተውና፡፡
 • ምኑን ነው የምንተወው፡፡
 • አንድ እጅ ከፍ አድርጋችሁ ታሪካዊ የምትሉንን! 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሐዘን ለመድረስ ጎረቤት ተገኝተው ለቀስተኛው በሙሉ የሚያወራው ነገር አልገባ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ባለቤታቸውን ስለጉዳዩ እየጠየቁ ነው] 

ጎረቤታችን ሐዘን ለመድረስ ብሄድ ለቀስተኛው በሙሉ በሹክሹክታ ያወራል። ግን የሚያወሩት ነገር ሊገባኝ አልቻለም። ምንድነው የሚያወሩት? እኔ ምን አውቄ? እንዴት? የሚያወሩትን ምንም አልተሰማሽም? እኔ እንድሰማ የፈለጉ አይመስልም ግን ... ግን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...