Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልኢትዮጵያዊነት በሕዝቦቿ ብዝኃነት እንዴትነት

ኢትዮጵያዊነት በሕዝቦቿ ብዝኃነት እንዴትነት

ቀን:

ኢትዮጵያ በሐውርታዊት አገር መሆኗ ይታወቃል፡፡ ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦችን በጉያዋ አቅፋለች፡፡ የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ሃይማኖቶች፣ ባህሎች ትውፊቶችና ልማዶችንም አሰባስባ ይዛለች፡፡ ኅብረ ብሔራዊት አገር፣ ልሳነ ብዙኃን አገር የሚለው አገላለጽም መለያዋ ነው፡፡

 

ይህ ሁሉ ሆኖ በየዓረፍተ ዘመኑ ከጥንተ እስከ ዛሬ ልዩ ልዩ ግጭቶች አልፎም እስከ ጦርነት የደረሱ ገጽታዎች መፈጠራቸው አልቀረም፡፡ በልዩ ልዩ ምክንያቶች የተፈጠሩ ግጭቶችን ለማስቆም በየብሔረሰቦቹ የባህላዊ ግጭት አፈታት መንገድ ሲከናወን ኖሯል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩት ግጭቶች መፍትሔ በማፈላለግ ረገድ ሃይማኖቶችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ጥረቶች ማድረጋቸው አልቀረም፡፡

ከወራት በፊት የካፑቺን ፍራንስቸስካዊ የፍልስፍናና የነገረ መለኮት ተቋም ‹‹የብሔር ብዝኃነት፣ ብጥብጥና የግጭት አፈታት በኢትዮጵያ›› (Ethnic Diversities, Violence and Conflict Resolution in Ethiopia) በሚል ርዕስ ሲምፖዚየም አዘጋጅቶ ነበር፡፡

የፍልስፍና፣ የሃይማኖት፣ የሕግ፣ የሥነ ምግባርና የሌሎች ዘርፎች ምሁራን ያቀረቧቸው ጥናታዊ ጽሑፎች ለኅብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግም እንዲታተሙ ተደርጓል፡፡ ሰሞኑን በካቶሊካዊው ተቋም በተዘጋጀ መርሐ ግብር መድበሉ ተመርቋል፡፡

በመድረኩ ላይ ስለ መድበሉ ይዘት ማብራሪያ የሰጡት የአፍሪካ የፍልስፍና መምህሩ ዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የብሔር ግጭትና ተግዳሮቶች ለአብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ የዕለት ተዕለት የሕይወት ልምድ እየሆነ በመምጣቱ፣ አሳሳቢነቱን የሚዳሰስ ጥናትና ርዕሱንም በመቅረፅ በጉባዔው 12 ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል።

መሪ ርዕሱ የዳስሰውም የብሔር ብዝኃነትና የግጭት አፈታት ከመጽሐፍ ቅዱስ፣ ከፍልስፍና፣ ከሥነ ልቡና፣ ከማኅበራዊና ፖለቲካዊ፣ ከሥነ ምግባርና ሕግ፣ ከመንፈሳዊ፣ ከወንጌል ተልዕኮና ከሥነ መለኮት ዕይታ አኳያ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡   

የመድበሉ ተቀዳሚ ዓላማ ለብዙኃነትና በተለይም ወጣቱ ትውልድን ከአደገኛ የዘርና ከፋፋይ አስተሳሰብ ለመታደግ፣ ከጥፋት መንገድ ለመከላከል፣ ከስሜታዊነትና ከበቀለኝነት የፀዳ አመለካከት እንዲያዳብሩ ማገዝ ነው፡፡ በአዕምሮውና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ምክንያታዊ ትውልድ እንዲፈጠር አስተዋጽኦ ስለሚያደረግ መድበሉ ታትሟል ብለዋል፡፡  

መምህሩ በመድበሉ የተካተቱት ጥናቶችን በየፈርጁ እንደሚከተለው አስቀምጠዋቸዋል፡፡

ኢትዮጵያዊነት በሕዝቦቿ ብዝኃነት እንዴትነት

የብሔር ማንነት ተፈጥሯዊ ስለመሆኑ

ማንኛውም ግለሰብ የዚህ ብሔር ወይም የሌላኛው የመሆን ውሳኔ ሰጪነት የለውም፡፡ ይህ ማለት የብሔር ማንነት ተፈጥሯዊ (Ontological) ወይም በተፈጥሮ የሚገኝ ፀጋ እንጂ የግለሰቡ ምርጫ አይደለም። ብሔር ቀርቶ ጾታና ቀለም የግለሰቡ ምርጫ አይደሉም። ተፈጥሮ የለገሰችንን ማንነት ማስወገድ አንችልም፡፡ ፍላጎቱ ቢኖረን እንኳ ከተፈጥሮ ጋራ መጣላት ይሆናል፡፡ ስለዚህም የብሔር ማንነት ምንም ስህተት የሌለበትና ጥሩም ሆነ መጥፎም ያልሆነ ነው፡፡ ብሔር በራሱ መልካም አሊያም መጥፎ አይደለምና። ይሁን እንጂ፣ ሁላችንንም ሊያሳስበን የሚገባው ብሔርን መልካም ወይም መጥፎ የሚያስብለውን የግለሰቡ ወይም የማኅበረሰቡ አረዳድና የሥነ ልቡና አቀራረፅን መገንዘቡ ላይ ነው። ምክንያቱም አዎንታዊ ብሔርተኝነት አገር ገንቢ ሲሆን አሉታዊ ብሔርተኝነት ደግሞ አገር አፍራሽ ነውና። መቼም ቢሆን የብሔር ወይም የባህል ልዩነቶች የበላይነትም ሆነ የበታችነት ትርጉም ሊሰጡ አይገባም። ለምሳሌ፣ አንድን ብሔር ከሌላው ከፍ አድርጎ ት፣ የመነጠል፣ የጅምላ ፍረጃ፣ ከሰው ደረጃ ማሳነስወዘተ. አሉታዊ ብሔርተኝነት ሲሆኑ እንደ አገር አፍራሽ ይታያሉ፡፡ ስለዚህ፣ የችግሩ ፍሬ ጉዳዩ የብሔር ግጭት በተፈጥሮ የተሰጠን ብሔር ራሱ ሳይሆን፣ አሉታዊ ብሔርተኝነት መሆኑ በአጽንኦት ተሰምሮበታል፡፡

ብዝኃነት የተፈጥሮ ሕግ ነው

ብዝኃነት ማንም ሰው ክደው የማይችለው የተፈጥሮ ሕግ ነው። የተለያዩ የባህል ልዩነቶች መኖራቸው በራሳቸው ችግር ሆኑ አይችሉም፡፡ ችግር የሚሆነው ዕውቅና ያለመስጠት ጉዳይ ነው። በተለይ በኢትዮጵያ የባህል ልዩነትን እንደሌለ አድርጎ መመልከት በጣም ስህተት ነው የሚሆነው የባህልና የቋንቋ ልዩነት የማኅበራዊ ሕይወታችን አንዱ አካል አንደመሆኑ መጠን እንደ ችግር ወይም ሥጋት መታየት የለበትም። በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ወጥ ባህል (ማለትም አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ የታሪክ አረዳድ፣ አንድ ሐሳብወዘተ.) ለማስረፅ መሞከር በጣም የተሳሳተና ተቀባይነት የሌለው አመለካከት ነው። ስለዚህ፣ ኢትዮጵያዊነት በሕዝቦቿ ብዝኃነት ላይ የተገነባ መሆን ይኖርበታል።

ጥልቅ አንድነትን በልዩነት የሚያከብር ኢትዮጵያዊነት

የባህል ብዝኃነት ኢትዮጵያዊ ብሔተኝነትን አይቃረንም። የጋራ ኢትዮጵያዊነት ስሜት መፍጠር የሚቻለው ሁሉን የሚያካትትና በጋራ ጥቅም ላይ የፀና የወል ተቋማትን መመሥረትና ሁሉን አሳታፊና እኩልነትን የሚያከብር መዋቅር መዘርጋት ሲቻል ነው። የባህል ብዝኃነት የኢትዮጵያ አንድነ በተሳትፎ የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ በተቃራኒው የራስን የብሔር የበላይነት ብቻ ጉላት ኢትዮጵያዊ ብሔተኝነትን የሚንድ ነው። የአገር ፍቅር ዕውን ሊሆን የሚችለው ጥልቅ አንድነትን በልዩነት የሚያከብር ኢትዮጵያዊነትን መፍጠር ሲቻል ብቻ ነው። ኢትየጵያዊነትም ሆነ የባህል ብዝኃነት የምንደሰትበት ውበታችን መሆን ይገባል።    

ክርስ ከብዝኃነት በላይ ነው

ማንም ሰው ክርስቲያን ስለሆነ ብቻ የብሔር ማንነቱን መቀየር አይቻለውም፡፡ ምክንቱም ክርስቲያን በሚኮንበት ጊዜ የባህል ማንነቶች ጨርሰው አይጠፉምና ነው። ይሁን እን የወን ቶች ከማንኛውም የባህል ብዝኃነት በላይ የመሆኑ እውነታ መቼም ቢሆን ጥያቄ ውስጥ መግባት የለበትም፡፡ የክርስ ጥሪ ክርስቲያን ከመኮኑ በፊት ከተያዘው ማንነት በላይ ነው። እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ የራሱን ቡድን (ብሔር) በተለየ መልክ ወንድሞቹ/እህቶቹ አድርጎ በመመልከት፣ ሌላውን እንደ ጠላት/መጤ/እንግዳ አይመለከትም። ይልቁንም ለሰው ልጅ ክብር የምሰጠው ሰው ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው የተፈጠረው በፈጣሪው ‹‹መልክና አምሳያ›› ነውና። ከሁሉ በላይ፣ በክርስ አስተም ሁሉም ሰው በክርስቶስ አንድ መሆኑንና ቤተ ክርስቲያንም በጾታ፣ በቀለም፣ በሃይማኖት፣ በብሔርና በመደብ ፈጽሞ ልትገደብ እንደማይቻላት ነው።

አፍካዊነት በሌሎች ሰዎች ውስጥ መገኘት

የአፍሪካ ባህላዊ ሥርዓት እንደሚያሳየው አንድ ሰው ሰው መሆኑን የሚያውቀው በሌሎች ሰዎች ውስጥ ሲገኝ ነው። እርስ በርስ መካባበር፣ መስማማት፣ ግለኝነትን ማስወገድና መልካም ምግባርን ማጎልበት የሚማረውም አገር በቀል በሆነው በዚህ ባህላዊ ሥርዓት ውስጥ መሆኑ ግልጽ ነው። አንድ ሰው እነህን ባህላዊ ቶች በማጎልበትና በማበልፀግ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የብሔር ጭት መፍታት እንደሚችል ማስታወስ እጅጉን አስፈላጊ ነው። ከሁሉም በላይ፣ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዎችን ከወን እሴቶች ጋር በማዋሀድ እውነተኛ ዕርቅ ማድረግና ዘላቂ ሰላም በኢትዮጵያ ማስፈን እንደሚቻል ለአንድ አፍታም ቢሆን መዘንጋት የለበትም።

ነፃነትና ግዴታ የማይነጣጠሉ እውነታዎች

የሰው ልጅ ዕድገት በየትኛውም ማኅበረሰብ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ለክብሩ ዕውቅና ሲሰጠውና መብትና ግዴታውም በትክክል የተዛመደ ሲሆን ብቻ ነው። ማንም ሰው ሌላውን በእኩል ደረጃ ማስተናገድ የሚችለው የራሱን መብት በመጠየቅ ብቻ ሳይሆን የሌላውን መብት የመጠበቅ ግዴታውን ወጣ ነው። ነፃነት ማለት የፈለጉትን ነገር ማድረግ (መናገር) ማለት ሳይሆን፣ በማኅበረሰቡና በተፈጥሮ በኩል ያለውን ግዴታ በትክክል መረዳት ነው። ያለ ግዴታ ነፃነት ምንም ትርጉም የለውም። አብዛኛውን ጊዜ የብሔር ግጭቶች የሚገናኙት በመብትና ግዴታ መካከል የጠነከረ ግንኙነት ባለመኖሩ ምክንያት ነው።

የካህናትና የመንፈሳዊ አገልጋዮች ሚና

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ካህናትና መንፈሳዊ አገልጋዮች በግጭት አፈታት ውስጥ ዘላቂ መፍትሔ በማስገኘት ኅብረት፣ ሰላምና ፍትሕ እንዲሰፍን የበኩላቸውን ሚና እንጫወቱ ጉባዔው በጥብቅ ያሳሰበበት ነው። ለዚህም ደግሞ ራሳቸውን በምሳሌነትና በአርዓያነት በመኖርና የሚያስተምሩትን ነገር በተግባር በማሳየት ለዕርቅና ለሰላም አጥብቆ መሥራት ይጠበቅባቸዋል። እውነተኛ የቤተ ክርቲያን አገልጋይ ከክርስቲያናዊ ሥነ ግባር ጋር ቃረን መልኩ ብሔርን መሠረት ያደረገ አግላይነትን ፈጽሞ መፈጸም የለበትም።           

‹‹ዕርቅ ማድረግ የፖለቲካ፣ የሥነ ልቡናዊ ወይም ያመራር ዘዴዎች ክዋኔ (ውጤት) ብቻ ማለት አይደለም፡፡ መንፈሳዊ ስፋትና ጥልቀት ያለውና የእያንዳንዱን ግንኙነት የሚነካ ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ትርጉም ከኃጢዓት መፈወስንና የሰው ልጅ ወደ ቀደመው ሙሉ ሰብዕናው መመለስ ማለት ነው፤›› የሚሉት ብጥብጥና የግጭት አፈታት ከሥነ ምግባር አኳያ የተመለከቱት አባ ተስፋዬ ወልደማርያም ናቸው፡፡

በክርስቲያን ልብ ውስጥ በግጭት አፈታትና በዕርቅ ሒደት መሳተፍ የእምነቱ መሠረታዊ አስተሳሰብና ሰዎች ከመጥፎ/እርኩስ መንፈስ ነፃ የሚወጡበት፣ ይቅርታን የሚያገኙበት፣ ተሐድሶና የእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ ሆነው ሥርዓት ውስጥ የሚገኙበት ማለት ነው ሲሉም አብራርተዋል፡፡

እንደ አባ ተስፋዬ ማስገንዘቢያ፣ ኢትዮጵያ ታላቅ አገር ናት፡፡ የተለያየ የአየር የአየር ንብረት እናይባታለን፡፡ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች ይነገሩበታል፡፡ የተለያዩ ባህላዊ አልባሳት፣ የበዓላት አከባበር፣ የእምነትና የሃይማኖት ሥርዓቶች ያለባትም አገር ነች፡፡ እነዚህ ሁሉ ብዝኃነት ኑረው እንኳ በኢትዮጵያውያን ውስጥ የኅብረትና የአንድነት ስሜት አልተለየም፡፡ በኅብረት ውስጥ አንድነትን የሚያስተምር እንጂ በልዩነት የሚያራርቅ አልሆነም፡፡

‹‹የተለያየን ልንሆን እንችላለን፤ ነገር ግን ጥብቅ ጓደኛሞች፣ ወንድማሞች ነን፡፡ አንዳችን ሌላውን በመደገፍ አብሮ ለጋራ ዓላማ እንሠራለን፡፡ እንግዲህ ልንደመድም የምንችለው ኢትዮጵያ በኅብረት ውስጥ ብዝኃነትን የያዘች መሬት መሆኗን ነው፤›› ሲሉም አስምረውበታል፡፡

‹‹እንደሁሉም ዜጎቿ ምኞትና ፍላጎት ሕይወታቸው የተሟላ እንዲሆን ማድረግና መፍጠር ከቻልን በርግጥ ኢትዮጵያን ትልቅ አገር መሆን ትችላለች፤›› ሲሉም ቋጭተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...