Friday, December 9, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየኮቪድ-19 ክትባት በክፍያ ሊጀመር ነው

  የኮቪድ-19 ክትባት በክፍያ ሊጀመር ነው

  ቀን:

  ሁለት ሚሊዮን ዶዝ የሳይኖፋርም ክትባት ለሽያጭ ይቀርባል

   

  ሜዲቴክ ኢትዮጵያ ከቻይናው ግዙፍ የክትባት አምራች ሳይኖፋርም የገዛውን ሁለት ሚሊዮን ዶዝ ክትባት፣ በዋሽንግተን የሕክምና ማዕከል አማካይነት ለሽያጭ ሊያቀርብ መሆኑን አስታወቀ፡፡

  በመጀመርያው ዙር 200,000 የሳይኖፋርም ክትባት ወደ አገር ውስጥ መግባቱን አስመልክተው በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ የሰጡት ሜዴቴክ ኢትዮጵያና ዋሽንግተን የሕክምና ማዕከል ሒደቱ የክትባት አቅርቦትና ተደራሽነት ለማሻሻል ያግዛል ብለዋል፡፡

  የሜዲቴክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሐመድ ኑሪ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ ከቻይና የመጣን ክትባት ከዋሽንግተን የሕክምና ማዕከል ጋር በመተባበር የቀረበ ሲሆን፣ በጤና ሚኒስቴር ዕውቅናም አግኝተዋል፡፡

  ከመድኃኒትና ቁጥጥር ባለሥልጣን ደግሞ ከውጭ የማስገባት ፈቃድ ማግኘታቸውን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

  ባለፉት ስድስት ወራት የኮቪድ-19 ክትባት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ጥረት ማድረጋቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ከብዙ ጥረት በኋላ መሳካቱን አስረድተዋል፡፡ ከዋሽንግተን የሕክምና ማዕከል ጋር የግሉን ዘርፍ ከግል ዘርፍ ለማስተሳሰር ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም አክለዋል፡፡

  የኮቪድ-19 የክትባት በመንግሥት የነፃ እየተሰጠ መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር መሐመድ፣ በእነሱ በኩል የሚሰጠው ክትባት ደግሞ በሽያጭ በአማራጭነት ቀርቧል ብለዋል፡፡

  የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መከላከል የሚቻለው አብዛኛው ማኅበረሰብ ክትባቱን ከወሰደ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በሽያጭ የሚቀርበው ደግሞ በመንግሥት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

  የክትባት ቱሪዝም (Vaccine Tourism) የሚል አዲስ አሠራር መዘርጋቱን፣ ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ከውጭ የሚመጡ ተጓዦችና ክትባቱን ፈልገው ለሚመጡ ዜጎች በአዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ቅጥር ግቢ ውስጥ የዋሽንግተን የሕክምና ማዕከል በዶላር እንዲከተቡ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

  ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንዳስረዱት፣ የኮቪድ 19ን አስቸጋሪ ሁኔታ ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር፣ ለኢትዮጵያ የወጭ ምንዛሪ እንዲያመጣ በክትባት ቱሪዝም ለመሥራት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

  የዋሽንግተን ሕክምና ማዕከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርቆስ ፈለቀ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ማዕከሉ ኮቪድ-19 ምርመራና ሕክምና ካደረገው አስተዋጽኦ በተጨማሪ ባሉት የተደራጁ ማዕከላት ከሜዲቴክ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ክትባቱን ይሰጣል ብለዋል፡፡

  ማዕከሉ በሚያደርገው ትምህርትና ቅስቀሳ የክትባቱን ተቀባይነት ለመጨመር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ዘመናዊ የክትባት የምስክር ወረቀት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

  የክትባቱ አገልግሎት የቦሌ ኤርፖርትን ጨምሮ በተለያዩ የዋሽንግተን የሕክምና ማዕከል ይሰጣል ተብሏል፡፡

  በሽያጭ ይቀርባል የተባለው የሳይኖፋርም የኮቪድ-19 ክትባት ዋጋው ተመጣጣኝና የኅብረተሰቡን የመክፈል አቅም ከግንዛቤ ያስገባ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...