Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትበርካታ ኢትዮጵያውያን የተካፈሉበት የታላቁ አፍሪካ ሩጫ በአሜሪካ

በርካታ ኢትዮጵያውያን የተካፈሉበት የታላቁ አፍሪካ ሩጫ በአሜሪካ

ቀን:

ጥሩነሽ ዲባባ የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚ ሆናችለች

 

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እዚያው የሚኖሩ አፍሪካውያንንም ማቀራረብ ግቡ ያደረገው የታላቁ አፍሪካ ሩጫ ለሦስተኛ ጊዜ ተከናውኗል፡፡

- Advertisement -

‹‹አብሮነት መሻል ነው›› በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 6 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋሽንግተን የተከናወነው የጎዳና ሩጫ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አሳትፏል፡፡ ውድድሩ ኢትዮጵያውያን ለማሰባሰብ፣ የመጀመሪያ ትውልድ ልጆችን ከባህላቸው  ጋር የበለጠ ለማቀራረብና ለተለያዩ በጎ ሥራዎች ገቢ ለማሰባሰብ ዓላማውን አድርጎ  እንደተከናወነ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ከ20 በላይ ኦሊምፒያኖችና የዓለም ሻምፒዮኖች በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት መገኘታቸውን የታላቁ አፍሪካ ሩጫ ዋና አዘጋጅ ጋሻው አበዝ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ባለፉት የታላቁ አፍሪካ ሩጫ ዝግጅቶች፣ የኢትዮጵያ አንጋፋ አትሌቶች ማለትም ደራርቱ ቱሉ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ገንዘቤ ዲባባ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ሚሊዮን ወልዴ፣ ፋጡማ ሮባና ሌሎችም በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡

የዘንድሮውን ውድድር በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋና ደራርቱ ቱሉ ያስጀመሩት ሲሆን፣ በሴቶች ምድብ ብርሃኔ አደሬና ቁጥሬ ዱለቻ አንደኛና ሁለተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡

እንደ ውድድሩ አዘጋጅ ጋሻው አበዝ (ዶ/ር) አስተያየት ከሆነ፣ ዝግጅቱ አትሌቲክስን እንደ መድረክ በመጠቀም፣ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በማቀራረብ ረገድ ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

ከዝግጅቱ ባሻገር የበጎ ሥራ ማከናወን ግቡ ያደረገው ታላቁ የአፍሪካ የሩጫ ዝግጅት፣ ዘንድሮም አርቲስት መሠረት መብራቴ የበጎ አምባሳደር ላደረገው የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል ድጋፍ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡

ከሩጫው ጎን ለጎንም በዋዜማው፣ በየዓመቱ የሚሰናዳው የአፍሪካ ኢምፓክት ሽልማት የተከናወነ ሲሆን፣ ሽልማቱ በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ወይም ለትውልድ አገራቸው በስፖርቱ፣ በኪነ ጥበብና በሥራ ፈጠራ መስኮች የጎላ አስተዋጽኦ ላደረጉ አፍሪካውያንና የአፍሪካውያን ቤተሰቦች ሽልማት የሚሰጥበት ነው፡፡

በዚህም ዓመት ጥሩነሽ ዲባባና አፍሪካዊ አቀንቃኝ ኤኮን ከተሸላሚዎቹ መካከል ናቸው፡፡ በመጀመሪያው የሽልማት ዝግጀት ድምፃዊው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና ደራርቱ ቱሉ ተሸላሚ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

በዝግጅቱ ላይ አምባሳደሮች፣ የዋሽንግተን ዲሲና የሜሪላንድ ግዛት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተገኙ ሲሆን፣ የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባና የሜሪላንድ ግዛት ሞንተገመሪ ክልል ለተሸላሚዎቹ ከፍተኛውን የዕውቅና ሽልማት ማበረከታቸውን ጋሻው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በዋሽንግተን የአፍሪካ ኅብረት ጽሕፈት ቤት ዋና ተጠሪ የሆኑት ሂልዳ ሱካ ማፉደዝ ሽልማቱን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፣ ተሸላሚዎቹ ለአፍሪካ ወጣቶች በአርዓያነትና ተግቶ በመሥራት ዙሪያ ያበረከቱት ሚና የጎላና ዕውቅናውም ትርጉም ያለው ነው ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...