Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትምሩፅ ይፍጠርን ዳግም ያስቃኘ የለተሰንበት ግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን

ምሩፅ ይፍጠርን ዳግም ያስቃኘ የለተሰንበት ግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን

ቀን:

ከዘንድሮ የሻሌንሽያ ግማሽ ማራቶን ገድል በኋላ የኢትዮጵዊቷን ለተሰንበት ግደይ አዲስ ክብረ ወሰን ተከትሎ በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች አትሌቷን ለመግለጽ ቃላት ያጡላት ይመስላል። ከሙገሳው ባልተናነሰ የሰው ልጅ እንዴት በዚህ ፍጥነት

20 ኪሎ ሜትር ሊያጠናቅቅ ይችላል? በሚል ጥያቄን ደግመው ደጋግሞ ሲያነሱ ሰንብተዋል።

በርካቶች እሑድ ጥቅምት 14 ቀን 2014 .ም. በቫሌንሽያው ማራቶን ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉትን ፍጥጫ ሲጠብቁ ነበር። ውድድሩን ተጠባቂ ያደረገው የግማሽ ማራቶን የክብረ ወሰን ባለቤቷ የዓለም ዘርፍ የኋላና በርቀቱ ለመጀመርያ ጊዜ የምትካፈለው 5,000 እና 10,000 ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤቷ ለተሰንበት ግደይ በውድድሩ መካፈላቸው ነበር።

ቀደም ብሎ በርካታ አስተያየት ሲሰጥበት የሰነበተው ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላም በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል። ይሄም በርቀቱ ለመጀመርያ ጊዜ መካፈል የቻለችው ለተሰንበት የሰው ልጅ እንዴት በዚህ ፍጥነት ሊያጠናቅቅ ይችላል በሚያስብል  1:02.52 ድል ማድረጓን ተከትሎ ነበር።

ለተሰንበት ያጠናቀቀችበትን ሰዓት ተከትሎ በርካታ ሚዲያዎች፣ ባለሙያዎችና በአትሌቲክስ ጥናት የሚያደርጉ ተቋማት መረጃን እየጎለጎሉ፣ ትንታኔ በመስጠት ተጠምደዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞም የዓለም አትሌቲክስ የአትሌቷን ውጤት ተከትሎ በቀላሉ እንደማይታይና የሌሎች ርቀቶች የውጤት መመዘኛ ተደርጎ መወሰድ እንዳለበት አስተያየቱን ሰንዝሯል።

ለተሰንበት በአሯሯጮቿ ድጋፍ አማካይነት የመጀመርያውን አምስት ኪሎ ሜትር 15 ደቂቃ፣ 10 ኪሎ ሜትርን 29:45.15፣ ኪሎ ሜትርን 44:20 እንዲሁም 20 ኪሎ ሜትርን ለማጠናቀቅ 59:46 ደቂቃ ነው የወሰደባት።

ለማስታወሻነት በውድድሩ ዕለት የውድድሩን አዘጋጆችተወዳዳሪዎችን እያንዳንዱን ኪሎ ሜትር የሚመዘግብ መሣሪያ (Tracking Site) ያሰናዱ ቢሆንም፣ ውድድሩ  ከመጀመሩ ሦስት ሰዓት ቀደም ብሎ መጠጥ ጠጥቶ ሲያሽከረክር የነበረ ግለሰብ 20 ኪሎ ሜትር ላይ የተቀመጠውን መቆጣጠሪያ መግጨቱን ተከትሎ፣ የርቀቱን ሰዓት ማወቅ መቸገራቸውን አስታውሰዋል።

ሆኖም በጊዜው ማወቅ ባይቻልም፣ ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላ ሰዓቱን ማሳወቅችሏል። ለተሰንበት 15 ኪሎ ሜትሩን ለማጠናቀቅ 44:20 ደቂቃ የምንጊዜም ክብረ ወሰን ያደርገዋል። እንደ ሌትስ ረን ትንተና ከሆነ የርቀቶች መመዘኛ ይፋ የተደረገው ከዘመናዊ የመሮጫ ጫማዎች በፊት ቢሆን፣ ይሄ ሰዓት የምንጊዜም የስፖርት ምርጥ ሰዓት ሆኖ ሊመዘገብ እንደሚችል ያስቀምጣል።

ከዚህም ባሻገር አትሌቷ ክብረ ወሰኑን 70 ሰከንዶች በማሻሻል ..አ. ከ1978 በኋላ ሰፊው ሰዓት ያደርገዋል። ከውድድሩ ቀደም ብሎ ከጋዜጠኞች ርቀቱን በስንት ሰዓት ልታጠናቅቅ እንደምትችል ጥያቄ የቀረበላት ለተሰንበት 1:02.30 ልታጠናቅቅ እንደምትችል ተናግራ ነበር።

ምሩፅን ይፍጠር ሺፍተረንና ለተሰንበትን ምን አገናኛቸው?

የሞስኮ ኦሊምፒክ 5,000 እና 10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ምሩፅ ይፍጠር፣ የዚያን ዘመን ድንቅ አትሌት ነበር። ምሩፅ በረዥም ርቀቱ በርካታ ድሎችን መጎናፀፍ የቻለ አትሌት ነው።

ምሩፅ በ1969፣ 1971 እንዲሁም 1972 በፖርቶ ሪኮ ግማሽ ማራቶን የደመቀበት ጊዜ ነበር። እ.ኤ.አ. 1977 የወንዶች ግማሽ ማራቶን 1:02.57  በሆነ ሰዓት ክብረ ወሰን መጨበጥ ችሏል።

ታዲያ ለተሰንበትም ምሩፅ ከሮጠበትና የዓለም ክብረ ወሰን ካስመዘገበበት ግማሽ ማራቶን፣ ፍጥነት በላይ መሮጥ ችላለች። ከዚህም ባሻገር እ.ኤ.አ. 2003 እንግሊዛዊቷ ፓውላ ራድክሊፍ በግማሽ ማራቶን ይዛው የነበረውን 1:05.40 በሦስት ደቂቃ ማሻሻል የቻለችበት ውድድር ነበር። በዚህም ምክንያት አትሌቷ በተለያዩ ርቀቶች አዳዲስ ክብረ ወሰኖችን እያስመዘገበች በመምጣቷ በጥርጣሬ ዓይን እንድትታይ ማድረጉ አልቀረም፡፡

ከለተሰንበት ክብረ ወሰን በኋላ ምን ተባለ?

የተለያዩ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች በኋላ ለሚመዘገቡት አዳዲስ ክብረ ወሰኖች ጋር ተያይዞ፣ እንዴት ሊሆን ቻለ? የሚሉ ጥያቄዎች ይከተላሉ። ሁሉም የየራሱን ትንታኔ ሲሰጥ ይስተዋላል። አብዛኛውን ጊዜ አበረታች ቅመሞችን ተጠቅመው ነው የሚለው አስተያየት ሚዛን ይደፋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ አትሌቶች የሚጫሙት ጫማ እንደሆነ ይገለጻል። በእርግጥ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ትጥቅ አምራቾች በሚያቀርቧቸው ጫማዎች አማካይነት በርካታ አዳዲስ ክብረ ወሰኖች ተሰብረዋል።

የለተሰንበትን የቫሌንሺያውን የዓለም ክብረ ወሰን በኋላም ተመሳሳይ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል። ሆኖም አትሌቷ አበረታች ወስዳ ሊሆን ይችላል ከሚለውን ግምታዊ አስተያየት ባሸገር፣ እስካሁን በየትኛውም መንገድ ክስ ሲቀርብባት አልተስተዋለም።

በተለይ ከቅርብ ዓመታት በኋላ እየተመዘገቡና እየተሻሻሉ የመጡትን ክብረ ወሰኖች ተከትሎ፣ ዓለም አቀፍ የትጥቅ አምራቾች አትሌቶች የተጫሙት የመሮጫ ጫማና የሮጡበትን ሰዓት እያመዛዘኑ ይገኛሉ።

በዚህም መሠረት የጫማ መጠኑ 0.5 በመቶ የሆነ ግማሽ ማራቶን ርቀቱን (1:03.10)፣  1፡00 በመቶ የሆነ (1:03.30)፣ 1.5 በመቶ (1:03.49) እንዲሁም 2፡00 በመቶ የሆነ ጫማ የተጫማ አትሌት (1:04.08) በሆነ ሰዓት ርቀቱን ሊያጠናቅቁ እንደሚችሉ ያስቀምጣል።

ከዚህም ባሻገር አትሌቷ የተሳተፈችበት ውድድሮች በተመሳሳይ ሁኔታ በመገምገም፣ ‹‹አበረታች ቅመም ተጠቅማለች›› ከሚለው ይልቅ፣ አትሌቷ ‹‹የዘመኑ ድንቅ አትሌት ነች›› የሚለው ምስክርነት ሚዛን ደፍቷል።

በሌላ በኩል በሰሜን አየርላንድ ግማሽ ማራቶን በ1:04.00 ሰዓት ክብረ ወሰን መሰበር የቻለችው የዓለም ዘርፍ (በጊዜው ክብረ ወሰኑ ያልፀደቀ) በቫሌንሽያው 1:03.51 በማጠናቀቅ በዓመት ውሰጥ ያሻሻለችው ሁለተኛው ሰዓት ሆኖላታል። ኬንያዊቷ ሼይላ ችብኪሩ 1:04.54 በሆነ ሰዓት ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። በወንዶች አቤል ኪብቹምባ 58:48 በማጠናቀቅ በበላይነት አጠናቋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...