የምላስ ንግግር፣
ተገላጭ በከንፈር፣
ለጊዜው ቢያስደስት…
ሩቅ አያሻግር፣
በድካም ተዘርቶ…
ምርት እንደማይሰጥ ዘር፡፡
ቆይ ብቻ…ቆይ ብቻ!!
ትርጉም የለሽ ዛቻ፣
በእጅ የያዙት ዕድል…
አንዴ ካመለጠ…
ዳግም ላይመለስ…
በትርክት ዘመቻ፡፡
ዛቻና ፉከራው፣
ልብ ለሌለው…ለማይረባው፤
ምን ሊዘይድ…ምን ሊረባ??
ወደ ተግባር ካልተገባ፡፡
- ኤፍሬም አብርሃም ‹‹ካድማስ ወዲያ ማዶ›› (2013)