የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ ከንጉሥ ተፈሪነት ወደ ንጉሠ ነገሥት አፄነት በጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም. ከተሸጋገሩ በኋላ ለ44 ዓመታት ግድም ኢትዮጵያንና ሕዝቧን መርተዋል፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ዘውድ የደፉበት፣ ሉል የያዙበት፣ ሰይፍ የጨበጡበት ‹‹ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ›› (የይሁዳ ነገድ የሆነው አሸናፊው አንበሳ፣ የንጉሦች ንጉሥ ሆኖ በእግዚአብሔር የተሾመው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ) ከተባሉ ማክሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. 91 ዓመት ሞላቸው፡፡
- ሔኖክ መደብር