Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ የመጣው በኮቪድ-19 የሚሞቱት ቁጥር

በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ የመጣው በኮቪድ-19 የሚሞቱት ቁጥር

ቀን:

  • በአንድ ሳምንት ከ200 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል

‹‹አሁንም እንጠንቀቅ›› እያለ ሳያሠልስ ማሳሰቢያ እየሰጠ ያለው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ-19 ሥርጭት፣ ከመስፋፋቱ ባለፈ ሕይወታቸውን እያጡ ያሉት ወገኖች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል፡፡ በበሽታው የሚያዙ፣ በፅኑ የሚታመሙ ቁጥር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ በከፍተኛ መጠን እየጨመረም ይገኛል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ምክትል ኃላፊ ሚኪያስ ተፈሪ (ዶ/ር) ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጡት የጋዜጣ መግለጫ ላይ እንዳመለከቱት፣ ወረርሽኙ ለረዥም ወራት ከመቆየቱ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ መሰላቸት ምክንያት በኅብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለው የመከላከያ መንገዶችን የመተግበር እንዲሁም የመከላከያ ክትባት ለመውሰድ የታየው ዳተኝነት የወረርሽኙን ሁኔታ እጅግ አሳሳቢና አስደንጋጭ አድርጎታል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ ከጥቅምት 1 እስከ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ከተመረመሩት 52‚424 ሰዎች መካከል 4‚771 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፣ የመያዝ ምጣኔም ዘጠኝ በመቶ ሆኗል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በአገር አቀፍ ደረጃ 227 ሰዎች በበሽታው ምክንያት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ምክትል ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹ይህም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 98፣ በኦሮሚያ 8፣ በሲዳማ ክልል 8፣ በደቡብ ክልል 10፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 10፣ በሶማሊያ ክልል 20፣ በሐረሪ ክልል ሁለት እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አንድ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፡፡ በአሁኑ ጊዜ 1‚202 ሰዎች በሕክምና ማዕከል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል 600 የሚሆኑት ታካሚዎች ወደ ፅኑ ሕክምና ገብተው የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ፡፡›› ብለዋል፡፡

ከምክትል ኃላፊ ማብራሪያ ለመረዳት እንደሚቻለው፣ በአገራችን በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የበሽታው ሥርጭት መኖሩንና አሁንም የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን አዘውትሮ መተግበርና እንዲሁም የመከላከያ ክትባቱን ሳይዘገዩ መውሰድ ሊከሰት የሚችለውን የሕመም ሥቃይንና ሞትን መከላከል እንደሚገባ ያሳያል፡፡

የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን ሲባል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ፣ እጅ መታጠብና ርቀትን መጠበቅ እንዲሁም ክትባቱን መውሰድ ላይ የኅብረተሰቡ ቁርጠኝነት ያነሰ መሆኑ ችግሩን አሳሳቢና ውስብስብ እንዳደረገው ምክትል ኃላፊው ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

በመሆኑም በተደጋጋሚ ጊዜ ለመግለጽና ለማስታወቅ እንደተሞከረው፣ አሁንም የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከልና የሚያስከትለውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሰባዊ ቀውስን ለማስቆም መከላከያ ዘዴዎች ላይ ሁሉም ልዩ ትኩረት በመስጠት ተግባራዊ ማድረግ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከመከላከያ ዘዴዎች መካከልም መመርያ 803/2013 ዓ.ም. ተግባራዊነት ላይ በየደረጃው የሚገኝ ኃላፊነት የተጣለበት ግብረ ኃይል አመራሮች፣ የፀጥታ አካላትና ማኅበረሰቡ ትኩረት መስጠት፣ በየደረጃው የሚገኝ አመራር በኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች ትግበራ ላይ ለማኅበረሰቡ አርዓያ መሆን፣ ሚዲያዎች ተገቢውን የአየር ሰዓት በመስጠት ለኅበረተሰቡ ወቅታዊ መረጃዎችን ማድረስና በሕዝባዊ ሃይማኖት በዓላት የሚፈጠሩ መሰባሰቦችን ማስቀረት የሚሉት እንደሚገኙባቸው ነው ያመለከቱት፡፡

ከዚህም ሌላ የመንግሥት የሕዝብና የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን እንዲተገብሩ፣ የኮቪድ-19 ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አፋጣኝ ምርመራ ማድረግ፣ ሁሉም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነው የማኅበረሰቡ ክፍል የኮቪድ-19 ክትባትን በመንግሥት ጤና ተቋማት በመሄድ መውሰድ፣ ትምህርት ቤቶች በመክፈት ላይ በመሆናቸው ሁሉም ትምህርት ቤቶች የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች መተግበራቸውን መከታተል ይገባቸዋል፡፡ ለዚህም አስተማሪዎች፣ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ክትትልና ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል የሚሉት ነጥቦችም ከመከላከያ ዘዴዎች ተጠቃሽነት እንደሆኑ ነው ሚኪያስ ተፈሪ (ዶ/ር) የገለጹት፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ዓይነት ክትባቶች እንዳሉ ከእነዚህም መካከል አንደኛው ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ሲሆን፣ ሁለተኛውና ሦስተኛው በየቅደም ተከተላቸው መሠረት ሲኖ ፋርምና አስትራዜኒካ እንደሚባሉ ገልጸው፣ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተባለው ክትባት አንድ ጊዜ ብቻ፣ የቀሩት ሁለቱ ክትባቶች ግን እያንዳንዳቸውን ሁለቴ መውሰድ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...