– ይቅርታ ይህን ቅርጽ የሠራኸው አንተ ነህ?
* እኔ ነኝ
– ሰውየው…
* ያው ወታደር ናቸው
– ማለቴ..
* መነሻ ሐሳቡን ሊጠይቁኝ ነው?
– የለም! ማዕረጋቸውን ለመለየት…
* ጄኔራል ናቸው
– ምነው ታዲያ?!
* ምነው?
– ሽብርክ ማለታቸው ትንሽ ፈገግ አላሰኘም
* ጉዳዩ ሌላ ነው
– እንዴት?
* ሥራው ሲጀመር ፈረሰኛ እንዲሆኑ ነበር
– ታዲያ?!
* አሠሪ ኮሚቴው ገንዘብ ስለአጠረው ፈረሱ ቀረ
– ‹‹ጠብታ›› (1999)