Thursday, May 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊ‹‹በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሚመዘገበው ሞት ከስድስት በመቶ በላይ በስትሮክ  የሚከሰት ነው›› የጤና...

‹‹በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሚመዘገበው ሞት ከስድስት በመቶ በላይ በስትሮክ  የሚከሰት ነው›› የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ ዱጉማ (ዶ/ር)

ቀን:

የአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ ስትሮክ አንጎልና የደም ሥር ላይ ከሚከሰቱ ሕመሞች አንዱ ነው፡፡ ባለሙያዎች ስትሮክ ድንገተኛ የሆነ አንጎል ውስጥ የደም ሥርጭት መዛባት ችግር እንደሆነ፣ የደም ሥርጭት መቀነስን ወይም መጨመርን ተከትሎም የሚከሰት ሕመም መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ በዓለም ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ እንደመጣ የሚነገርለት ስትሮክ በዓመት በርካታ ሰዎችን ለድንገተኛ ሞት፣ እንዲሁም አካል ጉዳት እያደረገ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ ከጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ሳምንት እየተከበረ ያለውን የዓለም የስትሮክ ቀን በማስመልከት ጥቅምት 17 ቀን በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ ዱጉማ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሚመዘገበው አጠቃላይ የሞት ምጣኔ 6.23 በመቶው በስትሮክ ሳቢያ የሚከሰት ነው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃም በየዓመቱ 13.7 ሚሊዮን ሰዎች በስትሮክ ሳቢያ ለሕመም፣ እንዲሁም በዓመት ከአምስት ሚሊዮን በላይ በየአራት ደቂቃው ደግሞ አንድ ሰው ለሕልፈተ ሕይወት እንደሚዳረጉ፣ የሕመሙን አስከፊነት በአግባቡ ግንዛቤ በመያዝ ኅብረተሰቡ ራሱን መጠበቅና መከላከል እንዳለበት ነው ሚኒስትር ዴኤታው የተናገሩት፡፡

- Advertisement -

የዓለም ስትሮክ ቀን፣ አንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ፣ የጤና ሚኒስቴር

ጤና ሚኒስቴር ስትሮክን ለመከላከል የጤና ባለሙያዎችን በብዛት በማሠልጠን ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲሰጡ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸው፣  በሽታውን ለማከም ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅመሆኑ የተነሳ መንግሥት በተቻለ መጠን መድኃኒቶችንና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በየጤና ተቋማቱ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡  

የኢትዮጵያ ኒዩሮሎጂስቶች ማኅበር ጸሐፊ ሜሮን አውራሪስ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኅብረተሰቡ ከስትሮክ ራሱን ለመጠበቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የስብ መጠንን ማስተካከል እንዲሁም አስፈላጊውን የጤና ምርመራ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የስትሮክ መንስዔ

‹‹ስለጤናዎ ምን ያውቃሉ? ጠቅላላ ዕውቀት›› በሚል ርዕስ በድረ ገጽ ላይ የቀረበው ሐተታ፣ የዓለም ጤና ድርጅት በአንጎልና በደም ስሮች ላይ በሚከሰቱ ሕመሞች ዙሪያ ያደረጋቸው ጥናቶችን ዋቢ እንዳደረገው፣ ስትሮክ በተለይ ባደጉ አገሮች ከልብ ሕመምና ከካንሰር በመቀጠል ሦስተኛ የሞት መንስዔ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡

የአሜሪካ የሕክምና ባለሙያዎች ማኅበር ዓመታዊ ጆርናል የስትሮክ ሕመም ሦስት ዋና ዋና ደረጃዎች እንዳሉት ይገልጻል፡፡ በዚህም መሠረት ድንገተኛው ስትሮክ በዋናነት የሚጎዳው አንጎልን ነው፡፡ አንጎል ላይ የሚደርስ ጉዳት ደግሞ በመቀጠል የደም ሥሮችን የነርቭ ሥርዓት ይጎዳል፡፡

በስትሮክ ሕመም ሕክምና ላይ ስፔሻላይዝ ያደረጉት አንቶኒዮ ጉቲሬዝ (ዶ/ር) የስትሮክ ሕመም ዋና ዋና አጋላጭ ምክንያቶች በሚል የሚከተሉትን ነገሮች በመንስዔነት ያቀርባሉ፡፡ በአንጎል ውስጥ በሚከሰት ድንገተኛ የደም ሥርጭት መዛባት የሚገለጸው ስትሮክ የሚከሰተው የደም ሥሮች መጥበብን፣ በተለያዩ ምክንያቶች የደም ሥሮች በድንገት መቀደድንና ደም በዘፈቀደ አንጎል ውስጥ መፍሰስን፣ በተለያዩ ምክንያት በሚከሰት የደም መርጋት ችግር የተነሳ ወደ አንጎል የሚደረገው የደም ሥርጭቱን ማስተጓጎልን፣ የደም ሥሮች በድንገት መኮማተርን ተከትሎ እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ሕመሞች የተነሳ የደም ዝውውር መስተጓጎል፣ በተለይ ደግሞ በደም ግፊትና በስኳር ሕመም መጠቃትን ተከትሎ አንጎል ውስጥ ያለው የደም ፍሰት ሥርዓት መዛባት፣ በተለያዩ የደም ሥር ሕመሞች መጠቃት እንደ አንቶኒዮ (ዶ/ር) ገለጻ የስትሮክ ዋነኛ መምጫ መንገድ ነው፡፡

‹‹ከሁሉም በላይ ግን የደም ግፊትና በቁጥጥር ሥር መዋል ያልቻለ ስኳር ሕመም ለስትሮክ ዋነኛ አጋላጭ ምክንያቶች ናቸው፡፡ በተለየ መልኩ ደግሞ የአመጋገብ ባህላችን፣ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ረዥም ሰዓት ተቀምጦ መዋል የስትሮክ ዋነኛ መንስዔ ነው›› ይላሉ የስትሮክ ሕመም ስፔሻሊስቱ፡፡

በተለይ የደም ግፊትና የስኳር ሕመም ባለባቸው ሰዎች ላይ በድንገት የሚከሰት የራስ ምታት ሕመም፣ በተደጋጋሚ ማስመለስ፣ የማቅለሽለሽ ስሜትን ማስተናገድ፣ የማጅራት አካባቢ ሕመምና የማጅራት መገታተር፣ ድንገተኛ ፊት መጣመም እንዲሁም እጅና እግር መዛልና የጡንቻዎች መዛል፣ በድንገት ግማሽ ወይም ሙሉ የአካል ክፍል መደንዘዝ፣ የእጅ፣ የእግርና የፊት ሕመም የሕመሙ ዋነኛ ምልክቶች ናቸው፡፡

ስትሮክ ከመከሰቱ በፊት ባሉት ሳምንታት በድንገት ብርድ ብርድ ማለት፣ የጡንቻዎች ሕመሞች፣ የሰውነት በቀላሉ መድከም፣ የመናገር ችግርና የአንደበት መያያዝ ችግር መከሰት፣ መንተባተብ፣ ጆሮ ላይ የሚደርስ ጉዳትን ተከትሎ የሰዎችን ንግግር ለመስማትና ለመረዳት መቸገር፣ አካላዊ ሚዛን ለመጠበቅ መቸገር፣ ሲንቀሳቀሱ መንገዳገድ፣ የእጅና የእግር ጡንቻዎች መንቀጥቀጥ፣ የዕይታ አቅም መቀነስ (የዕይታ የጥራት መቀነስና ብዥታ) እንዲሁም ሽንትና ሰገራን መቆጣጠር አለመቻል የስትሮክ ሕመም ዋነኛ ምልክቶች ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...