Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊልብ ያልተባለው ‹‹ሪሁማቲክ›› የተሰኘው የልብ ሕመም

ልብ ያልተባለው ‹‹ሪሁማቲክ›› የተሰኘው የልብ ሕመም

ቀን:

የልብ ሕመም መንስዔዎቹ ብዙ ናቸው፡፡ በቶንሲል ኢንፌክሽን (ሕመም) በጊዜው አለመታከም የሚከሰተው የልብ ሕመም ታዳጊዎችን ያጠቃል፡፡ የጤና ባለሙያዎች እንደሚናገሩት አብዛኛው የልብ ሕመም ቀድሞ በመከላከል 80 በመቶ ሕልፈተ ሕይወትን መቀነስ ይቻላል፡፡

የሕፃናት ስፔሻሊስቲ ሰናይ ዘሪሁን (ዶ/ር) በአንድ መጣጥፋቸው እንደገለጹት፣ ‹‹የቶንሲል ሕመም በራሱ ልጆቹን ከጊዜያዊ ሕመምና ምቾት መንሳት ያለፈ የከፋ ጉዳት ላይ ላይጥላቸው ይችላል። ይህም ቢሆን ግን ሁሉም በሕመሙ የተያዙ ሕፃናት ሕክምና ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ምክንያቱ ደሞ ከቶንሲልመም በኋላ የሚከተለውን የሪሁማቲክ የልብ ሕመም (Acute Rheumatic Fever) ለመከላከል ነው። ይህ ሕመም አስከፊ የሆነ የልብ ችግር ሲሆን አሁን በአገራችን ውስጥ አሳሳቢ ለሆነው የልብመም የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል።››

በዓለም 33 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ በሪሁማቲክን እንደተጠቃ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 300,000 የሚሆነው በዚሁ ሕመም ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡

ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ‹‹ሪሁማቲክ›› የልብ በሽታ ቀድሞ በመከላከል የሞት ምጣኔውን መቀነስ እንደሚቻል ነው፡፡ የሪሁማቲክ የልብ በሽታ ግሩን ኤ ስትሬናቶብስ በሚባል ባክቴሪያ የሚመጣ የጉሮሮ ኢንፌክሽን (ቶንሲል) ተከትሎ የሚመጣ በሽታ ነው፡፡

በሽታው በዋነኛነት ዕድሜያቸው ለጋ የሆነውን የማኅበረሰብ ክፍል የሚያጠቃ ነው፡፡ ይህም በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ትልቅ ለሚባል የገንዘብ ወጪ እየዳረገ ለመሆኑ ከልብ ሕሙማን ማዕከል የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡ ስለዚህ በሽታ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ሁኔታው ባይታወቅም ከ100 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ በሪሁማቲክ የልብ በሽታ ተጠቂ እንደሚሆኑ ይገመታል፡፡

ስለ ሪሁማቲክ የልብ በሽታ የተለያዩ አመለካከቶች መኖራቸው ይገለጻል፡፡ የቶንሲል ሕመም ቀዝቃዛ ውኃ በመጠጣትና ከምግብ በኋላ አፍን ሳይታጠቡ ለፀሐይ መጋለጥ ለሊከሰት ይችላል ተብሎ በማኅበረሰቡ ይታመናል፡፡ ነገር ግን ቶንሲል ኢንፌክሽን (መቆጣት) ሲሆን በባክቴሪያና በቫይረስ የሚመጣ መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በተለምዶ በዚህ ሕመም የተያዘ ታዳጊ ዳማከሴ መስጠት፣ እንጥል ማስቧጠጥና ሌሎችም ባህላዊ የሕክምና ዓይነቶችን ማኅበረሰቡ በተለምዶ ይጠቀማል፡፡ የቶንሲል ኢንፌክሽን በመጀመርያ በዘመናዊ ሕክምና መታከም እንዳለበት ባለሙያዎች የሚናገሩ ሲሆን ዳማከሴን ከዚያ በኋላ መጠቀም እንደሚቻል ይገልጻሉ፡፡

የሪሁማቲክ የልብ በሽታን ለመከላከል የአካባቢን ንፅህና መጠበቅ፣ የጉሮሮ ሕመም ሲሰማ ወደ ጤና ተቋም መሄድ፣ ጥርስ ማፅዳትና ሌሎችንም ማከናወን ይገባል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም ከካንሰርና ከሌሎች በሽታ በቀዳሚነት ገዳይ ብሎ ያስቀመጠው የልብ ሕመምን ነው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰዎች ከሚሞቱባቸው የበሽታ ዓይነቶች 32 በመቶውን የሚይዘው ልብና የተያያዥ ጉዳዮች መሆኑን አስቀምጧል፡፡ በልብና ተያያዥ ሕመሞች በዓመት 18.6 ሚሊዮን ሰዎች ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት በዓለም ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ሰዎች በልብ ሕመም ይሰቃያሉ፡፡ የልብ ጡንቻ፣ የልብ ደም ስር፣ የደም መርጋትና ሌሎችም የልብ ሕመሞች ተብለው በዓለም የጤና ድርጅት ተዘርዝረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በልብ የተያያዘ ጉዳዮች ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ሰዎች እንደሚሰቃዩ ይታመናል፡፡ ከልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በአዲስ አበባና ትልልቅ ከተሞች ላይ 24 በመቶ የሚሆኑት በልብና ተያያዥ ጉዳዮች ይጠቃሉ፡፡

ብዙ ምክንያቶች እንዳሉት የሚነገርለት የልብ ሕመም፣ የጤና ዘርፍ አለማደግና የግንዛቤ እጥረት፣ የሕክምና ክፍተትና የሕክምና ግብዓት እጥረት፣ እንዲሁም አሁን ደግሞ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሥጋት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የልብ ሕሙማን ሕፃናት መረጃ ማዕከል ሜዲካል ዳይሬክተር  ሳምሶን አደራ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ የልብ ሕመም አብዛኞቹ ቀድሞ በመከላከል ያለ ጊዜ መሞትን መቀነስ ይቻላል፡፡  ይህም ባለማጨስ፣ ከበቂ በላይ አልኮል አለመጠቀም፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ሌሎችም ተግባሮች በማከናወን መከላከል ይቻላል ብለዋል፡፡

አብዛኞቹ የልብ ሕመሞች ስር ከሰደዱ በኋላ ምልክት እንደሚያሳዩ ገልጸው፣ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ተገቢውን የመከላከል ላይ ማተኮር እንዳለበት ይመክራሉ፡፡

በማዕከሉ ከሰባት ሺሕ በላይ ሕሙማን የቀዶ ሕክምና ለማድረግ እየተጠባበቁ መሆኑን፣ በየዓመቱ 500 የሚደርሱ ሕፃናት የልብ ቀዶ ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

ሜዲካል ዳይሬክተሩ፣ በተለይም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ሕይወታቸውን ያጡ ሕሙማን መኖራቸው ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...