Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
እኔ የምለዉተገቢ ትኩረት ያላገኘው ዂነት ቱሪዝም

ተገቢ ትኩረት ያላገኘው ዂነት ቱሪዝም

ቀን:

በዕዝራ ኃይለ ማርያም መኮንን

ዂነት ቱሪዝም ‘’Meetings Incentives Conferences and Exhibitions’’ የሚሉትን የእንግሊዝኛ ቃላት ምህጻረ ቃል በመያዝ ‘’MICE’’ ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህ የቱሪዝም ንዑስ ዘርፍ በስብሰባ፣ በማበረታቻና በማነቃቂያ፣ በጉባዔ ኮንፈረንስ (ኮንግረስ) እና በኤግዚቢሽን ላይ የተመሠረተ የቢዝነስ ቱሪዝም ነው፡፡

በዓለማችን ባለፉት አሥር ዓመታት በዂነት ቱሪዝም በርካታ ስብሰባዎች ማበረታቻዎች፣ ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽኖች በአፍሪካና በመላው ዓለም የተደረጉ ሲሆን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአገሮችን ዓመታዊ ብሔራዊ ምርት (GDP) በማሳደግ፣ ለዜጎች ተጨማሪ የሥራ ዕድል በመፍጠርና የታክስ ገቢ በማስገባት ከፍተኛ አስተዋኦ አበርክተዋል፡፡

አፍሪካ በዂነት ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ምቹ ዕድል ያላት ከፍተኛ የገበያ ማዕከል ነች፡፡ ቱሪዝም ኢትዮጵያ ከቢዝነስ ቱሪዝም ካምፓኒ ጋር በመተባበር “Meeting, Incentives, Conferences, Events and Exhibitions” በሚል ርዕስ በመስከረም 2019 ዓ.ም. ያወጣው ያልታተመ የጥናት ሰነድ እንደሚያመለክተው  እ.ኤ.አ. በ2018 በመላው ዓለም ከተካሄዱት 13,019 ዓለም አቀፍ የማኅበራት ጉባዔዎችና ስብሰባዎች ውስጥ በአፍሪካ የተካሄዱት 415 (ሦስት በመቶ) ብቻ ናቸው፡፡

ኢትየጵያ ከአፍሪካ አንጋፋዋ ነፃአገር፣ ውበትን ከተፈጥሮ ሀብት ጋር የታደለች፣ ታላላቅ ወንዞችና የዓለም ሞቃት ቦታ የሆነውን ዳሎልን፣ አክሱምን፣ ላሊበላንና ሌሎች እፅብ ድንቅ ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶችን የያዘች፣ ከ80 በላይ ብሔረሰቦችን ያቀፈች ጥንታዊ አገር ነች።

አዲስ አበባ በርካታ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችና ቅርሶችን የያዘች፣ ሦስተኛው የዓለምና የአፍሪካ የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ከተማ ስትሆን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መቀመጫ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንና የሌሎች 115 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ እንዲሁም የበርካታ አገሮች ኤምባሲዎች መቀመጫ ነች፡፡

የኢትዮጵያ ተመክሮ በዂነት ቱሪዝም

ኢትዮጵያ በዂነት ቱሪዝም ተጠቃሚ መሆን የጀመረችው ግንቦት 17 ቀን 1955 ዓ.ም.አዲስ አበባ ከተመሠረተው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (Organisation of African Unity) ጋር ተያይዞ ነው፡፡ ለድርጅቱ መመሥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት ባለግርማ ሞገሳዊ (Charimastic) የአፍሪካ መሪዎች ነበሩ፡፡ በተለይም የተከፋፈሉትን የሞኖሮቪያና የካዛብላንካ ሁለት ቡድኖች በማግባባት አንድ ድርጅት እንዲመሠረት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሚና የላቀ ነበር፡፡ ከድርጅቱ ምሥረታ በተጨማሪ በአፍሪካ አገሮች የተፈጠሩ ግጭቶችን በማስታረቅ ባበረከቱት አስተዋጽኦ አፍሪካ አባት” የሚል መጠሪያ አግኝተዋል፡፡

አፄው የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት አዲስ አበባ እንዲሆን ባቀረቡት ሐሳብ መሠረትም አፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ እንዲሆን በ32 መሥራችገር መሪዎች ፊርማ (OAU Charter) ፀድቆ  ዋና መሥሪያ ቤቱ አዲስ አበባ ሆኗልየመሥራች አገሮች መሪዎችና ልዑካን በአዲስ አበባ በመሰብሰባቸው አገራችን በዂነት ቱሪዝም ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ችላለች፡፡ በ1994 ዓ.ም የድርጅቱ ሥያሜ የአፍሪካ ኅብረት በሚል ተለውጧል።

የቢዝነስ ስብሰባ ኢንዱስትሪያልተነካው ሀብት’’ በሚል ርዕስ የወጣው መጣጥፍ እንደሚያመመለክተው፣ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍና አኅጉራዊ ትልልቅ ስብሰባዎችን የማዘጋጀት አቅም እንዳላት አስመስክራለች፡፡ እ.ኤ.አ. በ2015 ዓ.ም ሰባት ሺሕ ያህል እንግዶች የተሳተፉበትን ሦስተኛውን ፋይናንስ ለልማት ኮንፈረንስ በብቃትመወጣት እንግዶቿን አስደስታ ሸኝታለች፡፡

ዂነት ቱሪዝም ከፍተኛ ተሞክሮ ያላቸው አቶ ዓለማየሁ ገብረ ትንሳዔ እንዳሉት አገራችን በርካታ የቱሪዝም ሀብቶች ቢኖራትም፣ ከዘርፉ የምታገኘው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑን መንግሥት ተገንዝቦ ለቱሪዝም ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ነው፡፡ 

እንደ ባለሙያው ገለጻ ለዂነት ቱሪዝም ቀልጣፋና ምቹ ትራንስፖርት፣ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት፣ ምቹና ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች፣ በመስኩ የሠለጠነ የሰው ሀብት፣ እንግዳ ተቀባይ የሆነ ሕዝብና በአጠቃላይ ምቹና ጥራት ያለው መሠረተ ልማት መሟላት አለበት። ይህን መሠረት በማድረግም የበለፀጉ አገሮች ዂነት ቱሪዝም ያላቸውን መልካም አጋጣሚ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እ.ኤ.አ. በ2017 በሰሜን አሜሪካ 329.7 ሚሊዮን እንግዶች የተገለገሉ ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው በአማካይ 1156 ዶላር ወጪ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ በየዓመቱ አኅጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን በማስተናገድ አቅም ብትፈጥርም፣ዂነት ቱሪዝም ላይ ግን ብዙ አልሠራችም፡፡ በአዲስ አበባ ከ120 በላይ የኮከብ ደረጃ ያላቸው ሆቴሎች ሲኖሩ፣ በመስተንግዶና አንዳንድ ችግሮች መኖራቸውን ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡

አገራችን ኢኮኖሚዋን ልታሳድግምትችልባቸው መልካም ዕድሎች ውስጥ የቱሪዝም ዘርፍ ቀዳሚው ቢሆንም፣ ዘርፉ በሚጠይቀው መጠንሠለጠነ የሰው ኃይል እጥረት፣ የቱሪስት አገልግሎትና መሠረታዊ ልማት በብቃት አለመሟላት ጎልተው የሚታዩ ችግሮች ናቸው፡፡ በእነዚህና በመሳሰሉት ጉድለቶች የተነሳ እ.ኤ.አ. በ2018 የኮንቬሽንና የኮንግረስ ማኅበር (ICCA) ያወጣው መረጃ ኢትዮጵያ በዂነት ቱሪዝም ከ140 አገሮች 122ኛ ደረጃ ላይ እንድትገኝ አድርጓታል

ኬንያ፣ ሩዋንዳና ደቡብ አፍሪካ በዂነት ቱሪዝም ተጠቃሚዎች መሆናቸውን አቶ አለማየሁ ገብረ ትንሳዔ ጠቁመው፣ ንዑስ ዘርፉም በቢሊዮን ዶላር የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ ለአገራችን ኢኮኖሚ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ አገራችንም በዂነት ቱሪዝም ስኬታማ ለመሆን አቅም አላት ብለዋል፡፡

የዂነት ቱሪዝም በሥራ ምክንያት ሰዎች የሚያደርጓቸው ጉብኝቶች ወይም እንቅስቃሴዎች ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፣ ወዐጪያቸውን የሚሸፍንላቸው ሌላ አካል በመኖሩ በጉዟቸው፣ በስብሰባዎቻቸውና በጉብኝታቸው ቦታ ሁሉ ከፍተኛ ወጪ ያወጣሉ፡፡

ታሪካዊ፣ ባህላዊና የተፈጥሮ መስህቦችን ለመጎብኘት የሚመጡ ቱሪስቶች በቀን 100 ዶላር ሲያጠፉ፣ ዂነት (ማይስ) ተሰብሳቢዎች ደግሞ በቀን ከ500 እስከ 600 ዶላር እንደሚያጠፉ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

በአንድ አገር የሚኖር አንድ ትልቅ ኩባንያ በዓመቱ ባደረገው እንቅስቃሴ ከዕቅዱ በላይ የላቀ ትርፍ ካገኘ የሠራተኞቹን ወጪ ችሎ ሠራተኞቹ ወደ መረጡት አገር ሄደው እንዲዝናኑ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ተሳታፊዎቹ የተሰጣቸውን ገንዘብ ለማጥፋት አይሰስቱም። እንዲያውም በሚሄዱበት አገር የሚገኝ ረከስ ያለ ነገር ወይም መታሰቢያ ለመግዛት የራሳቸውንም ገንዘብ ይዘው ሊጓዙ ይችላሉ፡፡ በአብዛኛው ከአገራቸው ይዘው የተነሱትን ዶላር ኤግዚቢሽኑን ባዘጋጀው አገር ያጠፋሉ እንጂ ይዘውት አይመለሱም፡፡

ዕቅድ ይዘው ውቅያኖስ አቋርጠው የቱሪዝም መዳረሻዎችን የሚጎበኙ ተጓዦች ግን በአብዛኛው ወጪያቸውን የሚሸፍኑት ራሳቸው በመሆናቸው፣ የሚያወጡት ገንዘብ ኪሳቸውን ይነካል፡፡ በዚህም የተነሳ በዂነት ቱሪዝም የሚገኘው ጥቅም ከሌሎቹ አምስት እጅ እንደሚበልጥና ይህም ገቢ የውጭ ምንዛሪ ችግርን በመፍታት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የመስኩ ባለሙያዎች ያመለክታሉ፡፡

ዂነት ቱሪዝም የስብሰባና ኤግዚቢሽን ፕሮግራሞችን በቀላሉ ከሚያዘጋጁ ድርጅቶች ጋር በቅንጅትና በድርድር በመሥራት ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ ንዑስ ዘርፍ በመሆኑ አገሮች ለንዑስ ዘርፉ ትኩረት እንዲሰጡ አነሳስቷቸዋል፡፡

ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የታተመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ አቶ ቴዎድሮስ ደርበውን ጠቅሶ እንዳቀረበው፣ ዂነት ቱሪዝም አንድ ሰው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሲንቀሳቀስ በአማካይ 4500 ዶላር ያወጣል። ስብሰባና ኮንፈረንስ ላይ የሚካፈሉ እንግዶች በእረፍት ጊዜያቸው መዝናናትና ጉብኝት ፕሮግራም ጎን ለጎን ያረፉበትን ከተማ የቱሪስት መዳረሻዎች ይጎበኛሉ። የተለያዩ የገጸ በረከት ዕቃዎች ይገዛሉ፣ ይዝናናሉ። ስብሰባውን የሚያዘጋጀው አገር ዜጎችም የውጭ አገር ጉባዔ ተሳታፊዎች በሚያወጡት ወጪ ተጠቃሚ ይሆናሉ

የተፈጥሮ፣ ሰው ሠራሽና ታሪካዊ ቅርሶች የያዙ የቱሪስት መዳረሻዎች ማስጎብኘት ብቻ ሳይሆን፣ የተለያዩ ኩነቶችን በማከናወን በተቀናጀ አሠራር ማኅበራዊ ልማትን ለማፋጠንና ለዜጎችም የሥራ ዕድል በመፍጠር ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ማግኘት ይቻላል።

ፕሬዚዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ  ቱሪዝም የቦርድ ሰብሳቢ አቶይለ ማርያም ደሳለኝ በተገኙበት ዂነትየማይስ ኢትዮጵያየኮንቬንሽን ቢ ሮጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም ተቋቁሟል፡፡ ቢሮው “በምድረ ቀደምት እንገናኝየሚል መሪ ቃል አለው፡፡ የተቀረፀው የዂነት (ማይስ) ብራንድ የአማርኛ ፊደላትን ይዟል፡፡ ዂነት ቱሪዝምን ጽንሰ ሐሳብ የያዘ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ከአገራችን ምድረ ቀደምት የቱሪዝም መለያ (ብራንድ) ጋር ተዛማጅ ነው፡፡

የቢሮው መቋቋም በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ መጣው ዂነት ቱሪዝም ስኬታማ ከሆኑ አገሮች ተሞክሮ በመቅሰም፣ አገራችንን ከዓለም አቀፍ ጉባኤዎችና ዂነቶች ተጠቃሚ ያደርጋታል።

ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፍ በዓመት ሦስት ቢሊዮን ዶላር የምታገኝ ቢሆንም፣ የተጠናከረ ሥራ ቢሠራ ከዚህ በላይ ገቢ ልታገኝ ትችላለች፡፡ ‘’በእጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል’’ እንዲሉ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሳይንስ፣ትምህርትናባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ዘጠኝ የዓለም ቅርሶች በማስመዝገብ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም የሆነችው አገራችን በዚህ ዘርፍ የሚገባትን ጥቅም ሳታገኝ ቆይታለች፡፡

አቶ አለማየሁ እንደሚሉት የማይስ ኮንቬንሽን ቢሮ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን፣ ኮንግረሶችንና ኹነቶችን በአገራችን እንዲካሄዱ በመሳብ ዂነት ቱሪዝም ተጠቃሚ ለማድረግ ነው፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና ቅርሶቻችንን፣ ታላቁን አየር መንገዳችንን፣ ባለኮከብ ሆቴሎቻችንንና እሴቶቻችንን፣ እንዲሁም የጥቁር ሕዝቦች አርዓያና አለኝታ የሆነችውን ታሪካዊ አገራችንን በስፋት በማስተዋወቅለም አቀፍ ዂነቶችን ወደ አገራችን መሳብ ከንዑስ ዘርፉ ተጠቃሚ እንድትሆን ነው፡፡ ባለድርሻ አካላትም አገራችን በዂነት ቱሪዝም ተጠቃሚ እንድትሆን በንዑስ ዘርፉ ላይ ሳተፉ አዋጭ መሆኑን ባለሙያው አስታውቀዋል፡፡

“ስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም”

ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምሥራቅና በአፍሪካ መካከል የመሸጋገሪያ ድልድይ፣ የአውሮፓና የእስያ መተላለፊያ መንገድ ነች፡፡ ከዚህም አንፃር ሌላው የቱሪዝም የገቢ ምንጭ ሆኖ የሚያገለግለው ‘’ስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም” ሲሆን፣ ተጓዦች ከመነሻ አገራቸው በሚነሱበት ጊዜ በመሸጋገሪያነት በኢትዮጵያ ሲያልፉ ጥቂት ቀናት በአገራችን ቆይታ አድርገው ወደ መዳረሻ አገር እንዲሄዱ የሚያስችል የቱሪዝም ዓይነት ነው፡፡ በ”ስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም” ከፍተኛ ተጠቃሚ ከሆኑ አገሮች ውስጥ አይስላንድ፣ ዱባይና ፖርቹጋል ለአብነት ይጠቀሳሉ፡፡

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ‘’ስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም’’ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ1950ዎቹ ሲሆን በርካታ አገሮች ይህን የቱሪዝም ቢዝነስ በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡ በዚህ የቱሪዝም መስክ ተጠቃሚ የሆኑ አገሮች ተመክሮ እንደሚጠቁመው፣ በጥናት ላይ በመመሥረት በሚሠሩ የገበያ ልማትና የማስተዋወቅ ሥራ ተጓዡ መንገደኛ የጉዞውን ቀን እንዲጨምር በማድረግ ተጠቃሚ መሆን ይቻላል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመት ከ10 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን ከ120 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹ ወደ ተለያዩ አገሮች ያጓጉዛል፡፡ አዲስ አበባ ከሰሜን አፍሪካ አገሮች በስተቀር፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ ወደ ሌሎች አገሮች ከሌሎች አገሮች ደግሞ ወደ አፍሪካ አገሮች የሚጓጓዙ ተጓዦች ኮሪደር (መተላለፊያ) ነች፡፡ ከዚህም አንፃር ኢትዮጵያ በ”ስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም’’ ለመጠቀም ምቹ ዕድል እንዳላት የመስኩ ባለሙያዎች ይገልጻሉ

ቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት እያገኘ መጥቷል፡፡ መንግሥት በገበታ ለአገርና በሸገር ፕሮጀክቶች ዘርፉን ለመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል፡፡ ዂነት ቱሪዝም በአግባቡ ከተሰራበት ውጤታማ ሊያደርገን የሚችል የቢዝነስ ቱሪዝም መሆኑን አቶ አለማየሁ ገብረ ትንሳዔ አመልክተዋል፡፡

በአገራችን ዂነት ቱሪዝምን ለማስፋፋት ሆቴሎችን መገንባትና የምግብ፣ የመጠጥና የመኝታ አቅርቦት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ከልማዳዊው የቱሪዝም አሠራርና አቅርቦት መላቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰፊና ምቹ አዳራሾችን መገንባት፣ የቱሪዝም መዳረሻ አካባቢን ታሪክና ድንግል ባህል ላይ በመመሥረት የቱሪስቶችንና የተስተናጋጆችን መንፈስና ቀልብ የሚገዛ መስተንግዶ ማድረግ ግድ ይላል፡፡

በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት የተቀዛቀዘው የቱሪዝም ዘርፍ አሁን በመነቃቃት ላይ ይገኛል፡፡ ያለ ድካም ስኬት አይኖርምና አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሐረር፣ ባህር ዳርና ጎንደር ከተሞችንና ሌሎች የአገራችን ከተሞችን ለዂነት ቱሪዝም መዳረሻነት ምቹ ለማድረግ በትጋት መሥራት ያስፈልጋል፡፡

ዂነት ቱሪዝም የማይመለከተው ኅብረተሰብ፣ ሙያና የሥራ መስክ የለም፡፡ በተለይ ከትራንስፖርት፣ ከሆቴሎች፣ ከአስጎብኝዎችና ለዘርፉ ቅርበት ካላቸው ሌሎች ሥራዎችና ሙያዎች ጋር ድርና ማግ ነው፡፡

መንግሥት ለቱሪዝም ዘርፍ በሰጠው ትኩረትም፣ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ወጣው አዋጅ፣ የ“ቱሪዝም ሚኒስቴር’’ እንዲቋቋም አድርጓል፡፡ ይህም ለዘርፉ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይታመናል፡፡  

በአገራችን ብዙ ያልተሠራበት ዂነት ቱሪዝም ከኢኮኖሚ ፋይዳው በተጨማሪ፣ ለአገር ገጽታ ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የላቀ በመሆኑ አይመለከተኝም የሚባልበት አይደለምና በዜግነታችን የዂነት ቢዝነስ ቱሪዝምን ለማሳደግ የበኩላችንን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...