የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ጥቅምት 20 ቀን 2014 ዓም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ውጤት መሠረት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 11ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ ወስኗል።
ምክር ቤቱ ባካሄደው ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን አንደኛ ዓመት የስራ ጊዜ አንደኛ አስቸኳይ ስብሰባ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ውጤትን መርምሮ አጽድቋል።
ምክር ቤቱ ህዝበ ውሳኔውን ያጸደቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰበሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሪፖርት ካቀረቡና የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሃሳብ ካቀረበ በኋላ ነው።
ምክር ቤቱ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 11ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ በሙሉ ድምጽጽ አጽድቋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ራሳቸውን ችለው በክልልነት ለመደራጀት መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ሕዝበ ውሳኔ ማካሄዳቸው ይታወሳል።
ለህዝበ ውሳኔው በተካሄደው ድምፅ አሰጣጥ አምስቱ ዞኖችና አንዱ ልዩ ወረዳ አንድ የጋራ ክልል መመሥረቱን ደግፈው 1, 221,092 ድምፅ ሰጥተዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት አንዱ የብሔር ብሔረሰቦችን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ወይም ራስን በራስ የማስተዳዳር ጥያቄዎችን ሕገመንግስቱን መሠረት አድርጎ እልባት መስጠት መሆኑ ይታወቃል።