Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመኖሪያ ቤትም ሆነ ንግድ ቤቶችንና ተሽከርካሪዎችን ያከራዩ በአስቸኳይ ለፖሊስ እንዲያሳውቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ

መኖሪያ ቤትም ሆነ ንግድ ቤቶችንና ተሽከርካሪዎችን ያከራዩ በአስቸኳይ ለፖሊስ እንዲያሳውቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ

ቀን:

መንግሥት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኛነት በተፈረጀው ሕወሓት ላይ እየወሰደ ያለው ሕጋዊ ዕርምጃ ውጤታማ እንዲሆን የነቃ የሕዝብ ተሳትፎ ወሳኝ ስለሆነ ኅብረተሰቡ ያከራያቸውን መኖሪያ ቤቶች፣ ንግድ ቤቶች፣ መጋዘኖች፣ ድርጅቶችና ተሽከርካሪ ተከራዮችን ማንነት በጥንቃቄ በማጣራት በአስቸኳይ ለፖሊስ እንዲያሳወቁ የአዲስ አበባን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የተቋቋመው የደኅንነትና የፀጥታ ግብረ ኃይል አሳሰበ፡፡

ግብረ ኃይሉ በሰጠው መግለጫ እንደገለጸው፣ የኢትዮጵያ ቀንደኛና አደገኛ የሰላም ሥጋት የሆነው ቡድኑ፣ ሕዝቡን ለማሸበርና ለማደናገር የተዛቡና ሐሰተኛ መረጃዎች እያሠራጨ ነው፡፡ የሽብር ቡድኑ ጥቅምት 24 ቀን 2013 .ም. በሰሜን ዕዝ ላይ ከፈጸመው ጥቃት ባለፈ አገር የማፍረስ ዓላማውን አጠናክሮ በመቀጠል የኢትዮጵያን የዕልቂት ዓውድማ ለማድረግ መረቡን ዘርግቶ ቢንቀሳቀስም፣ በሕዝብና በፀጥታ አካላት ትብብር መከላከሉን ግብረ ኃይሉ አክሏል፡፡

የአዲስ አበባን ሰላምና ፀጥታ በሚፈታተኑ ጉዳዮች ላይ የማያዳግም ሕጋዊ ዕርምጃ መውሰድ መጀመሩን፣ በጥምረት በመሥራትም የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደኅንነት ማስጠበቅ መቻሉን፣ የሕወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ወደ ግጭትና ትርምስ በመክተት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የጎነጎነውን ሴራ ለማክሸፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

ታጣቂ ቡድኑ ለ27 ዓመታት ሲያደርገው እንደነበረው ዛሬም በሕዝቦች መካከል የተለያዩ የጥላቻና የልዩነት ወሬዎችን በማናፈስ፣ ሕዝብ በሕዝብ ላይ እንዲነሳ ልዩ ልዩ ሴራዎችን ሸርቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንና የጥፋት ኃይሉ በተደጋጋሚ ባስተላለፈውና ደጋፊዎች ባናፈሱት የተዘባ መረጃ በአማራና በአፋር ክልሎች በርካቶችን ከቀዬአቸው ማፈናቀሉንና ንፁኃንን መግደሉንም ጠቁሟል፡፡

መኖሪያ ቤት ተከራይተው በጋራ የሚንቀሳቀሱና ሰዋራ ሥፍራ በመምረጥ ግንኙነት የሚያደርጉ የቡድኑ ደጋፊዎችና ናፋቂዎች መኖራቸውን፣ በተጨማሪም ደጋፊዎቹ ኅብረተሰቡን ለማደናገርና የጥፋት ተልዕኳቸውን ዕውን ለማድረግ ይረዳቸው ዘንድ የተለያዩ የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ በመልበስ ለመንቀሳቀስ ዕቅድ እንዳላቸው ጠቁሞ፣ ኅብረተሰቡ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት በአካባቢው ላለ የፀጥታና የደኅንነት ተቋማት በአስቸኳይ እንዲያሳውቅ ጠይቋል።

ሐሰተኛ መረጃ የሚያስተላልፉና የሚያስተጋቡ አካላት ከሕገወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስቦ፣ የፀጥታ አካላት በታጣቂ ቡድኑ ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ እየወሰደ መሆኑን ሕዝቡ ተገንዝቦ፣ በየአካባቢው በመደራጀትና በመቀናጀት ለፀጥታ አካሉ እየሰጠ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የጋራ ግብረ ኃይሉ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...