Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትከአራት ቢሊዮን ወደ ስምንት ቢሊዮን ብር ያሻቀበው የብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ በጀትና የጠቅላይ...

ከአራት ቢሊዮን ወደ ስምንት ቢሊዮን ብር ያሻቀበው የብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ በጀትና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት 

ቀን:

ከስድስት ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ አራት ቢሊዮን ብር በጀት ወጥቶለት ግንባታው የተጀመረው ብሔራዊ ስታዲየም የግንባታው ወጪ በእጥፍ ጨምሮ አሁን ላይ እስከ ስምንት ቢሊዮን ብር የሚጠይቅ መሆኑ ተነገረ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የብሔራዊ ስታዲየሙ የግንባታ ሒደት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ የሥራ መመርያም ሰጥተዋል፡፡

በቀድሞ ስፖርት ኮሚሽን ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተለቀቀው መግለጫ እንደሚያስረዳው ከሆነ፣ የስታዲየሙ ግንባታ ከሚጠበቀው ጊዜ በላይ መጓተቱ፣ ለዚህ ደግሞ በዋናነት የውጭ ምንዛሪ እጥረት መሆኑ በአማካሪ ድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር መሰለ ኃይሌ (ዶ/ር) እና የግንባታውን ሒደት በሚከታተሉት አቶ አስመራ ግዛው አማካይነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

ከገለጻው በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት ስታዲየሙ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ፍላጎት ያለው መሆኑ፣ ያጋጠሙ ችግሮችን በአፋጣኝ እንደሚፈታ መግለጻቸውን ያስረዳው መግለጫ፣ ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅና ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን የሥራ መመርያ ሰጥተዋል ብሏል፡፡

 መግለጫው ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተገናኘ በዝርዝር ያለው ነገር ባይኖርም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንባታውን የሚከታተለው የመንግሥት አካልና የአማካሪ ድርጅቱ ኃላፊዎች በተለይ ከውጭ ምንዛሪ እጥረት ጋር በተገናኘ ወደሚመለከተው የመንግሥት አካል በመሄድ ተነጋግረው ችግሩን እንዲፈቱ፣ የስታዲየሙ ግንባታ በአፋጣኝ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ እንደሰጡ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘው ብሔራዊ ስታዲየም በወንበር 62 ሺሕ ተመልካች የማስተናገድ አቅም ያለው ሲሆን፣ ከስድስት ዓመት በፊት በአራት ቢሊዮን ብር እንዲጠናቀቅ የተያዘው ዕቅድ ግንባታው በመጓተቱ ምክንያት አሁን ላይ ስምንት ቢሊዮን ብር የሚጠይቅ ስለመሆኑ ጭምር በመግለጫው ተካቷል፡፡

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ሲከበር ለነበረው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዓመታዊ ክብረ በዓል ዝግጅት በሚል፣ ከኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ውጪ በሌሎቹ ማለትም በአፋር፣ በሐረሪ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻጉል ጉሙዝ፣ በአማራ፣ በትግራይና በደቡብ ክልሎች ከ30 እስከ 60 ሺሕ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም ያላቸው ስታዲየሞች ግንባታ ተከናውኗል፡፡

የግንባታው ዓይነትና ደረጃ እንደ ክልሎቹ አቅምና ሁኔታ የሚወሰን መሆኑ ቢታመንም፣ ከባህር ዳር፣ ከሐዋሳና ከመቐለ ውጪ ያሉት ሁሉም ስታዲየሞች ለክብረ በዓሉ ሲባል ካልሆነ በስተቀር፣ ከበዓሉ በኋላ የስታዲየም ቅርፅና ይዘት እንዲኖራቸው የሚያስችል ግንባታ እንዳልተደረገላቸው የሚናገሩ አልጠፉም፡፡ 

በግንባታ ላይ የሚገኘውና መጠርያው አደይ አበባ የሆነው ብሔራዊ ስታዲየምን ጥቅምት 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ከጎበኙት መካከል፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሸመልስ አብዲሳና የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መስፍን ቸርነት ይገኙበታል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...