Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

የጥምረቱ ድምፅ

‹‹የሲቪል ማኅበራት እንደ ተልዕኳችን የተለያዩ ተግባራትን የምንፈጽም ቢሆንም የአገር አንድነትን፣ ፍቅርን፣ ሰላምን፣ ወንድማማችነትን፣ አብሮነትን በማጎልበት የተረጋጋችና በሁሉም መስክ ያደገች አገር እንድትኖረን እየሠራን ነው፤›› የሚለው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ለኢትዮጵያውያን ነው፡፡ ጥምረቱ ከ300 በላይ በአገር ውስጥ የተቋቋሙና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶችን ያሰባሰበ ሲሆን በተሰጠው ሕጋዊ ፈቃድ አማካይነት በኢትዮጵያ ለተከሰተው ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ መፍትሔ ለማስገኘት የድርሻውን ለመወጣት እየሠራ ይገኛል፡፡ ጥምረቱ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በሐረር፣ በደቡብና ሶማሌ ክልሎች በሚካሄደው ምርጫ ከ15 በላይ የጥምረቱ የሲቪል ማኅበራትን ለማሳተፍ በዝግጅት ላይ ነው፡፡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ለኢትዮጵያውያን ወቅታዊውን አገራዊ ሁኔታ አስመልክቶ መስከረም 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በምክትል ሰብሳቢው አቶ ታደለ ደርሰህ አማካይነት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የመግለጫውን ዋና ዋና ነጥቦች ሔለን ተስፋዬ እንደሚከተለው አጠናቅራዋለች፡፡

  • የሲቪል ማኅበረሰብ ጥምረት ለኢትዮጵያ በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ያለው ዕይታና የወሰደው አቋም?

ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ የነፃነት ተምሳሌት ነን፡፡ ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች እንዲሁም በርካታ ሃይማኖቶች ያሉባት አገር ናት፡፡ ለምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትስስርና ሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ታደርጋለች፡፡ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የተሰጠን በርካታ ተግባራትን እየፈጸምን ያለን ቢሆንም ከመላው ዓለም ከቅርብ ጊዜ በኋላ ነገሮች ሲታዩ እንደ አንድ የሲቪክ ማኅበረሰብ ጥምረት እጅግ በጣም አሳሳቢ ሆኖብናል፡፡ መንግሥትና ሕዝቡ የዓለም ማኅበረሰብም እንዲያውቁት ባለስምንት የአቅም መግለጫ አውጥተናል፡፡ የመጀመርያው በአገራችን ሰላማዊ ዜጎች በቤተ ክርስቲያንና መስጊዶች፣ በትምህርት ቤቶችና ጤና ጣቢያዎች እየተፈጸመ ያለውን ጥቃቶች አበክረን እናወግዛለን፡፡ ይህንን እየፈጸሙ ያሉት አካላት ላይም የሚመለከታቸው የአገር ውስጥና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እንዲያወግዙ እንጠይቃለን፡፡ የአማራ፣ የአፋር ክልል ከተሞች በከባድ መሣሪያ ጭምር በመደብደብ የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል፡፡ ለአብነትም የማይካድራ፣ ጭና የተፈጸሙ ጥቃቶችን የጅምላ መቃብሮችን በማስረጃነት ማንሳት ይቻላል፡፡ ይህንን የዘር መሠረት ያደረገ ጥቃት እኛ ሲቪል ማኅበራት አጥብቀን የምናወግዝ ሲሆን ፈጻሚ የሕወሓት ቡድን በአገርና በዓለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ሕጎች እንዲጠየቅ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ የመንግሥትና የግል ተቋሞችን በመዝረፍ የሕክምና የትምህርት ሕዝባዊ ተቋም ኅብረቶች በቡድኑ ወድሟል፡፡ ድርጊቱን የፈጸመው አካልም በሕግ መጠየቅ አለበት፡፡

  • የሱዳን ወረራና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ

ወቅታዊና አገራዊው ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሱዳን ድንበራችን ላይ ያደረገችው ወረራ አጥብቀን እናወግዛለን፡፡ ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት እንድትለቅና ሁኔታው ቀድሞ ወደነበረበት እንዲመለስ ሌሎች ጥያቄዎች ካሉም በድርድር እንዲታዩና ለዘመናት የቆየውን የሁለቱን አገሮች ወዳጅነት እንዲጠናከር ሁለቱ አገሮች በትብብር እንዲሠሩ እንጠይቃለን፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን የውስጥ ችግር በራሷ እንድትፈታ ዓለም አቀፍ ተቋሞች ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን እንዲተዉ ጠይቀናል፡፡ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድርም የአፍሪካውያን ችግር በአፍሪካውያን ለመፍታት በተቋቋመው የአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ሥር ሆኖ እንዲፈታ እንጠይቃለን፡፡ ማንኛውንም የአገራችን ላይ የሚደረግ አስገዳጅ የሌሎች አገሮችን ጫና ጥምረቱ አጥብቆ ይቃወማል፡፡  

  • ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እየወሰዱት ስላለ አቋም

ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በርካታ የዓለም አገሮች የተፈራረሟቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት አድርገው ሰውን በእኩል ዓይን በማየት ሚዛናዊ ሆነው ፍርድ መስጠት አለባቸው፡፡ ስለሆነም በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር፣ በወለጋና በሌሎች የአገራችን ክፍሎች እየተፈጸሙ ያሉትን አሰቃቂ የሰው ልጅ ግድያ፣ ሕፃናትን ለወታደራዊ ግዳጅ ማሠለፍ፣ የዜጎች መፈናቀልና ማኅበራዊ ቀውስን በሚገባ በማጤንና በትክክለኛ መረጃ በመታገዝ ከወገንተኝነት የፀዳና ዓለም አቀፍ መርሆዎችን መሠረት ያደረገ፣ የኢትዮጵያን አንድነትና ሰላም በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲሠሩ አበክረን እንጠይቃለን፡፡ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ፍትሐዊ ካልሆነ ዘገባ እንዲወጡና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች የደረሰውን የዜጎች ዕልቂት በኢትዮጵያ ለመድገም የሚደረጉትን እንቅስቃሴዎች ቆም ብለው እንዲያስቡና ከድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸው እናምናለን፡፡

  • በመስከረም ወር የመጨረሻ ሰኞ ለሚሰየመው መንግሥት የቀረቡ ጥያቄዎች በመስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም. የሚደረገው የመንግሥት ምሥረታ በኅብረተሰቡ ለበርካታ ጊዜያት ሲጠየቁ  የነበሩትን ለምሳሌ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የኑሮ ውድነት፣ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት እጥረትና የተለያዩ ችግሮች ፍትሐዊ ያልሆኑ የሀብት ክፍፍል፣ የመንግሥት ተግባሮች፣ ኢትዮጵያዊነትና ወንድማማችነት ከሚከፋፍል ዓይነት የተደራጀ ተግባርና ሌሎች ችግሮችን ሲፈጥሩ የነበሩና ያሉትን ጉዳዮች በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲፈቱ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡ በተለያዩ ዘርፎች የሚመደቡ የመንግሥት ኃላፊዎች ተልኮዎችን መፈጸም የሚያስችል የትምህርት ዝግጅትና ልምድ ያላቸው፣ ከዘረኝነትና ከሌሎች ከፋፋይ ተግባራት የፀዱ እንዲሆኑ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

 

ተዛማጅ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች ለማግኘት

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

አዋሽ ባንክ ለሁሉም ኅብረተሰብ የብድር አገልግሎት የሚያስገኙ ሁለት ክሬዲት ካርዶች ይፋ አደረገ

አዋሽ ባንክ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች በዘመናዊ መንገድ ብድር ማስገኘት...

ብሔራዊ ባንክ ለጥቃቅንና አነስተኛ ብድሮች ዋስትና መስጠት ሊጀምር ነው

ኢንተርፕራይዞችን ብቻ የሚያገለግል የፋይናንስ ማዕከል ሥራ ጀመረ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ...

ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ በርካታ ሰዎች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ በፖሊስ መከልከላቸውን ገለጹ

‹‹የኦሮሚያ ክልል መፍትሔ እንዲሰጥበት አሳውቀናል›› የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ‹‹ጉዳዩ...

አይኤምኤፍና ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የምንዛሪ ገበያ እንዳይኖር ሊመክሩ ነው

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍና ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያለውን...