Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚ የጥሩነሽ ዲባባ ማሠልጠኛ ማዕከልን እንዲያካትት ተወሰነ

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚ የጥሩነሽ ዲባባ ማሠልጠኛ ማዕከልን እንዲያካትት ተወሰነ

ቀን:

ቀደም ባሉት ዓመታት የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዴሚ ተብሎ ሲጠራ የቆየው ተቋም፣ በአዲሱ አደረጃጀት ‹‹የኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚ›› ተብሎ እንዲጠራ ተወስኗል፡፡ በአሰላ የሚገኘው የጥሩነሽ ዲባባ የስፖርት ማሠልጠኛ ማዕከል በስፖርት አካዴሚው ስር ሆኖ እንዲቀጥል ስለመደረጉ የአስፈጻሚ አካላትን በአዲስ መልክ ለማደራጀት በተዘጋጀው አዋጅ ተካቷል፡፡

 

በአዲሱ የመንግሥት የሥራ አስፈጻሚ ተቋማትን ለመወሰን በወጣው አዋጅም፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ‹‹የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዴሚ›› በሚል መጠሪያ ተቋቁሞ ሲንቀሳቀስ የቆየው ብሔራዊ አካዴሚ ከሚታወቅበት ስያሜው ‹‹ወጣቶች›› የሚለው ወጥቶ ‹‹የኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚ›› ተብሎ እንዲጠራ ተደርጓል፡፡

ከዚሁ የአደረጃጀት ለውጥ ጎን ለጎን ከዓመታት በፊት በአሰላ ከተማ ‹‹የጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል›› በሚል መጠሪያ በአትሌቲክሱ ዘርፍ የሜዳ ተግባራትን ጨምሮ ታዳጊ ወጣቶች ላይ ራሱን ችሎ ሲሠራ የቆየው ማዕከል መብትና ግዴታዎች ጭምር፣ ለኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚ ተላልፎ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ ቀደም ሲልም የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዴሚና የጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል አሁን ባለው መልክ እንዲደራጅ ፍላጎት የነበራቸው በርካታ የዘርፉ ሙያተኞች እምነትና አስተያየት ሆኖ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

በአዲሱ አዋጅ መሠረት የጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ተጠሪነት፣ ለኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለሪፖርተር አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል በኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚ ውስጥ የሚገኙ ሙያተኞች ይጠቀሳሉ፡፡

አስተያየት ሰጪዎቹ የተቋማቱን ዝርዝር ሥልጣንና ተግባር የሚገልጸው አዋጅ ገና እጃችን አልገባም በሚል ለጊዜው ማንነታቸው መግለጽ ባይፈልጉም፣ በአገር አቀፍ ደረጀ ለተመሳሳይ ዓላማ እና ግብ የተቋቋሙት ሁለቱ ተቋማት እስከ አሁንም መለያየት አልነበረባቸውም፡፡ ምክንያቱንም ብሔራዊ ተቋሙም ሆነ አሰላ የሚገኘው የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል፣ ከበጀት አኳያ ለሀብት ብክነት መንስኤ ከመሆን ያለፈ ፋይዳው ብዙም አልነበረምና ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ኃላፊነትን ከመወጣትና ተጠያቂነትን ከማስፈን አንጻርም አስቸጋሪና እልህ አስጨራሽ አሠራሮች እንዲሁም መረጃዎች በተገቢው መንገድ ትኩረት አግኝተው በተግባር ላይ ለማዋል ተግዳሮት ሆኖ ቆይቷል በማለት የተደረገው የመዋቅር ለውጥ ተገቢነት ያለው ስለመሆኑ ጭምር ይናገራሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...