Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመንግሥት በትግራይ ክልል ለስድስተኛ ጊዜ የአየር ድብደባ ማካሄዱን አስታወቀ

መንግሥት በትግራይ ክልል ለስድስተኛ ጊዜ የአየር ድብደባ ማካሄዱን አስታወቀ

ቀን:

  • ተፈናቃዮች ወደ መሀል አካባቢዎች መጓጓዣ ትራንስፖርት ማጣታቸው ተጠቁሟል

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለስድስተኛ ጊዜ ባካሄደው የአየር ድብደባ ከመቀሌ ከተማ በትንሽ ኪሎ ሜትር ርቀት ኵሃ ከተማ አካባቢ የሚገኘውን፣ የትግራይ የልዩ ኃይል ፖሊስ ማሠልጠኛ ተቋም መምታቱን መንግሥት አስታወቀ፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ማክሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጠው መግለጫ፣ በአየር ኃይል የተደበደበው ማሠልጠኛው በርካታ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች እየሠለጠኑበት እንደነበር አስታውቋል፡፡

አየር ኃይሉ ጥቅምት 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ባደረገው ድብደባ በዓድዋ አካባቢ የሕወሓት ወታደራዊ ትጥቅና አልባሳትን አመሳስሎ የሚያመርትበትን ማዕከል፣ እንዲሁም በምዕራብ ግንባር ማይጠብሪ የሕወሓት ማሠልጠኛና የሰው ኃይል ማደራጃን መደብደቡ መገለጹ ይታወሳል፡፡

ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. የመጀመርያውን የአየር ድበደባ ያካሄደው አየር ኃይል፣ በመቀሌ የወታደራዊ ማሠልጠኛና ማዘዣ ማዕከልና የቀድሞ የመከላከያራዊት ማሠልጠኛ እንደነበረ ይታወሳል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ምንም እንኳ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የሕወሓት የወታራዊ ማሠልጠኛና የመሣሪያ ማከማቻ በሚላቸው በተመረጡ አካባቢዎች የአየር ድበደባ ቢያካሂድም፣ በአማራ ክልል ዋግህምራ፣ ሰሜን ወሎና ደቡብ ወሎ ዞኖች በርካታ አካባቢዎች ከሕወሓት ታጣቂዎች ጋር የእግረኛ ውጊያ ቀጥሏል፡፡

በተለይም ወሎ ውስጥ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል፣ ከሚሊሻና ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ከሕወሓት ታጣቂዎች ጋር እያደረጉት ያለው ጦርነት፣ የሰሜን ወሎ ዞን ተሻግሮ በደቡብ ወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሏል፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሺያ በወሎ ግንባር በወረባቦ፣ በተሁለደሬ፣ በኩታበርና ደላንታ በወሰዱት የፀረ ማጥቃት ዕርምጃ፣ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱ መሆናቸውንና ሕወሓት በእነዚህ አካባቢዎች ያሠለፋቸው በርካታ ታጣቂዎችን ሙትና ቁስለኛ እንዳደረጓቸው አስታውቋል፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ተስፋው ባታብል ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የሚኖርበት ሰሜን ወሎ ሙሉ በሙሉ በሕወሓት ቁጥጥር ሥር ነው፡፡ ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከ350 ሺሕ በላይ የሚሆነው በደሴና በባህር ዳር ተፈናቅሎ በመጠለያ ውስጥ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ስለሚያስተዳድሯት ዞን ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው የተናገሩት አስተዳዳሪው፣ አመራሩንና ወጣቱን አደራጀተው በደሴ፣ በራያና በመቄት ግንባሮች የሽምቅ ውጊያ እያደረጉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

‹‹ምንም እንበሕወሓት ቁጥጥር ሥር ላለው የሰሜን ወሎ ዞን ዕርዳታ እንዲቀርብ ለመንግሥትም ሆነ ለድርጅቶች ጥያቄ ብናቀርብም፣ እስካሁን ምንም ዓይነት የዕርዳታ ድርጅትም ሆነ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የሰብዓዊ ዕርዳታ እያቀረቡ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

በደቡብ ወሎዋ ሐይቅ ከተማና  በቅርብ ርቀት በሚካሄደው ውጊያ ምክንያት ከደሴ ወደ አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ቦረና፣ እንዲሁም ወደ ሌሎች ቦታዎች የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከቀን ቀን እየጨመረ መሆኑን፣ የትራንሰፖርት ዋጋም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ከመምጣቱም በላይ ተሽከርካዎችን ለማግኘትና ወደ መሀል አገር ለመጓዝ ቀናት መጠበቅ ግድ እንዳላቸው፣ አዲስ አባባ የደረሱ ተፈናቃዮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...