- አለመቀበል/አለማመን (ይኼ የሚፈጠረው ድምፅ በሚቆጠርበት ጊዜ ነው) – ፈጽሞ ሊሆን የማይችል ነገር ነው! አይደረግም፤ ሊሆን አይችልም፡፡
- ቁጣ (ውጤቱ ተጠቃሎ ከገባ በኋላ) – በዚህን ጊዜ የሚነገሩ ቃላትን መድገም አያስፈልግም፡፡ ለታዳጊ ወጣቶች የሚስማሙ አይደሉምና፡፡
- ድርድር (ውጤቱ ከታወቀ በኋላ) – እባካችሁ፣ ምርጫውን እንደገና እናከናውን፡፡ ድምፆቹ በትክክል አልተቆጠሩም፡፡ እባካችሁ፣ እንደገና ቁጠሩአቸው፡፡ ማንኛውንም ነገር አደርጋለሁ፡፡
- ድብርት (ድርድር ከተካሄደ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ) – አገራችን እስከዛሬ ድረስ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነበረች፡፡ በመጪዎቹ ሳምንታት ግን መበታተናችን የማይቀር ነው፡፡ አገሪቱ ትፈረካከሳለች፡፡ ወራሪዎች ይነሱብናል፤ የአየር ድብደባዎች ይከተላሉ፤ በሁሉም ረገድ ውድቀት!
- መቀበል (ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ ከተደረገ ከ24 ሰዓታት በኋላ) – የተመረጠው ፕሬዚዳንት ጥሩ ሥራ እንደሚሠራ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ጥሩ ውጥኖች አሉት፡፡ ምናልባት ዕድል ልንሰጠው ሳይገባ አይቀርም፡፡
* * *
አረፈ ዓይኔ ሐጎስ ‹‹ፖለቲከኞች እፈሩ›› [2013]