Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአርሶ አደሮችን ያማከለው ሽልማት

አርሶ አደሮችን ያማከለው ሽልማት

ቀን:

አርሶ አደሮች መደበኛ ትምህርት ያላገኙ እንደመሆናቸው፣ የቁጠባን አስፈላጊነትን በሚገባ ባለመረዳታቸው ከድህነት አዙሪት ሳይወጡ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ በመግፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ አዝመራ ሰምሮላቸው ያገኙትን ምርት ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ብዙ ፈተና እንደተጋረጠባቸውና ዘመናዊ ግብርና እንደናፈቃቸው ዘመናት ተቆጥረዋል የሚለው የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ነው፡፡

ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ መሠረቱ የሆኑትን አርሶ አደርና አርብቶ አደር ማኅበረሰብን ለማገልገል ዘርፈ ብዙ ፋይዳ የሚያስገኝላቸውን የቁጠባ አማራጭ እያቀረበ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ለዚህም የአርሶ አደሮች የቁጠባ ሒሳብን ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ ለማስተዋወቅ መቻሉን ገልጿል፡፡

በተጓዳኝም ባንኩ ዘንድሮ ባለውና ለመጀመርያ ጊዜ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሽልማት ዕጣ የማውጣት ሥርዓት መስከረም 25 ቀን 2014 ዓ.ም. አካሄዷል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ደርቤ አስፋው እንደገለጹት፣ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት በመጨመርና የቁጠባ ልማዳቸውን በማዳበር ከፍተኛ የሆነ ንቅናቄ ማድረግ ይገባል፡፡

ለግብርና የሚያገለግሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የአርሶ አደሩን አቅም ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ ምርቶችን በአግባቡ በማምረት ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ገበያ በማቅረብ ውጤት ተኮር ሥራዎችን መሥራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

የአርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማኅበራዊ ዕድገት ከፍ ለማድረግ ባንኩ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበርክትም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱም በብሔራዊ ሎተሪ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተከናወነ ሲሆን፣ ትራክተር ከነማረሻው የሚያስገኘው አንደኛ የዕጣ ቁጥር 147292 ሆኗል፡፡ በሁለተኛው ዕጣ የእጅ ትራክተር ማረሻ የሚያስገኙ ሁለት ቁጥሮች ደግሞ 114924 እና 108103 ሆነው መውጣታቸው ተገልጿል፡፡

በሽልማት መርሐ ግብሩ ሦስት ሞተር ሳይክሎችና አሥር የሞባይል ቀፎዎች ሦስተኛና አራተኛ ዕጣ ሆነው ለደንበኞች ወጥተዋል፡፡

የኦሮሚያ የኅብረት ሥራ ባንክ 10 ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 161,878 በላይ አርሶ አደሮችን የአገልግሎት ተጠቃሚ በማድረግ ብር ከ1.055 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ መሰብሰቡን ገልጿል፡፡

አርሶ አደሮች ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የሚጠቅማቸውን ግብዓት እንዲያገኙና ወደ ኢንቨስትመንት ለመግባት እንዲረዳቸው የፋይናንስ አቅርቦት የማግኘት ዕድላቸውን ለማሳደግ የሚጠቅም መሆኑን በወቅቱ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...