በጣፋጭ ንግግር
አስመስሎ መኖር
እጅግ አሰልቺና-
አንገሽጋሽ ነው ከምር፡፡
በጤፍ ቆዪ ምላስ
በሸጋ አንደበት
ድርጊት በሌለበት
ለከት በታጣለት፤
ሰሚውን አታክቶ
ልሳን አዘግቶ
ህሊናና አዕምሮን ሸብቦና አግቶ
ምናብን በመስረቅ – ቀልባችንን ገዝቶ
በስሜት ማዕበል – አድማጭን አስቶ
ምን ዋጋ ሊኖረው – ካልገበርነው ከቶ፡፡
ኤፍሬም አብርሃም ‹‹ካድማስ ወዲያ ማዶ›› (2013 ዓ.ም.)