Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበደሴ ከተማ የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር አሳሳቢ መሆኑ ተጠቆመ

በደሴ ከተማ የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር አሳሳቢ መሆኑ ተጠቆመ

ቀን:

በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን የደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሁኔታ የተረጋጋ ሁኔታ ላይ ቢገኝም፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር አሳሳቢ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

 

የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል ለሪፖርተር እንዳስረዱት፣ የክልሉም ሆነ የከተማው ነዋሪዎች በዚህ ወቅት በህልውና ዘመቻ ውስጥ እየተሳተፉ ነው፡፡ በዚህ ወቅት የተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች በአሸባሪነት ከተፈረጀው ኃይል ነፃ እየወጡ እንደሚገኙ፣ የደሴ ከተማን ፀጥታ ለማጠናከርም በርካታ ዕቅዶችን በማዘጋጀት ወደ ሥራ እንደተገባ ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከዕቅዱ መካከል የፀጥታ፣ የሎጂስቲክስ፣ የሞቢላይዜሽንና የመሳሰሉት ተጠቃሾቹ እንደሆነ ያስታወቁት ከንቲባው፣ ኅብረተሰቡ በደንብ የሚያውቀውን የፀጥታ ኃይል በመፍጠርና ሕዝባዊ ኃይል በማድረግ ጠላትን የመመከትና የማጥፋት ሰፊ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በደሴ ከተማ ላይ ካለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ በአሸባሪው ቡድን ልሳኖች  የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሲሠራጭ እንደነበር ያስታወቁት አቶ አበበ፣ ዓላማውም “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” የሚለው ዓይነት ይዘት ያለው እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ የፕሮፓጋንዳው ዋነኛ ዓላማ ሕዝብን ማሸበር፣ ማስጨነቅና ባልተገባ ሁኔታ ችግር የሚፈጠርበትን የሁከት ሥራ ለመፍጠር የሚደረግ እንቅስቃሴ እንደሆነ ከንቲባው ገልጸዋል፡፡ ይህን ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ አመራር ተባብሮ ሌት ከቀን እየሠራ ይገኛል ብለው፣ የከተማዋ ሰላም ግን የተጠበቀ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

የሐሰት ፕሮፓጋንዳዎችን  ማሠራጨት  በስፋት የሚስተዋል ችግር እንደሆነ ያስታወቁት አቶ አበበ፣ ኅብረተሰቡ ከአገር መካለከያ ሠራዊት፣ ከልዩ ኃይልና ከሚሊሻ ጋር በመተባበር ጠንካራ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙና የደሴ ከተማ እንቅስቃሴ ፍፁም ሰላማዊ በመሆኑ፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንቅስቃሴም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንደ ቀጠለ አስረድተዋል፡፡

የፀጥታ መዋቅሩ የራሱ የሆነ የሥራ ሥምሪት አለው ያሉት አቶ አበበ፣ ከዚህም ውስጥ የፀጉረ ልውጦችን እንቅስቃሴ መከታተል አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ ውስጥ የአንዳንድ ፀጉረ ለውጦች እንቅስቃሴ እንደሚስተዋል የገለጹት ከንቲባው፣ ካለፈው ሳምንት የሬዲዮ መገናኛ መሣሪያዎች ከሰርጎ ገቦች ጋር እንደተያዙ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከሌላ አካባቢ የመጡ በርካታ የዘረፋ ቡድኖች በከተማዋ ውስጥ የዝርፊያ ሙከራዎችን ሲያደርጉ በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ተገልጿል፡፡ መኪኖች መዝረፍ፣ የፎርጅድ የሚሠሩባቸውን ማቴርያሎች ጨምሮ ገንዘብ፣ የትምህርት ማስረጃ፣ መታወቂያና የመሳሰሉትን በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነግሯል፡፡

በኬላ፣ በሆቴሎች፣ ቤት ተከራይተው ጥቆማ የሚቀርብባቸው ፀጉረ ልውጦች ላይ ራሱን ችሎ በተቋቋመ አንድ የኦፕሬሽን ቡድን ማጣራት እየተደረገ ነው ያሉት አቶ አበበ፣ የኦፕሬሽን ቡድኑ የሚደርሱ ጥቆማዎችን እግር በእግር በመከታተልና መረጃዎችን በመሰብሰብ መሰል ነገሮችን ለማወቅ ጥረቶች እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ 

በደሴ ከተማ በየጊዜው የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝ የገለጹት ከንቲባው፣ የጥፋት ቡድኑ ጨካኝ በመሆኑ ኢትዮጵያዊነት በማይታይበት ጭካኔ ሕዝቡ ደሴን ከሚያዋስኗት የተለያዩ ከተሞች እየተፈናቀለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጦርነት ባልተከናወነባቸው ቦታዎች ጭምር በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ኅብረተሰቡ ከቀዬው እንዲፈናቀል ተደርጓል ያሉት ከንቲባው፣ በዚህም የተፈናቃዮች ቁጥር ከአቅም በላይ እየሆነ ነው ብለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከተማው ውስጥ የመረበሽ ዝንባሌዎች ይታያሉ ያሉት አቶ አበበ፣ ከፀጥታ ቁጥጥሩ ባለፈ የዕርዳታ አቅርቦት ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዕገዛዎች ያስፈልጋሉ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በደሴ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች ከዕርዳታ ባሻገር የጤና አገልግሎቶችን በአግባቡ እንዲያገኙ ለማድረግ በሁሉም የጤና ጣቢያዎች የሕክምና ባለሙያዎች የተመደቡ መሆናቸውን፣ ከአቅም በላይ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ተፈናቃዮቹ በሚገኙበት አካባቢ ባሉ የጤና ተቋማት የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የጋራ መግባባት ተደርሶ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡

ከደሴ ወደ አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ቦረና፣ እንዲሁም ወደ ሌሎች ከተሞች የሚወስዱ መንገዶች ክፍት እንደሆኑ የተናገሩት አቶ አበበ፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴም ያልተቋረጠ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...