Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትያልተበገረው የለንደን ማራቶን አሸናፊ ሲሳይ ለማ

ያልተበገረው የለንደን ማራቶን አሸናፊ ሲሳይ ለማ

ቀን:

ዓለም በጉጉት ከሚጠብቃቸው ዓመታዊ የጎዳና ላይ ውድድሮች አንዱ መሆኑ የሚነገርለት ለንደን ማራቶን ባለፈው እሑድ ተከናውኗል፡፡ ተጠባቂዎቹ ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን አትሌቶች ውድድሩን በበላይነት ማጠናቀቃቸው ሲታወቅ፣ በወንዶች ሲሳይ ለማ በሴቶች ደግሞ ኬንያዊቷ ጆሴሊን ጄፕኮስጋይ አሸንፈዋል፡፡

ከአውሮፓ ታላላቅ ከተሞች በጥንታዊነቷና በታሪካዊነቷ በምትጠቀሰው የለንደን ከተማ መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ.ም. የተካሄደው የለንደን ማራቶን፣ በወንዶች ሲሳይ ለማ 2፡04.01 በሆነ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ሲሆን፣ በሴቶች ደግሞ ኬንያዊቷ ጆሴሊን ጄፕኮስጋይ 2፡17.54 በመግባት ነበር አሸናፊ መሆን የቻለችው፡፡ በማይክሮ ሰከንድ ዘግይታ ውድድሩን ሁለተኛ በመሆን ያጠናቀቀችው ደጊቱ አዝመራው ርቀቱን 2፡17.58 የግል ፈጣን ሰዓቷ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ከጅምሩ እስከ ፍፃሜው የለንደን ከተማ የቱሪስት መስህብ ተብለው በአብዛኛው በሚታወቁ ታሪካዊ ቦታዎች አቅራቢያ የተካሄደውና ዘንድሮ ለ41ኛ ጊዜ በተደረገው ማራቶን፣ በሴቶች አሸናፊ የሆነችው ኬንያዊቷ ጆሴሊን አቅምና ብልጠትን መጠቀሟ ለአሸናፊነቷ ትልቁን ድርሻ የተወጣላት መሆኑ ተነግሯል፡፡

በማይክሮ ሰከንድ ተቀድማ ሁለተኛ የወጣችው ደጊቱ አዝመራው በውድድሩ የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ውኃ በምትቀበልበት ቅጽበት ኬንያዊቷ ጆሴሊን አፈትልካ የወጣችበትን ብልጠት መመልከት ደጊቱን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ልምድ ሊማሩ እንደሚገባ የሚናገሩ አልጠፉም፡፡

ውድድሩን 2፡18.18 በመግባት ሦስተኛ በመሆን ያጠናቀቀችው አሸቴ በከሬን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተከታትለው በመግባት የለንደን ማራቶን በተከናወነባቸው ጎዳዎችን የደመቁበትን ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ ከነዚህ አትለቶች መካከል ዘይኔባ ይመር 2፡21.40 ስምንተኛ፣ ትዕግሥት ግርማ 2፡22.45 ዘጠነኛ፣ ብርሃኔ ዲባባና መገርቱ ዓለሙ የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

የለንደን ማራቶንን ጨምሮ በታላላቅ የጎዳና ላይ ውድድሮች ሲሳተፍ የሚታወቀውን ሲሳይ ለማን ተከትሎ ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን ያጠናቀቀው ኬንያዊው ቪሴንት ኪፕቹምባ ሲሆን፣ ርቀቱን 2፡04.28 አጠናቋል፡፡ በውድድሩ የነሐስ ሜዳሊያ ያገኘው ሌላው ኢትዮጵያዊ ሙስነት ገረመው ሲሆን፣ 2፡04.41 ርቀቱን ማጠናቀቅ የቻለበት ሰዓት ነው፡፡

ሙስነት በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ይወክላሉ ተብለው ከሚጠበቁት አትሌቶች አንዱ የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ በአገር ውስጥ ባዘጋጀው 35 ኪሎ ሜትር የማጣሪያ ውድድር ላይ ባለመሳተፉ ምክንያት ከምርጫ ውጪ መደረጉ አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...