Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
እኔ የምለዉከባንኮች ሽሽት ሲባል የት እንድረስ?

ከባንኮች ሽሽት ሲባል የት እንድረስ?

ቀን:

በጠቢቡ ሰለሞን

ባንኮች በሚያሰማሯቸው የአካውንት አስከፋቾች ሠራዊት ምክንያት መግቢያ መውጫ ካጡት ዜጎች መካከል አንዱ ነኝ፡፡ እንደ እኔ የመረራችሁና በየፊናችሁ በሚገጥማችሁ ማዋከብ የተጎሳቆላችሁ በርካታዎች እንደሆናችሁ አውቃለሁ፣ እሰማለሁም፡፡ ባንኮችና ሠራዊታቸው መብታችን ምን እንደሆነና ገደባቸው እስከ ምን ድረስ እንደሆነ አያውቁም፡፡ ትራንስፖርት ለመጠበቅ በተሠለፍኩበት ይመጣሉ፣ አካውንት ክፍት አልከፍትም ሙግት ነው፡፡ የአንዱ ባንክ ጀሌ ሲሄድ ሌላው ይከተላል፡፡ ዕቃ ለመሸመት ሱፐር ማርኬት ብገኝ አላስወጣ አላስገባ ግብግብ ነው፡፡ ቢሮ የለ፣ ሱቅ የለ፣ ቤተ ክርስቲያን የለ፣ መስጊድ የለ አካውንት ክፈት አልከፍትም የሞት የሽረት ትንንቅ ነው፡፡ በማንም ተደፍሮ የማያውቀው ቤቴ ሳይቀር በባንኮች ይደፈራል፡፡ ሰላሜን ተነስቺያለሁ፡፡ ሰብዓዊ መብቴ ተገፏል፣ የት ሄጄ አቤት እንደምል ጨንቆኛል፡፡ የመንግሥትና የሕግ ያለህ፣ በአገሬ ያለ ፈቃዴ መግቢያ መውጫ አጥቼ እየተሳደድኩ ነው፡፡

ወገኖቼ የሚያበሽቀው ጉዳይ ይህ ብቻ አይምሰላችሁ፡፡ አንድ ምስኪን ዜጋ የዕለት ጉርሱን ለማሸነፍ ሸቀጥ መንገድ ላይ ዘርግተህ ትሸጣለህ፣ ወይም መንገድ ላይ ወንበር ዘርግተህ አገልግሎት ሰጥተሃል ተብሎ ሲሳደድ ይውላል፡፡ ባንኮች ግን ግዙፍ ድንኳናቸውን እግረኛ መንገድ ላይ አንሰራፍተው ዘርግተው በግዙፍ ስፒከሮች እየደለቁ ወጪ ወራጁን ሲያስጨንቁ፣ በድምፅ ብክለት ሲረብሹና እግረኛውን ከመንገዱ አስወጥተው በተሸከርካሪ መንገድ ላይ እንዲጋፋ ሲያደርጉት ይውላሉ፡፡ ሀብታም ድርጅት ስለሆኑ ይሁን ወይም በማላውቀው ምክንያትርዓት አክብሩ፣ የዜጎችን መብት አትጋፉ የሚላቸውን ድምፅ አይሰማም፡፡ ጉዳዩ ባለቤት ያለውም አይመስልም፡፡

ባንኮች ትልልቅና ሀብታም ስለሆኑ የዜጎችን መብት የመጣስ፣ ዜጎችን የማጎሳቆል፣ ሰላማቸውን የመንሳት መብት የተሰጣቸው እስኪመስል ድረስ እንዲህ መግቢያ መውጫ እንዲያሳጡን ፈቃጁ ማነው? በተቃራኒው ደግሞ የዜጎች በሰላም የመንቀሳቀስ፣ በሥራና በመዝናኛ ቦታቸው ወይም በየመንገዱ ላይ ያለ መረበሽና ያለ መነትረክ መብታቸውንስ ለእነዚህ ኮርፖሬሽኖቹ አሳልፎ የመስጠት ሥልጣን የተቸረው የትኛው ተቋም ነው? እንደምንሰማው ከሆነም ከሠራተኞቻቸው ጋር ይህን ያህል ሺሕ አካውንት ከየትም ብለህ አስከፍት በሚል ግብግብ ተወጥረው እንደሚውሉ ነው፡፡ ይህ የውስጥ ጉዳያቸው ነው እንበል፡፡ አሳሳቢው ጉዳይ ግንራተኛው ላይ በሚፈጠረው የዘልማድ ጫና ተሸማቆ ከባንኩ በተሳደደ ቁጥር፣ በሰላም የመኖርና የመንቀሳቀስ መብታችን እየተገሰሰ መሆኑ ላይ ነው፡፡

ይህ ሁሉ የሚካሄደው በውድድር ስም ነው፡፡ ውድድሩ የባንኩን አሠራር በማዘመን፣ በማቀላጠፍ፣ አዳዲስ አሰራር በመዘርጋት ወይም አጓጊ የቁጠባና የወለድ ተመን በመስጠት የሚገኝ እንጂ፣ የዜጎችን የመንቀሳቀስ መብት በመድፈርናራተኛውን እናትህ እንደ ወለደችህ አካውንት ውለድ በማለት ወይም መንገድ እየዘጉና እጅ እየሳቡ እግረኛውን ለተሸከርካሪ አደጋ በማጋለጥ የሚሆን አይደለም፡፡ ባንኮች ደረስንበት የሚሉት በቅዠት ላይ የተመሠረተና የሌላውን ሕይወት ሰላም የሚነሳ የውድድር ዓለም ኃላፊት የጎደለውና ገንዘብ በማስቀመጥ፣ በመበደር፣ አገልግሎት በመቀበልና በመስጠት ህልውናቸው የተመሠረተበትን ሕዝብ መብት አለቅጥ የሚጋፋ ነው፡፡
 

ባንኮች ገንዘብ ስላላቸው ያውም ምንጩ ሕዝብ ነው፣አየር ሰዓት እየገዙ ከጠዋት እስከ ማታ በመገናኛ ብዙኃን ያደነቁሩናል፡፡ እሺ አማራጭ አለን፡፡ በምርጫችን ጣቢያውን በመዝጋታ መደንቆሩን እናልፈዋለን፡፡ ቀን መንገድ ዘግተው፣ በር አንኳኩተው፣ በተሸክርካሪ መስኮት አንገታቸውን አስግገው አስገብተው የሚነተርኩንን እንዴት እናምልጥ? ዘመናዊትና የማኅበራዊ ግዴታ ጸንሰ ሐሳቡም ያልተጻፈባቸው ባንኮች ገንዘብ በመስብሰብ ከማትረፍና የራሳቸውንና የባለ አክሲዮኖቻቸውን ኪስ ከማደለብ ውጪ አንዳችም የሞራል ግዴታ እንደማይሰማቸው አንዱ ማረጋገጫ ይኸው ነው፡፡ ገንዘብ ያለ ከመሰላቸው በሰላም የመንቀሳቀስና ያለ መደፈር የዜግንት መብት ስሜት አይሰጣቸውም፡፡

ሥነ ልቦናቸው ገንዘብ አምጡ አምጡ! አካውንት ክፈቱ ክፈቱ! ብድር ስጡ! ብቻ ነው፡፡ የባንኮች ሆድ ካልጠረቃ ለእነሱ ሲባል የት እንድረስ? የት እንሽሽ? የት እንፍለስ? ኃላፊነት የሰጠነው መንግሥት አለንሕግ አስከባሪዎችም በየዘርፉ ይገኛሉ፡፡ ዜጎች መቶ ሚሊዮኖችን መክፈል ባንችልም እንደ አቅማችን ግብር ከፋይ ነን፡፡ ተግተን እየሠራን አገራችንንም ሆነ ቤተሰባችን እያገለገልን ነው፡፡ ልጆቻችን፣ ቤተሰቦቻችን፣ አረጋውያንን በየሠፈሩ በየመንገዱ ላይ በውድድር ስም በአልጠግባ ባዮች፣ ከራስ በላይ ንፋስ በሚሉ ኢሞራላዊ ኃይሎች መደፈር የለባቸውም፡፡ ሲበቃ መብቃት አለበታ፡፡ ዜጎች በሰላም የመኖር፣ የመንቀሳቀስና ከትራፊክ አደጋ የመጠበቅ መብታቸው ሊከበር ይገባዋል እላላሁ፡፡

ይህ አካሄድ ሥርዓት እንዲይዝ ካልተደረገና ከወዲሁ መፍትሔ ሳይበጅለት ቀርቶ እያንዳንዱ አምራች፣ አስመጪ፣ ነባሮቹን ጨምሮ አዳዲስ የሚመጡት ባንኮች በየፈርጃቸው ተሠልፈው ድንኳናቸውን መንገድ ላይ እየዘረጉ መሸጥናቃቸውን ማስተዋወቅ ከቀጠሉ መድረሻች የት ሊሆን እንደሚችል በህሊናችሁ ሳሉት፡፡ በየመንገዱ ላይ ደጃፋቸውን መነገጃ ካደረጉ ሱቆች በር ላይ በተደቀኑ ግዙፍ ስፒከሮች አማካይነት የሚለቀቀው ከልክ ያለፈ የሙዚቃ ጩኽት ልባችን ሲተረተረው፣ ቀልባችንን ከላያችንን ላይ ሲያበረውና ስንሸማቀቅ እንውላለን፡፡ በዚህ ላይ ከፍሳሽ ካልፀዳ፣ ካልተሰበሰበ የመንገድ ዳር ጥራጊና ካልተስተካከለ የእግረኛ መንገድ ጋር እየታገልን፣ በሌላ በኩል ከተሸከርካሪ ጋር እየተጋፋን፣ በአናቱ ላይ ከአካውንት ክፈት አልከፍትም ውዝግባና ከድንኳን እየሸሸን እስከ መቼ እንዘልቃለን?

በእርግጥም መንገድ ላይ መነገድ እግረኛን ለአደጋ ስለሚያጋልጥ ስህተት መሆኑ ታምኖበት እግረኛ መንገድ ላይ መነገድ፣ አገልግሎት መስጠትም ሆነ ሸቀጥ መዘርጋት፣ ከድንበር ወጥቶ ሼድ ወይም ከለላ መሥራት፣ የተሸከርካሪም ሆነ የእግረኛ መንገድ ላይ ማስታወቂያ መዘርጋት፣ በግንባታ ቁሳቁስና በድንጋይፓርኪንግ አገልግሎት መንፈግና እግረኛን ማደናቀፍ በሕግ የተከለከለ ነው፡፡ በዚህ ምክንያትሃው ሸቃጭ እግረኞችን ለአደጋ አጋልጠሃል ተብሎ ሲሳደድ፣ ባለሀብቶች ግን ሰፋፊ ድንኳን ተክለው፣ የእግረኛውን መንገድ ዘግተው፣ እግረኛውን እያዋከቡና እያስቆሙ አገልግሎት የሚሰጡበትና የሚነግዱበት ሁኔታ አንዳችም አመክንዮ ሊቀርብበት አይችልም፡፡ ሁላችንም በሕግ ፊት እኩል ነን ብዬ እገምታለሁ፡፡ አንዳንድ ዜጎች/ድርጅቶችብታም ስለሆኑ ከሌሎች ዜጎች የበለጠ እኩል መብት አላቸው ካልተባለ በስተቀር፡፡ መንግሥት ሆይ!! ትሰማ እንደሆነ ስማና በሰላም የመንቀሳቀስና የእኩልነት መብታችን በአስቸኳይ አስመልስልን፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...