Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት እነ አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ ጥፋተኛ ተባሉ

በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት እነ አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ ጥፋተኛ ተባሉ

ቀን:

የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ከነበሩት አቶ አብዲ መሐመድ (አብዲሌ)  በክልሉ ከተሞች ማለትም ጅግጅጋና ሌሎች ከተሞች ተፈጥሮ በነበረው ከባድ ወንጀል ምክንያት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ሲውሉ፣ ተጠርጥረው ታስረው የነበሩት እነ አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) ትናንት ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. በተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ፡፡

ክሱን ሲመረምር የከረመው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አምስተኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ፣ ከቀድሞ የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ከአቶ መሐመድ አህመድና የሶማሌ ትምህርት ቢሮ የፋይናንስና ሎጂስቲክ የሥራ ሒደት ኃላፊ አቶ አብዱላሂ ሁሴን ጋር በመመሳጠር፣ ለክልሉ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች መማሪያ የሚሆን 578,274 መጽሐፍቶች በ18,990,000 ብር ታትሞ እንዲቀርብ የግዢ ውል አያይዘው ነበር።

ግዥውን ከመንግሥት የግዢና አስተዳደር መመርያ ውጪ በተያያዘ ውል ስምምነት ለመፈጸም፣ የቀድሞ የኒያላ ኢንሹራንስ ጂጂጋ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ይሠራ የነበረው አቶ አብዲ የሱፍ የኢንሹራንሱን የዋስትና ስምምነት መመርያና አሠራር በመጣስ፣ ከኃላፊነቱ ውጪ የቅድሚያ ማስያዣ ሳያሲዝ ያለ አግባብ ለአቶ ቴድሮስ አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ ) 15,306,803 ብር ክፍያ እንዲከፈለው ማድረጉን ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ በምስክሮችና በሰነድ ማስረጃዎች ማረጋገጥ መቻሉን በውሳኔው ተጠቁሟል፡፡

የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው የቀድሞ የኒያላ ኢንሹራንስ ጅጅጋ ቅርጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዲ የሱፍ መሐመድና የሶማሌ ፕሪንቲንግ ፕሬስ ድርጅት ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴድሮስ አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) ክፍያው ተከፍሏቸው የተማሪዎቹ መጽሐፍቶች አትመው መቅረብ ሲገባቸው ያላቀረቡ በመሆናቸውና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1ሀ) እናለ)፣ አንቀጽ እና የሙስና ወንጀል አዋጅ ቁጥር 881 /2007 አንቀጽ 13(1ሐእና3) መተላለፋቸው በመረጋገጡ፣ በቀረበባቸው የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ ጥፋተኛ መባላቸውን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡ የተከሳሾቹን መከላከያ ማስረጃዎችን የመረመረው ፍርድ ቤቱ በተሳትፎ ደረጃቸው በተከሰሱበት አንቀጽ ወንጀሉን ስለመፈጸማቸው በማስረጃ በመረጋገጡ የጥፋተኝነት ፍርድ እንዳስተላለፈ ጠቁሞ፣ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ለመጠባበቅ ለጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...