Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየብሔራዊ ምክክር መድረክ ተሳትፎ በተሳታፊዎች እንደሚወሰን ተገለጸ

የብሔራዊ ምክክር መድረክ ተሳትፎ በተሳታፊዎች እንደሚወሰን ተገለጸ

ቀን:

በቅርቡ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ የምክክር መድረክ ላይ የሚሳተፉ አካላት የሚወሰነው በተሳታፊዎች በራሳቸው እንደሚሆን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት የእሑድ ዕትሙ ሁሉን አቀፍ የሆነው ብሔራዊ የምክክር መድረክ በመጪው ኅዳር ወር 2014 ዓ.ም. እንደሚጀመርና ሁሉን አቀፍ በሆነው በዚህ የምክክር መድረክ ላይ በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሳተፉበት መድረኩን እያመቻቸ ከሚገኘው ማይንድ ኢትዮጵያ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ብሔራዊ የምክክር መድረኩን በበላይነት የሚያስተባብረው የሰላም ሚኒስቴር ለሪፖርተር በላከው ማብራሪያ ግን በኅዳር ወር የሚካሄደው ዋናው ብሔራዊ የምክክር መድረክ ሳይሆን ስለመድረኩ ሕዝባዊ ግንዛቤ መፍጠሪያና ማሳወቂያ ውይይት እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በዚህ የማስተዋወቂያ ፕሮግራም ላይ የሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎችንና ተቋማትን ለሚወክሉ ጥሪ እየተደረገ መሆኑንና እስካሁን ጥሪ ያልደረሳቸው ካሉም በድጋሚ የሚታይ እንደሆነ የሰላም ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡

ዋናው ብሔራዊ የምክክር መድረክ መቼ እንደሚካሄድ የሰላም ሚኒስቴር ባይገልጽም፣ በመድረኩ ላይ የሚሳተፉ አካላት የሚወሰነው ግን በራሳቸው በተሳታፊዎቹ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...