መውሊድ በልዩ ሥነ ሥርዓት ከሚከበርባቸው ቦታዎች አንዱ የጡርሲና መስጊድ ነው፡፡ ሀገሬ ሚዲያ ባዘጋጀው ‹‹የኢትዮጵያ ፌስቲቫል ማውጫ›› ላይ እንደተገለጸው፣ መስጊዱ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን (ወሎ) ከዞኑ ርዕሰ ከተማ ከከሚሴ 16 ኪሎ ሜትር በከሚሴና በወለዲ ከተሞች መካከል ሸከላ ተብላ በምትጠራ ትንሽ የገጠር ከተማ ይገኛል፡፡ ለበዓል ታዳሚዎች ከሚቀርበው መስተንግዶ አንዱ የቡና ሥነ ሥርዓቱ ነው፡፡ ፎቶው የሚያሳየው 190 ሲኒዎችን የሚደረድረው ባለ ሁለት ሜትሩ ረከቦትና እንስራ አከሎቹ ጀበናዎችን ነው፡፡
ፎቶ፡ ሀገሬ ሚዲያ