Thursday, March 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የታሸጉ ድርጀቶች ሥራ ሊጀምሩ ነው

ከሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የታሸጉ ድርጀቶች ሥራ ሊጀምሩ ነው

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሽብርተኝነት የተሰየመውን ሕወሓት ይደግፋሉ ተብለው የታሸጉ ፋብሪካዎችና ሌሎች የንግድ ድርጅቶች፣ አስተዳዳሪ ተሾሞላቸው በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምሩ ፍትሕ ሚኒስቴር  አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከጥቂት ወራት በፊት በርካታ የንግድ ድርጅቶችና ሆቴሎች  የንግድ ሕጉን በመጣስና የሕወሓትን የሽብር ተግባር በመደገፍ በመጠርጠራቸው ታሽገው እንዲቆዩ መደረጋቸው ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ በርካታ የንግድ ድርጅቶች ተመልሰው ወደ ሥራ እንዲገቡ ቢደረግም፣ ቁጥራቸውን በግልጽ ለማወቅ ያልተቻሉ ትልልቅ ሆቴሎች ተዘግተው ቆይተዋል፡፡

ከሆቴሎቹ መካካል ካሌብ ሆቴል፣ ኔክሰስ ሆቴል፣ አክሱም ሆቴል፣ ንግሥተ ሳባ ሆቴል፣ ሐርመኒ ሆቴልና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

ማክሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፍትሕ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ፈቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት፣ በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን የንግድ ድርጅቶችና ሆቴሎች አስተዳዳሪ ተሾሞላቸው ሥራቸውን እንደገና እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየተሠራ ነው፡፡ ነገር ግን በድርጅቶቹ ላይ የሚደረገው ምርመራ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር በወንጀል የተጠረጠሩትን ተቋማትና ግለሰቦች ወደ ፍርድ እንደሚያቀርብ በመጥቀስ፣ የከተማ አስተዳደሩ ደግሞ ድርጅቶቹን ለመክፈት ወይም ላለመክፈት አስተዳደራዊና የወንጀል ሕጉን መሠረት በማድረግ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስረድተዋል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ፈቃዱ ፀጋ

በሆቴሎችም ሆነ በንግድ ድርጅቶች ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሠራተኞች ሥራ አጥ መሆን እንደሌለባቸው የገለጹት አቶ ፈቃዱ፣ ድርጅቶቹ በታቻለ መጠን ወደ ሥራ እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን አክለው ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ለሕወሓት ድጋፍ ያደርጋሉ የተባሉ ወይም በድርጅቶቹ የበላይ ኃላፊዎች አማካይነት ይዘወራሉ ተብለው የተጠረጠሩ ሕንፃዎች፣ በፍርድ ቤት ውሳኔ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አስተዳዳሪ ሆኖ እያከራያቸው፣ የባንክ ብድር ካለባቸውም እየከፈሉ ሥራ ላይ እንዲቆዩ መደረጉን አውስተዋል፡፡

በምርመራ ላይ ያሉትን ሆቴሎችንም ሆነ ፋብሪካዎችን ቀጣይ ዕድል ለማወቅ፣ ፍትሕ ሚኒስቴር ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ውሳኔ ያሰጥባቸዋል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የታሸጉና የተዘጉ ሆቴሎች በዋነኝነት ገንዘብ በማሸሽ፣ ጦርነቱን ከሕወሓት ጎን በመሆን በፋይናንስ በማገዝ በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ማስረጃ የተገኘባቸው መሆኑንና ጉዳያቸውም ክትትል እየተደረገበት መሆኑን ሚኒስተር ዴኤታው አስታውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...