Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልለክብር የበቁት የሴቶችን ጥቃት ያወገዙ ፊልሞች

ለክብር የበቁት የሴቶችን ጥቃት ያወገዙ ፊልሞች

ቀን:

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ለማበረታታትና ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የተለያዩ ተቋማት ብቅ ብቅ እያሉ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ውስጥም የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶችን በማውገዝ የፊልም ኢንዱስትሪው ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሙያዎች ዓርብ ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል ዕውቅናና ሽልማቶችን አበርክቷል፡፡

በሽልማት መርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሳ ቢየና እንደገለጹት፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን ፆታዊ ጥቃት በፊልም ኢንዱስትሪው ላይ በማሳየትና ያሉትን ችግሮች ወደ አደባባይ በማውጣት ትልቁን ሚና ለተጫወቱ ባለሙያዎች በማበረታቻ ሽልማት መዘከር ይገባል፡፡ 

በሴቶች ላይ እየታየ ያለው ጫና ለመቅረፍ ማኅበሩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ሌንሳ፣ ማኅበራቸው በአዳማ፣ በሐዋሳ፣ በባህር ዳር፣ በድሬዳዋ፣ በጋምቤላና በሌሎች ከተሞች በመሄድ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ነድፎ እየሠራ መሆኑን አክለዋል፡፡

ዘንድሮም ለመጀመርያ ጊዜ የተካሄደው ይህ የሽልማት ፕሮግራም በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ውጣ ውረዶች በፊልም በማሳየት ጉልህ ሚና ለተጫወቱ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ማበረታቻ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ማኅበሩም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር አጋርነት በመፍጠር የተለያዩ ፕሮጀክቶች በመንደፍ በአገር አቀፍና አኅጉር አቀፍ ደረጃ የሚሠራ ሲሆን፣ ከእነዚህም ፕሮጀክቶች መካከል ከሲሃ ኔትወርክ (Strategic Initiative for Women in the Horn of Africa (SIHA Net Work)) ጋር በመተባበር በምሥራቅ አፍሪካ ደረጃ እየተተገበረ የሚገኘው ‹‹አንጠብቅም›› (We cannot wait) የተሰኘው በሴቶች ላይ የሚሠራው ፕሮጀክት ተግባራዊ እየሆነ ነው ሲሉ ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

ተሸላሚዎቹ እነማን ናቸው?

ለውድድሩ 30 ፊልሞች መቅረባቸውን፣ ከእነዚያ ውስጥም አምስት ፊልሞች ለዕጩነት እንደቀረቡ የማኅበሩ ቦርድ አባል ወ/ሮ ማህሌት ፍፁም ገልጸዋል፡፡

ለዕጩነት ከቀረቡት አምስት ፊልሞች ውስጥ ሔርሜላና ፍሬ የተሰኙት ፊልሞች የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃን አግኝተዋል፡፡

ለሽልማት የበቁትም ሁለቱ ፊልሞች የሴቶች ፆታዊ ጥቃት ለማኅበረሰቡ በተገቢው መንገድ ያሳወቁ መሆናቸውን ወ/ሮ ማኅሌት አስረድተዋል፡፡

የሽልማት መርሐ ግብሩም በቀጣይ በየዓመቱ የሚካሄድ መሆኑን ያስታወሱት ወ/ሮ ማኅሌት፣ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን በደል በድራማ፣ በሙዚቃ፣ በቴአትር፣ በሥዕል፣ በግጥምና በሌሎች ዘርፎች ለሚያሳዩ ባለሙያዎች ሽልማት የሚሰጥ መሆኑን አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የፊልም ፕሮዲውሰሮች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ቢኒያም ዓለማየሁ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በሴቶች ጥቃት ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለማስቆምና መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሠራ ለመጎትጎት ሽልማቱ የሚበረታታ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በሴቶች ጥቃት ላይ ትኩረት ሰጥተው እየተሠሩ ያሉ ፊልሞች እንዳሉ፣ ይህንንም አጠናክሮ ለመቀጠል፣ እንዲሁም ኢንዱስትሪውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የኢትዮጵያ የፊልም ፕሮዲውሰሮች ማኅበር ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ጋር በቅንጅት የሚሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በእርግጥ የፊልሞቹ ይዘት በሚገባ ታይተዋል ወይ? ሴቶች ላይ ያጠነጠነ ፊልም ተሠርቷል? የሚለውን ጥያቄ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ፕሬዚዳንቱ እንዲህ ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡ ‹‹በመጀመርያ ደረጃ በሴቶች ጥቃት ላይ የሚያተኩሩ ፊልሞች ከፍተኛ የሆነ ጥናት የሚጠይቁ መሆናቸውን፣ ከዚህ በኋላ ዘርፉ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል፡፡››

በቀጣይም ማኅበሩ የሴቶች ጥቃት ላይ የሚያተኩሩ ፊልሞች እንዲሠሩ ከተለያዩ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር የሚሠራ መሆኑንም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...