የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው የተሰየሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ አዲሱ
የከተማዋ ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ በከንቲባነት ከሰየማቸው በኋላ ካሰሙት ዲስኩር የተገኘ፡፡ የመጀመርያዋ የአዲስ አበባ ሴት ከንቲባዋ በንግግራቸው፣ አዲስ አበቤዎች በኢትዮጵያዊነት የጋራ ድርና ማግ የተሳሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡ የመሠረተ ልማት ተጠቃሚነትን ማሳደግ፣ ቤት አቅርቦትን ማሻሻል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሠራም ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡