Thursday, June 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዕርዳታ ጭነው ትግራይ ክልል የሄዱ ተሽከርካሪዎች እየተመለሱ አይደለም ተባለ

ዕርዳታ ጭነው ትግራይ ክልል የሄዱ ተሽከርካሪዎች እየተመለሱ አይደለም ተባለ

ቀን:

የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ ወደ ትግራይ ክልል የተላኩ ተሽከርካሪዎች በብዛት እየተመለሱ አለመሆናቸውን፣ መንግሥትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) አስታወቀ፡፡

ሐሙስ መስከረም 6 ቀን 2014 ዓ.ም. መግለጫ የሰጡት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም፣ እስከ መስከረም 6 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ወደ ትግራይ ከተላኩ 466 ተሸከርካሪዎች መካከል 428 ተሽከርካሪዎች እስካሁን አልወጡም ብለዋል፡፡

‹‹ምናልባትም እስካሁን አርባ ገደማ ተሽከርካሪዎች ብቻ ናቸው ከትግራይ ክልል የወጡት ይህም ተሽከርካሪዎቹ ለምን ጥቅም እየዋሉ እንደሆነ የተለያዩ መላምቶች እንዲሰጡና በተሽከርካሪዎቹ ተጭነው የሚሄዱ የሰብዓዊ ዕርዳታዎች እንዲዘገዩ የሚያደርግ ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ በትዊተር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት፣ ባለፈው ሳምንት ወደ ትግራይ ክልል ከተላኩ 149 ተሽከርካሪዎች መካከል የትኞቹም እንዳልተመለሱ፣ ከሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ከተላኩ ተሽከርካሪዎቸ መካከል ከክልሉ የወጡት 38 ብቻ ናቸው ብሏል፡፡

‹‹በትግራይ ክልል ለሚገኙ ሰዎች ሕይወት አድን ድጋፍ ለማድረስ ተሽከርካሪዎች ያስፈልጉናል፤›› ሲልም ጽሑፉ በመልዕክቱ አስታውቋል፡፡

በየኢትዮጵያ መንግሥት ከሰመራ ወደ ትግራይ ክልል ለሚደረገው የሰብዓዊ ዕርዳታ ማጓጓዝ በተለያዩ ሰባት ሥፍራዎች የፍተሻ ጣቢያዎች ተቋቁመው የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ቁጥራቸው ወደ ሁለት እንዲቀነሱ መደረጉንና በዚህም ሳቢያ በተደጋጋሚ በሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች ይቀርቡ የነበሩ የመዘግየት ቅሬታዎች መፍትሔ እንዳገኙ ቢልለኔ ገልጸዋል፡፡ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች ግን የሚያቀርቡትን ድጋፍና የተሽከርካሪ ቁጥር አላሳደጉም ብለዋል፡፡ ይኼን ማድረግ ግን የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች ሚና ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት (ኦቻ) ሐሙስ መስከረም 6 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጣው የሁነት ሪፖርት የትግራይ ክልል የሰብዓዊ ሁኔታ ‹‹አስከፊ›› እንደሆነ አስታውቆ፣ ‹‹ቀጣይነት ያለው የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት፣ ገንዘብና ነዳጅ ማቅረብ ባለመቻሉ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ በፍጥነት ሊባባስ ይችላል ሲል አሳስቧል፡፡

በትግራይ ክልል 75 በመቶ አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፎች ተደራሽ እንደሆኑ የሚያትተው የድርጅቱ ሪፖርት፣ ብቸኛው የሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረቢያ መስመር በሆነው የሰመራ-አብዓላ-መቀሌ መንገድ እክሎች ገጥሞታል ብሏል፡፡

‹‹በተጨማሪም ዋና የሰብዓዊ ድጋፍ ጭነቶች ማዕከል በሆነው በአማራ ክልል ኮምቦልቻና በሰመራ ከፍተኛ የወታደራዊ እንቅስቃሴ ይታያል፡፡ በዚህም ምክንያት ቢያንስ የፍተሻ ጣቢያዎች እንደተቋቋሙ የተሰማ ሲሆን፣ ይኼም የሰብዓዊ ድጋፍ ተሽከርካሪዎች መዘግየትን ያስከትላል፤›› ይላል ሪፖርቱ፡፡

ነገር ግን ቢልለኔ የአውሮፓ ኅብረት የአየር አገልግሎት ወደ ትግራይ ድጋፍ ማድረስ እንደጀመረ፣ ከመስከረም 4 ቀን 2014 ዓ.ም. አንስቶ 32 የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢዎች ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 144 ሚሊዮን ብር ወደ መቀሌ እንዲያጓጉዙ ተፈቅዷል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው አሠራር ወጣ ያለውን ‹‹የወደፊት ግብይት›› ሥርዓት በይፋ አስጀመረ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው የማገበያየት ተግባሩ ወጣ ያለና በኢትዮጵያ...

የባንክ ማቋቋሚያ መሥፈርት እንደሚጠነክር ሚኒስትሩ ተናገሩ

 ባንኮች ስለውህደት እንዲያስቡም መክረዋል በኢትዮጵያ ውስጥ ባንክ ለማቋቋም የሚያስፈልገው መሥፈርት...