Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን የወከለችው ብስክሌተኛ በስፖርት አካዴሚ ታቀፈች

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን የወከለችው ብስክሌተኛ በስፖርት አካዴሚ ታቀፈች

ቀን:

በፌዴራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት፣ ወደ ትውልድ ሥፍራዋና ቤተሰቦቿ መንቀሳቀስ ያልቻለችውና በቶኪዮ ኦሊምፒክ በብስክሌት አገሯን የወከለችው ሰላም አምሃ ቆይታዋን በወጣቶች ስፖርት አካዴሚ አድርጋ ልምምዷን እንድትቀጥል ተደርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚም በቀረበለት ጥያቄ መሠረት አትሌቷን ለጊዜው ተቀብሎ ማረፊያ መስጠቱ ታውቋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ብስክሌተኛዋን ሰላም አምሃን ጨምሮ ለዋናው አሠልጣኝ፣ ለተጠባባቂውና መካኒኩ በአጠቃላይ ለአራት የቶኪዮ 2020 ልዑክ ከነሐሴ ወር ጀምሮ በየወሩ አምስት ሺሕ ብር ወርኃዊ ክፍያ ሲፈጽም መቆየቱ ይገልጻል፡፡ በዚህ መልኩ የአትሌቷንና የአሠልጣኞቿን ወርኃዊ ክፍያ ከሆቴል ወጪ ጋር ለማሟላት እንደተቸገረና ይህንኑ የቀድሞ ስፖርት ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሸኩር እንዲያውቁት አድርጎ፣ እሳቸውም ከአካዴሚው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ችግሩ ሊፈታ ማስቻሉን ኃላፊዎቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉት የአካዴሚው ኃላፊዎች በበኩላቸው፣ ‹‹ስምምነቱ አትሌቷን በቋሚነት የሚያቆይ አይደለም፡፡ ምክንያቱም አትሌቷ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚ ንብረት አይደለችም፡፡ እንደሚታወቀው ብሔራዊ ተቋሙ በተለይም በአሁኑ ወቅት ወደ አካዴሚው ገብተው ለቀጣዮቹ ዓመታት ከተለያዩ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች እየመለመለ የሚያሠለጥናቸው ታዳጊ ወጣቶች ይዟል፤›› በማለት አትሌቷን በዘላቂነት ሊያኖር የሚችልበት አቅም እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...