Thursday, March 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየስፖርት አበረታች ቅመሞችን መጠቀምና ማዘዋወር እስከ ዕድሜ ልክ እንደሚያስጠይቅ ተገለጸ

የስፖርት አበረታች ቅመሞችን መጠቀምና ማዘዋወር እስከ ዕድሜ ልክ እንደሚያስጠይቅ ተገለጸ

ቀን:

  • አትሌቶችና ሙያተኞች ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተነግሯል

 አትሌቶችና ከዘርፉ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሙያተኞችና ግለሰቦች በተፈጥሮና በሥልጠና የተገኘ የአካል ብቃት በጊዜያዊ መልክ በይበልጥ እንዲጨምር ማድረግ በወንጀል እንደሚያስጠይቅ ተገለጸ፡፡ በማናቸውም ስፖርታዊ ውድድሮች ጊዜ ተወዳዳሪዎች አካላዊና ሥነ ልቦናዊ የበላይነት ለማግኘት በሕግ የተከለከሉና ጎጂ የሆኑ ሰው ሠራሽ ንጥረ ነገሮችን መጠቀም ወይም አትሌቶች እንዲጠቀሙ ማበረታታት ሕጉ አጥብቆ እንደሚከለክል ተነግሯል፡፡

በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 526 ፀረ አበረታች ቅመሞችን (ዶፒንግ) የሚመለከቱ ጉዳዮች በግልጽ መደንገጉን ያስታወቀው የኢትዮጵያ የፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (ኢትዮ- ናዶ)፣ ማንኛውም ስፖርተኛ አበረታች ቅመሞችን ላለመጠቀምና ተጋላጭ ላለመሆን ራሱን የመጠበቅና ጥንቃቄ የማድረግ ኃላፊነት ይጠበቅበታል፡፡ ተቋሙ በማንኛውም ዓይነት መንገድ ይህን የስፖርት ሕግ የተላለፈ ስፖርተኛም ይሁን ተባባሪ አካል በሕግ ተጠያቂ ይደረጋል፣ እንደ ጥፋቱ ዓይነትና ክብደት ከማንኛውም ውድድር እስከ ዕድሜ ልክ ዕገዳ እንደሚተላፍበት አስጠንቅቋል፡፡

የስፖርት አበረታች ቅመሞች የሕግ ጥሰቶች የሚያስከትሉት አስተዳደራዊ ቅጣቶችና የወንጀል ተጠያቂነት፣ የስፖርት ሕግን መተላለፍ ብቻ ተደርጎ መቆጠር እንደሌለበት፣ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 526 ላይ የወንጀል ተጠያቂነትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮች ሆነው በአዋጅ እንዲደነገጉ መደረጉ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ- ናዶ ይህን መነሻ በማድረግ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው፣ የተከለከሉ መድኃኒቶችና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን መጠቀም ወይም ተጠቅሞ መገኘት ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር አራት ዓመት፣ እንዲሁም የምርመራ ናሙና ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን በተመሳሳይ አራት ዓመት ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር ያሳግዳል፡፡

የአድራሻ ምዝገባ በአግባቡ አለማካሄድና በሰጡት አድራሻ አለመገኘት ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት እንዲሁም በዶፒንግ ቁጥጥር ሥራ ጣልቃ መግባትና ማወክ አራት ዓመት የሚያሳግድ ስለመሆኑ ጭምር ተመልክቷል፡፡

ተባባሪ አካላትን ወይም ከሙያው ጋር ግንኙነት ኖሯቸው የተከለከሉ ንጥረ ነገሮችንና ሌሎች ተዛማጅ ቅመሞችን ከቦታ ቦታ ማዘዋወር ከአራት ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ፣ አትሌቶች የተከለከሉ ንጥረ ነገሮችንና መድኃኒቶችን እንዲጠቀሙ ማገዝ በተመሳሳይ ከአራት ዓመት ጀምሮ እስከ ዕድሜ ልክ፣ እንዲሁም የፀረ አበረታች መድኃኒቶች የሕግ ጥሰት የፈጸመ አካል እንዲያመልጥ መተባበር፣ ከሁለት እስከ አራት ዓመት፣ በአበረታች ንጥረ ነገር ጥሰት ከተቀጣ ሰው ጋር ያልተገባ ግንኙነት መመሥረትና መሥራት ደግሞ ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ከማንኛውም ስፖርታዊ መድረኮች እንደሚያሳግድ ጭምር ኢትዮ-ናዶ አስጠንቅቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...