Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየፀጥታ አስከባሪዎች የነበሩበትን አካባቢ ለቀው ሲወጡ የሚፈጸሙ ጥቃቶች አሳሳቢ መሆናቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

የፀጥታ አስከባሪዎች የነበሩበትን አካባቢ ለቀው ሲወጡ የሚፈጸሙ ጥቃቶች አሳሳቢ መሆናቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

ቀን:

በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ አንድ አካባቢን ለቀው መሄዳቸውን ተከትሎ የሚፈጸሙ ጥቃቶች አሳሳቢ መሆናቸውን፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በምሥራቅ ወለጋና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በመስፋፋት ላይ በመሆናቸውና ባህሪያቸውን እየቀየሩ ብሔር ተኮር ወደ ሆነ የእርስ በርስ ግጭት ሊያመሩ ስለሚችሉ፣ መንግሥት በቂ የፀጥታ ኃይሎችን በአፋጣኝና በቋሚነት በአካባቢው ሊያሠማራ እንደሚገባ አሳስቧል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) እንዳስታወቁት፣ ግጭቶቹ ባሉባቸው አካባቢዎች በተለይም የአካባቢውንም ሆነ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ሥምሪት በተመለከተ  በተደጋጋሚ እየታየ ያለው ችግር፣ የፀጥታ አስከባሪዎች አንድ አካባቢን ለቅቀው መሄዳቸውን ተከትሎ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ናቸው፡፡

 የችግሩን  አሳሳቢነት ኢሰመኮ ከዚህ በፊትም ማሳወቁን የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፣ ‹‹ግጭቱ ሙሉ በሙሉ ባህሪውን በመቀየር ወደ እርስ በርስ ግጭት እንዳይለወጥና የአካባቢው ሰላምና ደኅንነት ሙሉ በሙሉ እስከሚረጋገጥ ድረስ፣ በቂ የፀጥታ ኃይሎች በተለይ ለግጭትና ጥቃት ተጋላጭ  የሆኑ አካባቢዎች ላይ በቋሚነት ተመድበው  መንግሥት የሁሉንም ነዋሪዎች ደኅንነት የማስጠበቅና ከጥቃት መከላከል ግዴታና ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከሦስት ሳምንት አስቀድሞ ባወጣው መግለጫ ጊዳ ኪራሙ ወረዳን ጨምሮ በተለያዩ የምሥራቅ ወለጋ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በአሥጊ ሁኔታ እንደሚገኙ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፣ ወደ ወረዳው የሚወስዱ የተዘጉ መንገዶችን ማስከፈትን ጨምሮ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ከፌዴራሉ የፀጥታ ኃይሎች ጋር ሊቀናጁ እንደሚገባ ማሳሰቡን በመግለጫው አስታውቋል።

የክልሉ የፀጥታ ኃላፊዎች ለኢሰመኮ እንደገለጹት፣ በኪራሙ ወረዳ፣ ሃሮ ከተማ የነበረው ‹‹የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ለሌላ ሥራ አካባቢውን ለቅቆ መውጣቱን›› ተከትሎ፣ በሃሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ ከመስከረም 30 ቀን 2014 .. ጀምሮ ሰላማዊ ሰዎችበኦነግሸኔታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለኮሚሽኑ እንዳስረዱ አስታውቋል፡፡

በዚሁ ከተማ ይህንኑ ግድያ ምክንያት በማድረግ በኢመደበኛ አደረጃጀት የተደራጁ የተወሰኑ የአካባቢውና አጎራባች ክልል ነዋሪዎች በሲቪል ሰዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን፣ የተጎጂዎች ቤተሰቦችና  የአካባቢው አስተዳደር  አካላት  ለኮሚሽኑ መረጃ እንደሰጡ ገልጿል፡፡

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በኡሙሩ ወረዳ ከነሐሴ 12 ቀን 2013 ..  ጀምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች በሆኑናራሳቸውን ከጥቃት እንዲከላከሉበሚል መሣሪያ እንዲታጠቁ ስለመደረጋቸው ወይም እንደተፈቀደላቸው በሚነገርላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች፣ በተመሳሳይ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ ኢሰመኮ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ጥቃቶችና ግድያዎች የብሔር ማንነትን መሠረት አድርገው አንድ ጊዜ በአማራ ብሔር ተወላጆች፣ ሌላ ጊዜ በኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ላይ የሚፈጸሙ ብሔር ተኮር ጥቃቶች ናቸው ያለው ኮሚሽኑ፣ በዚህም በአካባቢው ነዋሪዎች በሆኑ በሁለቱ ብሔር ተወላጆች መካከል ከፍተኛ ውጥረትና የእርስ በርስ ግጭት ሥጋት ፈጥሯል ሲልም አስረድቷል፡፡

ይህንኑ ግጭት በመሸሽ ከምሥራቅ ወለጋ ሊሙ ወረዳ፣ ጉደያ ቢላ ወረዳ፣ ኪረሙ ወረዳ፣ ሌቃ ዱለቻ ወረዳ፣ ዲጋ ወረዳና ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ኡሙሩ ወረዳ በአጠቃላይ 43,139 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የዞኑ የአስተዳደርና የፀጥታ አካላት ለኮሚሽኑ ማስረዳታቸውን አክሏል፡፡ በተጨማሪም ወደ እነዚህ አካባቢዎች የሚያደርሱ መንገዶች አሁንም ዝግ በመሆናቸውና በአካባቢው ያለው ውጥረት አሁንም ባለመርገቡ ምክንያት፣ ሰዎች መሠረታዊ አቅርቦቶችንና ሕክምና ለማግኘት ጭምር በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚገኙ ኢሰመኮ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...