Thursday, March 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየስፖርተኞች የሕክምና አሰጣጥ ሥርዓት ተዘረጋ

የስፖርተኞች የሕክምና አሰጣጥ ሥርዓት ተዘረጋ

ቀን:

ዓለም አቀፉ የፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (ዋዳ) የስፖርተኞች ሕመምን ተከትሎ በየጊዜው ተለዋዋጭ እየሆነ የመጣውን የሕክምና አሰጣጥ ሥርዓት መቆጣጠር የሚያስችል የስፖርተኞች የሕክምና ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት ከዘረጋ ውሎ አድሯል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት (ኢትዮ ናዶ) የዋዳን መመርያ ተከትሎ ብሔራዊ የስፖርተኞች የሕክምና አሰጣጥ ሥርዓት መዘርጋቱን አስታውቋል፡፡

 

ኢትዮ ናዶ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው ከሆነ፣ አትሌቶች ሕመም ወይም ጉዳት ሲያጋጥማቸው የተከለከሉ መድኃኒቶችና ዘዴዎችን ጭምር በመጠቀም አስፈላጊውን ሕክምና የማግኘት መብት እንዳላቸው ያምናል፡፡ ይሁንና ብሔራዊ ተቋሙ ይህን የሕክምና አሰጣጥ ዘዴ ተከትሎ በአትሌቶች ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ለመከላከል ይችል ዘንድ፣ በየደረጃው የሕክምና ባለሙያዎችን የያዘ እንዲሁም ነፃና ገለልተኛ የሆነ ራሱን የቻለ የስፖርኞች የሕክምና አሰጣጥ ሥርዓት (Therapeutic Use Exemption System) ኮሚቴ ማቋቋሙን ይፋ አድሯል፡፡

እንደ መረጃው ከሆነ፣ የተቋቋመው የሕክምና አሰጣጥ ኮሚቴ የቀረበውን የሕክምና ምርመራ ማስረጃ በጥልቀት በመፈተሽ፣ እንደ አስፈላጊነቱ ፈቃድ ሊሰጥ ወይም ሊከለክል የሚችል ነው፡፡ በክልከላው ቅሬታ ያለው ማንኛውም ሰው በ21 ቀናት ውስጥ ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ የሚችልበት ሥርዓት መኖሩን ብሔራዊ ተቋሙ አስታውቋል፡፡

መረጃው በዓለም አቀፍ የስፖርት ማኅበራት የምርመራ ቋት ውስጥ የተካተቱ አትሌቶች በዓለም አቀፍ የስፖርት ማኅበራት፣ እንዲሁም በአገር አቀፍ የምርመራ ቋት ውስጥ የተካተቱ አትሌቶች፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት ጥያቄያቸውን በማቅረብ የተከለከሉ መድኃኒቶችን መጠቀም የሚችሉ ስለመሆኑ ጭምር ያስረዳል፡፡ ጥያቄ ማቅረቢያ ፎርሙን በተመለከተ ብሔራዊ ተቋሙን በአካል መጠየቅ እንደሚቻል አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...