Sunday, November 27, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናኢዜማ በምሥራቅ ወለጋ በንፁኃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ

  ኢዜማ በምሥራቅ ወለጋ በንፁኃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን በንፁኃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ፡፡

  ፓርቲው ማክሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ በምሥራቅ ወለጋ ኪራሙ ወረዳ ሀሮ ቀበሌና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤደንጎሮና ሆሮ ወረዳሎሚጫ፣ ተሉሞቲ፣ ቦቶሮ፣ ቦራ፣ ወለጌ፣ ትጌ፣ ኮትቻ፣ ጋሬሮ፣ ጎርቴና አርቡሲንታ የዜጎች ሞት መቀጠሉን አስታውቋል፡፡

  በተጨማሪም አርቡሶቴ፣ ገበርጉን 2ኛ፣ ኢዶቦቲና ሌሎች አካባቢዎች በሚኖሩ ንፁኃን ዜጎች ላይ ማንነታቸውን መሠረት አድርጎ እየተፈጸመ የሚገኘው አሰቃቂ ጥቃት ጊዜ እየጠበቀ እያገረሸ፣ አሁንም የዜጎች ውድ ሕይወት እየቀጠፈ መሆኑን አመላክቷል፡፡

  ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ንፁኃን ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ከመጠቃታቸው በፊት ሥጋታቸውን በአካባቢያቸው ላሉ የመንግሥት አካላት ሲገልጹ ቢቆዩም የዞኑ አስተዳደር አካላት፣ ‹‹በቁጥጥራችን ሥር ነው የሚያሠጋ ነገር የለም›› እያሉ ብዙ ወገኖች እንደተገደሉ ኢዜማ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

  ‹‹መንግሥት በአካባቢው ያለውን የአስተዳደር መዋቅር እንዲፈትሽ በተደጋጋሚ ያሳሰብን ቢሆንም፣ ይህ ነው የሚባል ዕርምጃ ባለመወሰዱ ጥቃቶቹ አሁንም ቀጥለዋል፤›› ሲል  በመግለጫው አክሏል፡፡

  በተገለጹት አካባቢዎች ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር መገናኛ መንገዶች ተቆፋፍረው በታጣቂዎች በመዘጋታቸው ምክንያት እንቅስቃሴ በመቋረጡ፣ በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች ሕክምና፣ መድኃኒትና ሸቀጣ ሸቀጥ ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ሆነባቸው እንደሰነበተና የመሣሪያ ድምፅ እየሰሙ የሚውሉ ሕፃናት እጅግ መሸበራቸውንም አስታውቋል፡፡

  ንፁኃንን ለመታደግ በቦታው ያሉ የፌዴራል የፀጥታ አካላት ቁጥራቸው ጥቂት በመሆኑ ሕዝቡን መታደግ ካለመቻላቸው ባለፈ፣ እነሱም የጥቃቱ ሰለባ ስለመሆናቸው ከቦታው መረጃ እንደ ደረሰው ፓርቲው በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

  በጥቃቱ መደጋገምና ተመሳሳይነት የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት ማስጠበቅ ተቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን የሚገባው መንግሥት፣ ለችግሩ የሚገባውን ያህል ትኩረት እንዳልሰጠው አመላካች እንደሆነ ገልጿል፡፡

  በተደጋጋሚ የሚደርሱትን ጥቃቶች ለማስቆምና አጥፊዎችን ሕግ ፊት አቅርቦ የማያዳግም ዕርምጃ ለመውሰድ ለምን እንዳልተቻለ፣ የክልሉ መንግሥትና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ማብራሪያ እንዲሰጡበት ጠይቋል፡፡

  ፓርቲው ከዚህ በፊት በአካባቢው ነዋሪዎች የደረሱ ከሰብዓዊነት ፍፁም የራቁ ግፎች አሁንም በአካባቢዎቹ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ዳግም ሳይከሰቱ ዕርምጃ እንዲወሰድ፣ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ከሚደርስባቸው የደኅንነት ሥጋት ወጥተው ሰላማዊ የዕለት ከዕለት ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ዘላቂ መፍትሔ በአስቸኳይ እንዲሰጥ ኢዜማ አሳስቧል፡፡

  ሚወሰዱ ዕርምጃዎችን በተመለከተ ግልጽና ወቅቱን የጠበቀ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...